TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Audio
#Audio : ዛሬ አ/አ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ታዳሚው እነ CNN፣ አልጀዚራ፣ BBC ፣ ሮይተርስ በመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ እጅግ ኃይለኛ ትችት እና ወቀሳን ሰንዝሯል።

የሚዲያ ተቋማቱ እጃቸውን ከኢትዮጵያና ከህዝቧ ላይ እንዲሰበስቡ ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዲሁም ውሸቶችን ለዓለም ህዝብ ከማሰራጨት እንዲታቀቡ ሰልፈኞች አሳስበዋል።

ህወሓት /TPLF/ አሸባሪ ድርጅት ነው ያሉት የሰልፉ ታዳሚዎች አሜሪካ ለቡድኑ የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆምም ጠይቀዋል።

የሰልፉ ታዳሚያን በአሜሪካው ፕሬዜዳንት #ጆ_ባይደን አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ወቀሳን በእንዲሁም ትችት የሰነዘሩ ሲሆን ሀገራቸው አሜሪካ እጇን ከኢትዮጵያ ላይ እንድታነሳ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ታዳሚያኑ TPLF ሆነ ማንኛውም የውጭ አካል ኢትዮጵያን የማፍረስ አንዳችም አቅም የላቸውም ያሉ ሲሆን ፥ " ኢትዮጵያ ታሸንፋለች ! ህዝቧም ይወክለኛል ያለውን መንግስት መርጧል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"እንፀልይ" ፖፕ ፍራንሲስ ፥ ዛሬ እሁድ ባስተላለፉት መልዕክታቸው በከባድ ሰብአዊ ቀውስ ለተጎዳው ለኢትዮጵያ ፣ የትግራይ ህዝብ ቅርብ ነኝ ብለዋል። ግጭት እንዲቆም ፣ የምግብና ጤና ዕርዳታ ተደራሽነት ለሁሉም እንዲረጋገጥ እና ማህበራዊ መግባባት በተቻለ ፍጥነት እንዲመለስ በጋራ #እንፀልይ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። @tikvahethiopia
ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ።

በኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲቆም ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንዲደረግ ብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዛሬ ጥሪ አቀረቡ።

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ጊዜያት የሰላም ጥሪያቸውን ሲያሰሙ ነበር።

ዛሬ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በነበረ መርሃ ግብር ላይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ባሰሙት ንግግር ከኢትዮጵያ የወጡትን ዜናዎች እየተከታተሉ መሆኑን ገልፀዋል።

“ከ1 ዓመት በላይ በዘለቀው ግጭት በርካታ ሰዎች ተጎጂ መሆናቸው እና ግጭቱ ከባድ ሰብዓዊ ቀውስን ያስከተለ መሆኑን የሚገልፁ ዜናዎችን “በአሳሳቢነት” እየተከታተልኩ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ወንድማማችነት መግባባትና ሰላማዊ የውይይት መንገድ እንዲሰፍን ጥሪዬን አቀርባለሁ" ብለዋል።

@tikvahethiopia
#Mekelle

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊ እና የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ የሆኑት ማርቲን ግሪፊትስ እና በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ዛሬ የትግራይ ክልል መዲና መቐለ መግባታቸውን ሮይተርስ ከአንድ የሰብዓዊ ድጋፍ አድራጊ ምንጭ እና ጉዳዩን ከሚያውቅ አንድ ሰው መስማቱን ዘግቧል።

በኢትዮጵያ የሚገኘው የUN የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ቃል አቀባይ በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ አልሰጠም።

በኒውዮርክ የሚገኙ የUN ባለስልጣናት ስለጉዳዩ መረጃ እንዲሰጡ ወዲያውኑ ማግኘት እንዳልተቻለ እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ቃል አቀባይ ኢባ ካሎንዶ አስተያየት እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አለመስጠታቸውን የዜና ወኪሉ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ ዶክተር ለገሰ ቱሉ በባለስልጣናቱ ጉብኝት ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አለመስጠታቸውን ዜና ወኪሉ ዘግቧል።

ከዚሁ ጋር በተገናኘ ዘግይቶ በወጣ መረጃ ሁለቱም ባለስልጣናት በመቐለ ከዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውና ማምሻውን ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊና የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ የሆኑት ማርቲን ግሪፊትስ ከቀናት በፊት አዲስ አበባ መግባታቸው እና ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ጉዳይ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።

የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት እና የአሁኑ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ቆሞ ሰላም እንዲወርድ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ መሆናቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ህወሓትን እና ሸኔን የሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ነው። በሰልፉ ላይ የውጭ ሀገር ጣልቃ ገብነትንና የውጭ ሀገር መገነኛ ብዙሃንን አጥብቀው የሚተቹ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ የተፃፉ የተለያዩ መፈክሮች በሰልፈኞች ተይዘዋል። ሰልፈኞች ካያዟቸው መፈክሮች መካከል ፦ - የአሜሪካ…
" ... ሕዝብ ተናግሯልና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሊያዳምጥ ይገባል " - የመንግስት ኮሚኒኬሽን

ሰሞኑን በተለያዩ ክልሎች ከ30 ሚልዮን በላይ ሕዝብ ዐደባባይ ወጥቶ ስለሀገሩ ተናግሯል ሲል የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን " ህዝቡ ኢትዮጵያን ለማዳን እስከ ሕይወት መሥዋዕትነት እንደሚከፍል፣ ለጸጥታ ኃይሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ፣ ማንኛውንም የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደማይቀበል፣ የሕወሐትንና አጋር ጽንፈኛ ኃይሎችን ሀገር የማፍረስ የሽብር ተግባራት አጥብቆ እንደሚያወግዝ በግልጽ ተናግሯል" ሲልም አክሏል።

አንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች፣ ዲፕሎማቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ስለ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፉትን የተዛባ መረጃ ሕዝቡ መኮነኑንም ገልጿል።

" የሚያስተዳድረውን መንግሥት ነጻ፣ ገለልተኛና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መምረጡንና ይህንን ውሳኔውንም ዓለም እንዲያከብርለት ሕዝቡ አጥብቆ ጠይቋል። ሕዝቡ ሀገሩን ለማዳን ማንኛውንም መሥዋዕትነት እንደሚከፍል በተግባር አሳይቷል " ብሏል።

ሕዝቡ በወራሪው በተያዙ አካባቢዎችም በከፍተኛ ግለት እየተነሣ ነው ያለው የመንግስት ኮሚኒኬሽን " በተወረሩ አካባቢዎች የሚገኘው ሕዝብ ጽንፈኛውን ሕወሐት ምቾት ተሰምቶት እንዳይቀመጥ እያደረገው ይገኛል" ብሏል።

አክሎ ፥ " ይህ የሕዝብ ንቅናቄ አሸባሪውን በሁሉም ቦታዎች እግር በእግር እየተከታተለ ርምጃ በመውሰድ አከባቢዎችን ተገድዶ እንዲለቅ እያደረገው ይገኛል " ሲል ገልጿል።

ያንብቡ : telegra.ph/ETHIOPIA-11-07-2

ፎቶ ፦ አቤል ጋሻው

@tikvahethiopia
#Harari

ከፌደራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መምሪያ የሚተላለፉ መመሪያዎች እንደተጠበቁ ሆነው÷ የሀረሪ ክልል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ በክልሉ ውስጥ ከጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የክልከላ መመሪያዎች አውጥቷል።

ክልከላዎቹም ፦

1. ከፀጥታ አካላት ውጪ ማንኛውም እግረኛ በክልሉ ውስጥ ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 11:00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

2. ከአምቡላንስ እና ከጸጥታ አካላት ተሽከርካሪ ውጪ ማንኛውም ተሸከርካሪ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 11:00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎችና ሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች ከከተማው በስተጀርባ ያለውን መንገድ ወይም ባይ ፓስ መጠቀም ይችላሉ።

