TIKVAH-ETHIOPIA
" ድርጊቱ አስደንግጦናል፤ ረብሾናል " - ኢሰመኮ በሁለት ፖሊስ አባላት ድብደባ ሲፈፀምባት የነበረችው እናት በልመና የምትተዳደር ሲሆን አጠገቧ የነበረችውም ልጇ ናት። ድርጊቱ "ጀሞ ሚካኤል መብራት" አካባቢ የተፈፀመ መሆኑን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በድርጊቱ ክፉኛ መደንገጡን እና መረበሹን አሳውቋል። የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር…
" ሁለቱ የፖሊስ አባላት ሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ " - ጠቅላይ ዐቃቤ

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የተገለፀው የልጅ እናቷን ሴት የደበደቡት እና ያንገላቱት ሁለቱ የፖሊስ አባላት #ሰኞ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ አሳውቋል።

ፅህፈት ቤቱ ከክፍለ ከተማው ፖሊስ ጋር በመሆን ምርመራው በአስቸኳይ በማጠናቀቅ ሰኞ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ገልጿል።

@tikvahethiopia