TIKVAH-ETHIOPIA
#Facebook ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም መተግበሪያዎች መስራት አቁመዋል። በፌስቡክ ስር የሚገኙት እኚህ መተግበሪያዎች በተለያዩ የዓለም ሀገራት ሙሉ ለሙሉ መስራት አቁመዋል። እዚሁ ሀገራችን ላይም ከ25 ደቂቃዎች በፊት አገልግሎታቸው ተቋርጧል። እስካሁን መተግበሪያዎቹ መስራት ያቆሙበት ምክንያት አልታወቀም። @tikvahethiopia
#Facebook

ፌስቡክ ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር በአሁኑ ወቅት በበርካታ አገሮች ውስጥ አገልግሎታቸው መቋረጡን ኔትብሎክስ አሳውቋል።

ክስተቱ በአገር ደረጃ ካለ የኢንተርኔት ግንኙነት ጋር ያልተገናኘ መሆኑንም ጠቁሟል።

እስካሁን በፌስቡክ በኩል ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ የተገለፀ ነገር የለም።

@tikvahethiopia