3. የክልሉ ሰሌዳ የሌላቸው ማናቸውም ታክሲዎች (ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪናዎች ጨምሮ) ወደ ክልሉ መግባት አይችሉም፤ የክልሉ ሰሌዳ ያላቸው ታክሲዎችም ወደ ሌላ ክልል መውጣት የተከለከለ ነው።

4. ከህክምና ተቋማትና የመድኃኒት ቤቶች በስተቀር ማንኛውም የንግድ ተቋማት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 11:00 ሰዓት አገልግሎት መስጠት አይችሉም።

#Share #ሼር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ከ5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስገልገዋል " - የአማራ ክልል መንግስት የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስታና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ፥ በክልሉ ህወሓት ወረራ በፈፀመባቸው ዞኖች ማለትም ፦ - ሰሜን ወሎ - ደቡብ ወሎ - ከፊል ደቡብ ጎንደር - ዋግኽምራ ውስጥ የሚኖሩ እና ተፈናቅለው ያሉትን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል…
"... እስከ ትናንት ድረስ በጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው ወደ ሰሜን ሸዋ ዞን 218 ሺህ 955 ዜጎች መጥተዋል " - አቶ አበባው መሰለ

ከ1 ሳምንት በፊት ከዋግህምራ እና ሰሜን ወሎ በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በደሴ እና አካባቢዋ ተጠልለው የነበሩ ዜጎች ጦርነቱን ሸሽተው በድጋሚ ወደ ሰሜን ሸዋ ዞን መፈናቀላቸው ተሰምቷል።

የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኀላፊ አቶ አበባው መሰለ ለአል ዐይን የዜና ማሰራጫ በሰጡት ቃል ፤ እስከ ትናንት ድረስ በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው 218 ሺህ 955 ዜጎች ወደ ሰሜን ሸዋ ዞን መምጣታቸውን ተናግረዋል።

ወደ ዞኑ የገቡ ተፈናቃዮችን ሰብዓዊ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆናቸውን የገለፁት አቶ አበባው ፤ 12 ጊዜያዊ መጠለያዎችን በማዘጋጀት ለተፈናቃዮች ድጋፍ በመደረግ ላይ መሆኑን አሳውቀዋል።

በተፈናቃዮች ስምም ሌሎች አካላት ሰርገው እንዳይገቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እየተደረገ መሆኑና አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲከሰቱ ከጸጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን አቶ አበባው ተናግረዋል።

በጦርነቱ የሚፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የተናገሩት ኃላፊው የክልሉ መንግስትና የፌደራል መንግስት ተጨማሪ ድጋፎችን እንዲያደርጉላቸው መጠየቃቸውን አል ዓይን ዘግቧል።

ህወሓት አማራ ክልል ላይ በከፈተው ጦርነት ከ991 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ቡድኑ በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ደግሞ ከ5 ሚሊዮን ህዝብ በላይ አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልገው እነዚህ ነዋሪዎች ለምግብ እጦት ፣ የመጠጥ ውሃ እና የመድሃኒት እጦት ችግር መጋለጣቸው ከቀናት በፊት የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስታና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ማሳወቁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#EMMPA

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር ከሰሞኑ የተወሰኑ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች፦
- የተዛቡ፣
- ትክክለኛ የጋዜጠኝነት መርህን ያልተከተሉ፣
- የአገር ሉዓላዊነትና የህዝቦችን አንድነት አደጋ ውስጥ የሚጥሉ ብሎም የፖለቲካዊ ውግንና ያላቸውን ዘገባዎች ማሰራጨታቸውን አጥብቆ ኮነነ።

ማህበሩ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ የሰሩትን ዘገባ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ መግለጫው ሰሞኑን አዲስ አበባን እና ዙሪያዋን በተመለከተ የተሰራጩ ዘገባዎችን ትክክለኛነትና ሚዛናዊነት ለማጣራት ጥረት ማድረጉን ገልጿል።

ለዘገባ ከተንቀሳቀሱና በየአካባቢው ከሚኖሩ አባሎቹ ብሎም ከነዋሪዎች ባገኘነው መረጃ መሰረት እስካሁን ድረስ አዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙት አካባቢዎች ሁሉ በተለመደው እንቅስቃሴያቸው ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ማህበሩ ከሰሞኑ ዓለምአቀፍ ሚዲያዎች የተዛቡ እና ፖለቲካዊ ውግንና ያላቸውን ዘገባዎች ማሰራጨታቸውን አጥብቆ የኮነነ ሲሆን በእንደዚህ ያሉ ሙያዊ መርሆን ባልተከተሉ ዘገባዎች እየተሳተፉ ያሉ ጋዜጠኞች ጋዜጠኝነታቸውን በሙያዊ አስተምህሮው መሰረት እንዲፈፅሙ ጠይቋል።

በተጨማሪ መቀመጫቸውን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ዓለም ያደረጉና ስለኢትዮጵያ የሚዘግቡ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ባለሙያዎች ከእንደዚህ አይነት አዘጋገብ እንዲወጡ አጥብቆ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ መንግስትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም የየትኛውም መገናኛ ብዙኃን ዘጋቢዎች ተገቢውን መረጃ እንዲያገኙና በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውረው እውነተኛ መረጃ ለህዝብ ማቅረብ እንዲችሉ አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስቧል።

የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃንም ፈጣን፣ ወቅታዊ፣ ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን እንዲያቀርቡ መክሯል።

*ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 11 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 3,962 የላብራቶሪ ምርመራ 148 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 421 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በተለያዩ ከተሞች ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር በመዋል ላይ የሚገኙ ሰዎች ሁኔታና የአያያዝ ሂደት ያሳስበኛል አለ።

ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀበት ከጥቅምት 23/2014 ዓ/ም ጀምሮ ሰዎች ከስራ ቦታቸው፣ ከመኖሪያ ቤታቸው እና ከመንገድ ላይ ጭምር በቁጥጥር ስር ውለው በተለያዩ የከተማዋ ፖሊስ ጣቢያዎች ተይዘው እንደሚገኙ አረጋግጫለሁ ብሏል።

ምንም እንኳን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ "ከሽብር ቡድኖች ጋር ይተባበራሉ ተብለው ምክንያታዊ በሆነ መልኩ የተጠረጠሩ ሰዎችን" ይዞ የማቆየት ስልጣን ለህግ አስከባሪ አካላት ቢሰጥም ፣ኢሰመኮ አደረኩት ባለው ክትትል እንዳረጋገጠው እስሩ ማንነት/ብሄርን መሰረት ባደረገ መልኩ በሚመስል ሁኔታ መከናወኑን በአንዳንድ ፖሊስ ጣቢያዎች የቤተሰብ ጥየቃ፣ ልብስ እና ስንቅ ማቀበል መከልከሉ እና እስሩ ህፃናት ልጆች ያሏቸው እናቶች እና አረጋዊያንን ያካተተ መሆኑ በእጅጉ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

ኢሰመኮ የህግ አስከባሪ አካላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁንና መመሪያዎቹን በስራ ላይ ሲያውሉ እና ሲያሰፈፅሙ የህጋዊነት ፣ የጥብቅ አስፈላጊነትና ተመጣጣኝ እንዲሁም ከመድልዎ ነፃ መሆን የሚሉትን የሰብዓዊ መብት መርሆዎችን ባከበረ መልኩ ሊሆን ይገባል ብሏል።

የህግ አስከባሪ አካላት በማንኛውም ሁኔታ ሊገደቡ የማይችሉ ሰብዓዊ መብቶችን የማክበርና የማስከበር፣ ተግባራቶቻቸውም በከፍተኛ የሙያ ስነምግባር በመመራት የማከናወን ኃላፊነት አለባቸውም ሲል ገልጿል።

በተለይ አረጋውያን፣ የህፃናት ልጆች እናቶች እንዲሁም የህክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎችን ጨምሮ ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን አያያዝ በተመለከተ ፈጣንና ልዩ የማጣራት አሰራር መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ፈተና መሰጠት ተጀመረ።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከዛሬ ጥቅምት 29 ጀምሮ መሰጠት ተጀምሯል።

ፈተናው ኅዳር 02/2014 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

በዛሬ ጥዋት የፈተና መርሃ ግብር መሰረት የእንግሊዘኛ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል።

በጸጥታ ችግር ምክንያት በመጀመሪያው ዙር ፈተናው በማይሰጥባቸው አካባቢዎች ፈተናው በሁለተኛ ዙር ለመስጠት እቅድ ተይዟል።

በ131 የፈተና ጣቢያዎች በጠቅላላው 36 ሺህ 340 ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተናው በመጀመሪያ ዙር አይቀመጡም።

ዛሬ ለሀገር አቀፍ ፈተና የተቀመጡ ተማሪዎች በሙሉ መልካም ፈተና እንዲሆን እየተመኘን ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ከፈተናው ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እንድትጠነቀቁ አደራ እንላለን።

ለሚመለከተው አካል ፦ ፈተናው ገና ከመጀመሩ ከፈተና ክፍል ውስጥ የተነሱ የፈተናውን ጥያቄ የያዙ ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ ደግሞ ቴሌግራም ላይ እየተዘዋወረ መሆኑን መመልከት ችለናል።

ይህ ትውልድ ገዳይ አገደኛ ድርጊት ፌስቡክ ላይም እየተፈፀመ ነው፤ ድርጊቱ ለዓመታት የለፉ ተማሪዎች ድካም ከንቱ የሚያስቀር በመሆኑ እጅግ አስቸኳይ መፍትሄ ይሰጠው (ሶሻል ሚዲያውን መዝጋት)

ለአክቲቪስቶች እና ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ፦ ተማሪዎች የዓመታት ድካማቸው ከንቱ እንዲሆን ለማድረግ ፎቶዎችን እየለጠፋችሁ የምትገኙ አካላት በተለይ አክቲቪስት ነን ምትሉ ምንም የማያውቁ ተማሪዎችን ህይወት ከፖለቲካ ጋር በማገናኘት የግል አላማን ለማሳካት ሚደረግ ተግባር ፍፁም ስነምግባር የጎደለ ተግባር መሆኑን በመረዳት ከድርጊታችሁ ልትቆጠቡ ይገባል።

የፖለቲካ ጉዳይን ከተማሪዎች ህይወት ጋር በማገናኘት ትውልድ አትግደሉ።

አጠቃላይ የማህበራዊ ሚዲያ ጉዳይ እጅግ አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልጋል።

#ቲክቫህ

@tikvahethiopia
የሸካ ዞን መቀመጫ ቴፒ እንዲሆን ተወሰነ።

ጥቅምት 27/2014 ዓ.ም የሸካ ዞን ም/ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የዞኑ ዋና መቀመጫ #ቴፒ_ከተማ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ ወሰኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ ቅዳሜ ባካሄደው 9ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ ዙር 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የአሠራር ቅልጥፍናና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የዞኑን ዋና ከተማ ከነበረበት ማሻ ከተማ ወደ ቴፒ ከተማ ለማዛወር የቀረበውን የውሣኔ አጀንዳ በመወያየት የዞኑ ዋና ከተማ ቴፒ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

ውሳኔው በተሻሻለው የደ/ብ/ብ/ህ/ክልል መንግስት ህገ መንግስት አንቀፅ 81 ንኡስ አንቀፅ 2 ላይ የዞን ምክር ቤቶች በዞኑ ውስጥ የበላይ የፖለቲካ ስልጣን ባለቤቶች ናቸው ተብሎ በተገለፀው መሠረት በጉዳዩ ላይ በመወያየት ካለው ህዝባዊ ጠቀሜታ እና ፋይዳ አንጻር የዞኑ ማዕከል አሁን ካለበት ማሻ ከተማ ወደ ቴፒ ከተማ እንዲዛወር በሙሉ ድምፅ ውሳኔ መተላለፉ ተገልጿል።

መረጃው የደረሰን ከሸካ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia