TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ... በድርጊቱ የተሳተፉ 2 የፓሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል" - ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

በአንድ ቪድዮ ላይ አንዲት ሴትን ሲደበድቡ የነበሩ ሁለት የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አስታውቀዋል።

"በርካታ ዜጎቻችን ልብ የሚሰብር የቪዲዮ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ሲቀባበሉ ተመልክተናል" ያሉት ሚኒስትሯ ፥ " የጀመርነው ተቋማዊ ለውጥ ሀላፊነትን ከነተጠያቂነቱ አጣምሮ የያዘ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ከፌዴራል ፓሊስ አመራሮች ጋር መረጃ ተለዋዉጠናል" ብለዋል።

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ፥ በድርጊቱ የተሳተፉ ሁለት የፓሊስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀው ህጉን ተከትሎ የማጣራትና ተገቢው የእርምት እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል።

ሚኒስትሯ ዜጎች ለሰብዓዊ መብት መከበር እንዲህ አይነት ህገወጥ ተግባራትን በመከታተልና በማጋለጥ ረገድ ማህበራዊ ሚዲያን አዎንታዊ ለሆነ ተግባር ማዋል መቻላቸው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... በድርጊቱ የተሳተፉ 2 የፓሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል" - ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በአንድ ቪድዮ ላይ አንዲት ሴትን ሲደበድቡ የነበሩ ሁለት የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አስታውቀዋል። "በርካታ ዜጎቻችን ልብ የሚሰብር የቪዲዮ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ሲቀባበሉ ተመልክተናል" ያሉት ሚኒስትሯ ፥ " የጀመርነው ተቋማዊ ለውጥ ሀላፊነትን ከነተጠያቂነቱ…
#Update

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፥ ከፖሊስ የሙያ ስነ-ምግባር ውጪ በአንዲት ግለሰብ ላይ ድብደባ የፈፀሙ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዉለዉ ምርመራ እየተጠራባቸው መሆኑን አስታውቋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ሚካኤል አደባባይ አካባቢ መስከረም 21 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ም/ኢ/ር ጃፋር አሊ እና ኮንስታብል መስፍን በተለ የተባሉ የቆሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አባላት አንዲትን ግለሰብ በአስነዋሪ ሁኔታ በመደብደባቸው በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጠራ እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።

"ህዝብን በሰብአዊነት ማገልገል የአዲስ አበባ ፖሊስ መርህ መሆኑ እየታወቀ ነገር ግን አንዳንድ አመራሮችና አባላት ይህን መርህ በመተላለፍ የሚፈፅሙት ህገ-ወጥ ድርጊት ተቋሙ አይታገስም" ያለው ፖሊስ በ2013 የበጀት ዓመት በልዩ ልዩ ጥፋት ላይ የተገኙ 171 የፖሊስ አመራሮችና አባላት ከሰራዊቱ እንዲሰናበቱ መደረጉን ገልጿል።

ከስራ ከተሰናበቱት 29ኙ ከሰብአዊ መብት ጥስት ጋር በተያያዘ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

ፖሊስ ህግን በመተላለፍ ጥፋት በሚፈፁም አባላትና አመራሮች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቆ ህብረተሰቡ እንዲህ ዓይነት ከፓሊስ የሙያ ስነ-ምግባር ውጪ የሆኑ ድርጊቶች በሚፈፀሙበት ወቅት በፍጥነት ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

ግለሰቧን በደበደቡ የፖሊስ አባላት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ ተወስዶ ውጤቱን ለህዝብ አሳውቃለሁ ብሏል አዲስ አበባ ፖሊስ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በሰላም ተጠናቋል።

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ የተከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሰላም መጠናቀቁን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች በመግለጫቸው በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን አሳውቀዋል።

የዘንድሮው በዓል ከሶስት ሚሊዮን በላይ ተሳታፊ እንደተገኘ የገለፁም ሲሆን በዓሉ በሰላም እንዲከበር ላደረጉ የፀጥታ ኃይሎች እና የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፥ ከፖሊስ የሙያ ስነ-ምግባር ውጪ በአንዲት ግለሰብ ላይ ድብደባ የፈፀሙ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዉለዉ ምርመራ እየተጠራባቸው መሆኑን አስታውቋል። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ሚካኤል አደባባይ አካባቢ መስከረም 21 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ም/ኢ/ር ጃፋር አሊ እና ኮንስታብል መስፍን በተለ የተባሉ የቆሬ አካባቢ…
" ድርጊቱ አስደንግጦናል፤ ረብሾናል " - ኢሰመኮ

