TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ሆነው የተሾሙት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዓሊ በዓለ ሲመታቸው በመስቀል አደባባይ የሚካሄድ ሲሆን ለዚሁ ስነስርዓት በርካታ ነዋሪዎች ወደ መስቀል አደባባይ እያቀኑ መሆኑን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት አሳውቋል። @tikvahethiopia
#Update

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በዓለ ሲመት በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው።

በዓለ ሲመቱ እጅግ ከፍተኛ የሰው ቁጥር በተገኘበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በበዓለ ሲመቱ ላይ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች ፣ ወጣቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።

የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ፣ የተለያዩ ሀገራት ተወካዮችም የበዓለ ሰመቱ ታዳሚዎች ናቸው።

@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) የሚወጡት መልዕክቶች ?

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኩል የወጡት ፅሁፎች መነጋገሪያ እየሆኑ ነው።

ከፅሁፎቹ መካከል አንደኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ ተብሎ የወጣው ነው።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ምንም እንኳን ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ንግግር ያላደረጉ ቢሆንም ኢብኮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያደረጉት ንግግር ብሎ አንድ ፅሁፍ አሰራጭቷል።

በተጨማሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በዝግ መምከሩን የሚገልፅ ሌላ ፅሁፍም አውጥቷል። ምክር ቤቱ ምንም አይነት ዝግ ስብሰባ አላደረገም ነበር።

ድርጅቱ እስካሁን ስለተፈጠረው ጉዳይ በግልፅ ማብራሪያ አልሰጠም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ንግግር አድርገዋል። ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የ "እንኳን ደስ አልዎት!" መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን መሪዎቹ በንግግሮቻቸው ያነሷቸውን ጉዳዮች በዚህ ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-10-04 @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ "አካታች ብሔራዊ ውይይት" እንደሚካሄድ ገለፁ።

ይህን የገለፁት በበዓለ ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ባሰሙት ንግግር ነው።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ ብሔራዊ ውይይቱ "ችግሮቻችንን በጠረጴዛ ዙሪያ ይፈታሉ ብለው የሚያምኑትን" የሚያካትት እና በኢትዮጵያውያን የሚመራ እንደሚሆን ጥቆማ ሰጥተዋል።

በትግራይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተዛመተው እና "በክህደት እና በእብሪት የተጠነሰሰ" ያሉት ግጭት "እንደ ሀገር እጅግ ከባድ ዋጋ" ማስከፈሉንም ተናግረዋል።

" ጠላት ብረት አንስቶ እንደ ብሌናችን የምናየውን የሰሜን እዝ አጠቃ፤ የጥሞና ጊዜ እንስጥ ባልንብት ጊዜም ህጻናትን እያስታጠቀ በርካታ ዜጎቻችንን አጠቃ፤ ንብረትም አወደመ" ሲሉም ተደምጠዋል።

“እኛ ኢትዮጵያውያን ሰልፍ ይዘን ስንዘምትም ሆነ ሰይፍ ይዘን ስነነሳ ጠባችን ኢትዮጵያ ጠል ከሆኑት ጋር ብቻ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፤ ኢትዮጵያ የተማሏ አቅም እና አቋም ያለው የፀጥታ ሀይል ታደራጃለች” ሲሉም ተናግረዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ "በመጪው ዘመን ብዝኃነታችንን በጌጥነት ተቀብለን መታረቅ የሚችል ሐሳባችንን አስታርቀን መከበር የሚገባው ልዩነቶቻችችን አክብረን ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጠንክረን ወደ ከፍታ የምንተምበት ጊዜ ይሆናል" ያሉ ሲሆን "ይኸም እንዲሳካ የፖለቲካ ልዩነቶቻችንን ለማጥበብ አካታች ብሔራዊ የውይይት መድረክ እናካሂዳለን" ብለዋል።

መረጃው ከዶቼቨለ እና አል ዓይን የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia
#Update

የUAE መሪዎች ዛሬ በድጋሚ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ለተሾሙት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደስታ መግለጫ ልከዋል።

የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት የላኩት የUAE ፕሬዝደንት ሼክ ክሃሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን፣ የዩኤኢ ምክትል ፕሬዝደንት፤ ጠቅላይ ሚኒስትርና የዱባይ ገዥ ሼክ ሞሃመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱም እንዲሁም የአቡዳቢ ዘውዳዊ ልዑል እና የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠቅላይ አዛዥ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ናቸው።

መሪዎቹ፤ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በድጋሚ ስለተመረጡ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል የኤርትራው ፕሬዝዳንት፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የደስታ መግለጫ ልከዋል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ፤ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ በመፈጸማቸው በራሳቸው እና በሚመሩት ሕዝብ ስም መደሰታቸውን ገልጸዋል።

አዲስ አበባ እና አስመራ ባለፉት ሶስት ዓመታት ከግጭት እና ከፍጥጫ በመውጣት ሰላምና ወዳጅነትን መመስረታቸው ለአፍሪካ ቀንድ አወንታዊ ማመላከቻ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።

Credit : አል ዓይን

@tikvahethiopia
#Facebook

ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም መተግበሪያዎች መስራት አቁመዋል።

በፌስቡክ ስር የሚገኙት እኚህ መተግበሪያዎች በተለያዩ የዓለም ሀገራት ሙሉ ለሙሉ መስራት አቁመዋል።

እዚሁ ሀገራችን ላይም ከ25 ደቂቃዎች በፊት አገልግሎታቸው ተቋርጧል።

እስካሁን መተግበሪያዎቹ መስራት ያቆሙበት ምክንያት አልታወቀም።

@tikvahethiopia
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ለዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ለሚመሰርቱት መንግስታቸው ፣ ለህዝብ ተ/ም/ቤት እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አዳዲስ አመራሮች በተጨማሪ በቅርቡ ለተቋቋሙ አዳዲስ የክልል መንግስታት አመራሮች መልካም የስራ ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገለፀ።

አዳዲሶቹ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት በእውነተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት መላው የሀገሪቱን ህዝብ በቅንነት እና ታማኝነት እንዲያገለግሉም ጥሪ አቅርቧል።

በከፍተኛ የሰላም እጦት ፣ ማህበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊና ዲፕሎማሲያዊ ጫና ውስጥ ለምትገኘው ኢትዮጵያ ከአዲሱ መንግስት በርካታ አፋጣኝ ውሳኔዎችን ትጠብቃለችም ብሏል ነእፓ።

ፓርቲው ፦

- በጦርነት፣ በግጭት እና በፍትህ እጦት የሚንገላቱ በርካታ ዜጎች ከጠቅላይ ሚንስትሩ እና ከመንግስታቸው በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እውን እንዲሆን ፈጣን ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ ውሳኔዎች በጉጉት ይጠበቃሉ።

- በከፍተኛ ድህነት፣ የኑሮ ውድነት እና ስራ አጥነት አዙሪት ውስጥ ለሚሰቃዩ እልፍ አእላፍ ኢትዮጵያውያን ከአዲሶቹ የፌዴራልና የክልል መንግስታት ተጨባጭ የመፍትሄ እርምጃዎችን በታላቅ ተስፋ ይጠብቃሉ።

- በትግራይ፣ አማራ፣ አፋር እንዲሁም ሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች በግጭት እና በጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በሀገራችን ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ወደ ቀያቸው ተመልሰው የሰላም አየር የሚተነፍሱበት ሰዓት በጉጉት በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ፤ በመሆኑም እነዚህ እና ሌሎች በርካታ የሀገሪቱ ዘመን ተሻጋሪ ውስብስብ ችግሮች የአዲሱን መንግስት አፋጣኝ ውሳኔ ይሻሉ ብሏል።

ነእፓ፥ " ዶ/ር ዐቢይ እና መንግስታቸው የሀገሪቱን እና የህዝቡን ድርብርብ ችግሮች ለመቅረፍ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው እንመኛለን " ሲል መልዕክቱን አስተላልፋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Facebook ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም መተግበሪያዎች መስራት አቁመዋል። በፌስቡክ ስር የሚገኙት እኚህ መተግበሪያዎች በተለያዩ የዓለም ሀገራት ሙሉ ለሙሉ መስራት አቁመዋል። እዚሁ ሀገራችን ላይም ከ25 ደቂቃዎች በፊት አገልግሎታቸው ተቋርጧል። እስካሁን መተግበሪያዎቹ መስራት ያቆሙበት ምክንያት አልታወቀም። @tikvahethiopia
#Facebook

ፌስቡክ ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር በአሁኑ ወቅት በበርካታ አገሮች ውስጥ አገልግሎታቸው መቋረጡን ኔትብሎክስ አሳውቋል።

ክስተቱ በአገር ደረጃ ካለ የኢንተርኔት ግንኙነት ጋር ያልተገናኘ መሆኑንም ጠቁሟል።

እስካሁን በፌስቡክ በኩል ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ የተገለፀ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
#Update

የተቋረጠው የፌስቡክ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር አገልግሎት ችግሩ በአገልግሎት ሰጪዎቹ በኩል እስኪስተካከል ድረስ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ኢትዮ ቴሌኮም መልእክት አስተላልፏል።

ፌስቡክ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባሰራጨው መልዕክት በተቻለ ፍጥነት ነገሮችን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል ፤ ለተፈጠረው ማንኛውም አይነት ችግርም ይቅርታ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የተቋረጠው የፌስቡክ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር አገልግሎት ችግሩ በአገልግሎት ሰጪዎቹ በኩል እስኪስተካከል ድረስ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ኢትዮ ቴሌኮም መልእክት አስተላልፏል። ፌስቡክ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባሰራጨው መልዕክት በተቻለ ፍጥነት ነገሮችን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል ፤ ለተፈጠረው ማንኛውም አይነት ችግርም ይቅርታ ጠይቋል። @tikvahethiopia
#Update

ከ6 ሰዓታት በላይ ተቋርጠው የቆዩት ፌስቡክ ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እንዲሁም ሜሴንጀር ወደ አገልግሎት ተመልሰዋል።

ፌስቡክ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ ከመጠየቅ ውጭ እስካሁን ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ ማብራሪያ አልሰጠም።

እንደብሉምበርግ ዘገባ ከሆነ በፌስቡክ መቋረጥ በ5 ሰዓታት ውስጥ ብቻ የማርክ ዙከርበርግ የግል ሃብት በ7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዝቅ ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የካቢኔ ሹመት ጉዳይ ? ዛሬ በፕሮግራም መደራረብ ምክንያት የካቢኔ ሹመት አልፀደቀም። የካቢኔ ሹሙቱ ነገ ወይም በቀጣይ ቀናት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። @tikvahethiopia
#Update

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ የካቢኔ ሹመት ያፀድቃል።

ምክር ቤቱ ዛሬ ከሰዓት በሚኖረው መርሃ ግብር መሰረት የመንግስት የካቢኔ ሹመትን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia