TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ንግግር አድርገዋል። ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የ "እንኳን ደስ አልዎት!" መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን መሪዎቹ በንግግሮቻቸው ያነሷቸውን ጉዳዮች በዚህ ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-10-04 @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ "አካታች ብሔራዊ ውይይት" እንደሚካሄድ ገለፁ።

ይህን የገለፁት በበዓለ ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ባሰሙት ንግግር ነው።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ ብሔራዊ ውይይቱ "ችግሮቻችንን በጠረጴዛ ዙሪያ ይፈታሉ ብለው የሚያምኑትን" የሚያካትት እና በኢትዮጵያውያን የሚመራ እንደሚሆን ጥቆማ ሰጥተዋል።

በትግራይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተዛመተው እና "በክህደት እና በእብሪት የተጠነሰሰ" ያሉት ግጭት "እንደ ሀገር እጅግ ከባድ ዋጋ" ማስከፈሉንም ተናግረዋል።

" ጠላት ብረት አንስቶ እንደ ብሌናችን የምናየውን የሰሜን እዝ አጠቃ፤ የጥሞና ጊዜ እንስጥ ባልንብት ጊዜም ህጻናትን እያስታጠቀ በርካታ ዜጎቻችንን አጠቃ፤ ንብረትም አወደመ" ሲሉም ተደምጠዋል።

“እኛ ኢትዮጵያውያን ሰልፍ ይዘን ስንዘምትም ሆነ ሰይፍ ይዘን ስነነሳ ጠባችን ኢትዮጵያ ጠል ከሆኑት ጋር ብቻ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፤ ኢትዮጵያ የተማሏ አቅም እና አቋም ያለው የፀጥታ ሀይል ታደራጃለች” ሲሉም ተናግረዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ "በመጪው ዘመን ብዝኃነታችንን በጌጥነት ተቀብለን መታረቅ የሚችል ሐሳባችንን አስታርቀን መከበር የሚገባው ልዩነቶቻችችን አክብረን ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጠንክረን ወደ ከፍታ የምንተምበት ጊዜ ይሆናል" ያሉ ሲሆን "ይኸም እንዲሳካ የፖለቲካ ልዩነቶቻችንን ለማጥበብ አካታች ብሔራዊ የውይይት መድረክ እናካሂዳለን" ብለዋል።

መረጃው ከዶቼቨለ እና አል ዓይን የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia