TIKVAH-ETHIOPIA
#OlusegunObasanjo በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲቆም እና ሰላም እንዲወርድ መፍትሄ እያፈላለጉ ያሉት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ ወደ አማራ ክልል አፋር ክልል ይጓዛሉ። ኦባሳንጆ ከቀናት በፊት ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ተጉዘው እንደነበር አይዘነጋም። ዛሬ ወደ ባህር ዳር እና ሰመራ በማቅናት ከክልሎቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እያደረጉት ስላለው የሰላም ጥረት ይወያያሉ ተብሏል፤ እስካሁን ስለጉዟቸው…
#OlusegunObasanjo

ትናንት በወቅታዊ የአፍሪካ የጸጥታ ሁኔታዎች ላይ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ስበስባ ተቀምጦ ነበር።

በዚህ ስብሰባ ላይ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ በመደረግ ላይ ስላሉ የሰላም ጥረቶች ገለጻ አድርገዋል፡፡

በገለጻቸውም በአዲስ አበባ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ ከፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር መነጋገራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ውጥረቱን ለማርገብ እና ለቀጣይ ውይይቶች ምቹ መደላድልን ለመፍጠር የሚያስችል ፍሬያማ ንግግር ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ከተነጋገሩና ወደ ትግራይ እንዲያቀኑ ከተስማሙ በኋላ እሁድ ጥቅምት 28 ቀን 2014 ዓ/ም በመቐለ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካዔልን ጋር ተገናኝተው ውጥረቱን ለማርገብና አመርቂ መፍትሄዎችን ለመፈለግ የሚያስችል ምክክር ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ እና በሰሜን ያሉ ሁሉም መሪዎች በመካከላቸው ያለው ችግር ፖለቲካዊ እንደሆነና በውይይት ሊፈታ የሚችል ፖለቲካዊ መፍትሄን እንደሚፈልግ በግለሰብ ደረጃ መስማማታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ችግሩ የከፋ ማህበረ ምጣኔ ሃብታዊ እና ሰብዓዊ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን በመጠቆም ዘላቂ እልባት ለመስጠት መፍጠን እንደሚያስፈልግ ኦባሳንጆ ተናግረዋል።

የጸጥታው ምክር ቤት ሁሉም አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁመው ወደ ውይይት እንዲመጡ፣ ያልተቆራረጠ የሰብዓዊ እርዳታዎች አቅርቦት እንዲኖር፣ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ እና ሁሉን አካታች ብሔራዊ ውይይት በአፋጣኝ እንዲደረግ ግፊት እንዲያደርግና ሁኔታዎችን በአንክሮ እንዲከታተል አሳስበዋል፡፡

Credit : አል ዓይን

@tikvahethiopoa