በሁለት ፖሊስ አባላት ድብደባ ሲፈፀምባት የነበረችው እናት በልመና የምትተዳደር ሲሆን አጠገቧ የነበረችውም ልጇ ናት።

ድርጊቱ "ጀሞ ሚካኤል መብራት" አካባቢ የተፈፀመ መሆኑን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በድርጊቱ ክፉኛ መደንገጡን እና መረበሹን አሳውቋል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ለሸገር ኤፍ ኤም በሰጡት ቃል ፥ "የተመለከትነው ቪድዮ በጣም የሚረብሽና የሚያስደነግጥ ነው" ያሉ ሲሆን ኮሚሽኑ የተሟላ መረጃ ለማግኘት እየሰራ መሆኑን እና ክትትሉም እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

አ/አ ፖሊስ እንዳሳወቀው ሁለቱ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#update አቶ ርስቱ ይርዳው የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ። የደቡብ ክልል ምክር ቤት አቶ ርስቱ ይርዳውን የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳደር አድርጎ የሾመ ሲሆን አቶ ርስቱ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። @tikvahethiopia
#Update

የደቡብ ክልል ምክር ቤት አዲስ መንግስት ምስረታ ጉባኤ የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትን በመምረጥ ተጠናቋል።

በሌላ በኩል ምክር ቤቱ በክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ርስቱ ይርዳው የቀረቡ የካቢኔ አባላትን ሹመት ያፀደቀ ሲሆን ከካቢኔ አባላቱ መካከል 3ቱ ከተፎካካሪ ፓርቲ ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ የክልሉ ም/ቤት 25 የቢሮ አደረጃጀቶችን ያፀደቀ ሲሆን ራሱን ችሎ መዋቅር የነበረው የእንስሳት እና አሳ ሃብት ቢሮ ከነመሉ ተግባሩ ወደ ግብርና ቢሮ ተካቷል።

* ከላይ የተያያዘው ሹመታቸው በክልል ም/ቤት የፀደቀላቸው የካቢኔ አባላት ሙሉ ስም ዝርዝር እና የ25ቱ የቢሮ አደረጃጀቶች ዝርዝር ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ድርጊቱ አስደንግጦናል፤ ረብሾናል " - ኢሰመኮ በሁለት ፖሊስ አባላት ድብደባ ሲፈፀምባት የነበረችው እናት በልመና የምትተዳደር ሲሆን አጠገቧ የነበረችውም ልጇ ናት። ድርጊቱ "ጀሞ ሚካኤል መብራት" አካባቢ የተፈፀመ መሆኑን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በድርጊቱ ክፉኛ መደንገጡን እና መረበሹን አሳውቋል። የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር…
" ሁለቱ የፖሊስ አባላት ሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ " - ጠቅላይ ዐቃቤ

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የተገለፀው የልጅ እናቷን ሴት የደበደቡት እና ያንገላቱት ሁለቱ የፖሊስ አባላት #ሰኞ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ አሳውቋል።

ፅህፈት ቤቱ ከክፍለ ከተማው ፖሊስ ጋር በመሆን ምርመራው በአስቸኳይ በማጠናቀቅ ሰኞ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ኢትዮጵያ በ72 ሰዓታት ከሀገሪቱ እንዲወጡ ያዘዘቻቸውን 7 የተመድ ግለሰቦች ጉዳይ መነጋገሪያነቱ የቀጠለ ሲሆን አሜሪካ ውሳኔውን ተቃውማለች። ኢትዮጵያ የተመድ ሠራተኞችን ከአገር ለማስወጣት የወሰነችው፤ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ምክንያት እየሞቱ ነው የሚል የማስጠንቀቂያ ሪፖርት ከወጣ በኋላ ነው ብላለች አሜሪካ። በሌላ በኩል ፥ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ…
" ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ የመጣል ዕድሉ ዝቅተኛ ነው " - ዲፕሎማቶች

ኢትዮጵያ 🇪🇹 በህገወጥ ድርጊቶች ላይ ተሳትፈዋል ያለቻቸውን 7 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ሰራተኞችን በ72 ሰዓት ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟ ይታወቃል።

ተመድ የኢትዮጵያ መንግሥት ባልደረቦቼን ከሀገር የማባረር መብት የለውም ብሏል።

የድርጅቱ የሕግ ክፍል በተመድ ለኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ በፃፈው ማስታወሻ ፥ "መንግሥት ማድረግ የሚችለው፣ ለተመድ ቅሬታውን አቅርቦ በምትካቸው ሌሎች እንዲላኩለት መጠየቅ ብቻ ነው " ብሏል።

ግለሰቦቹ በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ስለግባታቸው ማስረጃ አልቀረበልኝም ሲል አክሏል።

ድርጅቱ ውሳኔውን ያልተቀበለው፣ የዲፕሎማቲክ ከለላ ያላቸውን ግለሰቦች ከሀገር የማባረር መብት በሀገራት ላይ እንጅ በተመድ ላይ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም በማለት ነው።

መንግሥት ለግለሰቦቹ የሰጠው የጊዜ ገደብ ዛሬ የሚያበቃ ሲሆን ሃላፊዎቹ በሀገሪቱ እንደሚቆዩ የተመድ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

ትላንት ለሊት የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት በትግራይ ጉዳይ እና የተመድ ሃላፊዎች ከኢትዮጵያ የመባረር ውሳኔ ላይ በዝግ መክሮ ነበር።

ቻይና እና ሩሲያ ጉዳዩን በዝርዝር ማጤን እንደሚያስፈልግ እና የትግራዩ ግጭት የውስጥ ጉዳይ መሆኑን በመግለጻቸው ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ የመጣል ዕድሉ ዝቅተኛ እንደሆነ ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።

Credit : www.wazemaradio.com
Source :
https://www.reuters.com/world/africa/un-decries-ethiopia-expulsions-says-52-million-need-aid-tigray-2021-10-01/ & Associated Press

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 45 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 45 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,004 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 888 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 776 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

ውድ ቤተሰቦቻችን በየዕለቱ በበሽታው ሳቢያ የሚሞተው የሰው ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ በመሆኑ ጥንቃቄያችሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ #እንድታጠናክሩ አደራ እንላለን።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Irreecha2014

ዛሬ በቢሾፍቱ የሆራ ሀርሰዲ ኢሬቻ በዓል በመከበር ላይ ይገኛል።

በዓሉ ባለፈው ዓመት ልክ እንደ ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ሁሉ በኮቪድ-19 ምክንያት በአነስተኛ የሰው ቁጥር የተከበረ ሲሆን የዛሬው በዓል ላይ ከፍተኛ የሰው ቁጥር ተገኝቷል።

የበዓሉ ተሳታፊዎች ከለሊት ጀምሮ በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ በማቅናት በዓሉን እየከበሩት ይገኛሉ። የበዓሉ ታዳሚዎች በባህላዊ ልብስ ተውበው ፥የተለያዩ ባህሉን የሚገልፁ ዜማዎችን በማዜም በዓሉን በድምቀት እያከበሩት ነው።

ኢሬቻ የሰላም፣ የእርቅ፣ የይቅርታ መገለጫ በዓል ነው።

Baga ayyaana Irreecha nagaan geessan !
እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Metekel በመተከል የፀጥታ ችግር 194 ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸው ፤ ከ194ቱ ውስጥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ፤ 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል መፍረሳቸው ተገለፀ። ይህ የተገለፀው ዛሬ በአሶሳ በጀመረው 23ኛው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቀፍ ትምህርት ጉባኤ ላይ ነው።፡ በዚሁ መድረክ ላይ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ቢንያም መንገሻ እንደተናገሩት ፤ በመተከል ግጭት…
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የወደሙትን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለማቋቋም 15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ ከተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ተቀናሽ በማድረግ የተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት በተካሄደው 23ኛው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የትምህርት ጉባኤ ላይ በመተከል የፀጥታ ችግር 194 ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸው ፤ ከ194ቱ ውስጥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ፤ 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል መፍረሳቸው በክልሉ ትምህርት ቢሮ ሪፖርት መደረጉ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል በሰላም ተጠናቋል።

የቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።

ቢሮው ፥ በዓሉ ከሁሉም የኦሮሚያ ዞኖች እና ከሌሎች ክልሎች እንዲሁም ከመላ አገሪቱ የመጡ ታዳሚዎች በተገኙበት ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፤ በሰላምም ተጠናቋል ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BaankiiRaammis ራሚስ ባንክ በቂ ሃብት በማሰባሰቡ ወደ ምስረታ ተሸጋገረ። በምስረታ ሂደት ሁለት አመታትን ያስቆጠረው ራሚስ ባንክ ብሄራዊ ባንክ ያስቀመጠውን ቀነ ገደብ ባገናዘበ መልኩ ወደ ምስረታ ሂደት መሸጋገሩን አስታወቀ። ባለፈው ሚያዝያ ብሄራዊ ባንክ ባስተላለፈው ትእዛዝ በምስረታ ላይ የሚገኙ ባንኮች 500 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል ይዘው እና የመስራች ጉባኤ አድርገው እስከ ጥቅምት…
#BaankiiRaammis

ትላንት መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም ራሚስ ባንክ የመስራች ጉባኤውን በኢሊሊ ሆቴል አካሂዷል።

በጉባኤው ላይ 13 የቦርድ አባላት ምርጫ የተካሄደ መሆኑ ታውቋል።

ብሄራዊ ባንክ 500 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል በማሟላት በምስረታ ላይ ያሉ ባንኮች ተገቢውን የመስራች ሂደት አልፈው በ6 ወር ውስጥ ማለትም እስክ ጥቅምት 2 ድረስ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ መግለፁ ይታወቃል።

ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚያቀርበው ራሚስ ከ700 ሚሊየን ብር በላይ የተከፈለ ካፒታል አለው።

በቀነ ገደቡ የማይመጡ አዳዲስ ባንኮች የመመስረቻ ካፒታል 5 ቢሊየን ይሆናል።

Credit : Capital Newspaper

@tikvahethiopia