TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Irreecha2014

ኢሬቻ መስከረም 22 እና መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ/ም ይከበራል።

የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ፥ የኦሮሞ ህዝብ የአንድነትና የሰላም ተምሳሌት የሆነውን የኢሬቻን በዓል ያለ ምንም እንከን ለማክበር ዝግጅት መደረጉን አስታውቋል።

ህብረቱ ይህን ያሳወቀው መስከረም 22 እና 23 ቀን 2014 ዓ.ም የሚከበረውን የዘንድሮውን ኢሬቻ በዓል በማስመልከት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

የአባገዳዎች ህብረት ምክር ቤት ሰብሳቢ አባገዳ ጂሎ ማኖ ፥ በኢሬቻ ውስጥ ፖለቲካ የለም፣ ሰላምና ምስጋና ነው ያሉ ሲሆን “ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ የአንድነትና የሰላም ተምሳሌት ነው፤ በዓሉን ያለምንም እንከን ለማክበር ተዘጋጅተናል ነው” ብለዋል።

ዕለቱ የኦሮሞ ህዝብ በአንድነት ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት በመሆኑ በዓሉ ያለምንም ችግር በሰላም እንዲከበር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም አስገንዝበዋል።

የህብረቱ ፀሐፊና የቱለማ አባገዳ ጎበና ሆላ ደግሞ ፤ “በዓሉ የኦሮሞ ህዝብ ባህልና ትውፊቱን፣ ማንነቱ፣ የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት መሆኑን የሚያሳይበት ነው” ያሉ ሲሆን የበዓሉ ታዳሚ ህዝብ በዓሉን ሲያከብር ከኮሮና ወረርሽኝ ራሱን በመጠበቅ መሆን ይገባዋል ብለዋል።

በዓሉ የፖለቲካ ትርፍ ይገኝበታል ብለው ለሚያስቡ ሃይሎች መጠቀሚያ እንዳያደርጉት የኦሮሞ ቄሮዎች፣ ቀሬዎችና ፎሌዎች በየደረጃው ከሚገኙ የፀጥታ ሃይሎች ጋር በትብብር መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
#Irreecha2014 : ነገ ቅዳሜ በመዲናችን አዲስ አበባ ለሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል አስፈላጊው ሁሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በዓሉ የሚከበርበት የሆራ ፊንፊኔን አካባቢውን የማስዋብ ፣ የማሳመር እና የማፅዳት ስራዎች ተሰርቷል።

ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎችም የበዓሉ ተካፋዮች በዓሉን ለመታደም ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል፤ አሁንም በመግባት ላይ ይገኛሉ።

Baga ayyaana Irreecha nagaan geessan !
እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

@tikvahethiopia
#Irreecha2014 : የበዓሉ ታዳሚያን ለፍተሻ ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

የኢሬቻ ሆራ ፊንፍኔ በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ለወንጀል መከላከል ተግባራቸው ልዩ ትኩረት በመስጠት አብዛኛውን የሰው ኃይላቸውን በወንጀል መከላል ስራ ላይ እንዳሰማሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

በተለይ በዓሉ ወደ የሚከበርበት ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተገንዘበው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

በሌላ በኩል ፥ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97፣ መጠቀም ይችላል ተብሏል።

Baga ayyaana Irreecha nagaan geessan !
እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Irreecha2014 : ነገ ቅዳሜ በመዲናችን አዲስ አበባ ለሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል አስፈላጊው ሁሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ለማወቅ ተችሏል። በዓሉ የሚከበርበት የሆራ ፊንፊኔን አካባቢውን የማስዋብ ፣ የማሳመር እና የማፅዳት ስራዎች ተሰርቷል። ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎችም የበዓሉ ተካፋዮች በዓሉን ለመታደም ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል፤ አሁንም በመግባት ላይ ይገኛሉ። Baga ayyaana…
#Irreecha2014

የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በአዲስ አበባ በመከበር ላይ ይገኛል።

በዓሉ ባለፈው ዓመት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቀዛቅዞ ፣ በውስን የሰው ቁጥር መከበሩ የሚታወስ ሲሆን በዘንድሮው በዓል ላይ ከፍተኛ የሰው ቁጥር ተገኝቷል።

ከትላንት ጀምሮ በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ዜጎች ወደ አዲስ አበባ ከተማ የገቡ ሲሆን በርካታ ወጣቶች ለሊቱን በመስቀል አደባባይ በጭፈራ፣ በደስታ አሳልፈዋል።

ትላንት ለሊቱን የተቃውሞ ድምፃቸውንም ያሰሙ ወጣቶችም ነበሩ ፥ ተቃውሞው በዋነኝነት በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ጃዋር፣ አቶ በቀለ፣ አቶ ሃምዛ ፣ አቶ አብዲ ሌሎችም የኦሮሞ ፖለቲከኞች ከእስር ይፈቱ የሚል ነበር።

ወጣቶቹ ለሰዓታት የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙም ተቃውሞ ሲያሰሙ ተደምጠዋል፤ ዛሬ ጥዋትም ተቃውሞ ያሰሙ ወጣቶች ነበሩ።

የዘንድሮው ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በድምቀት በፍፁም ሰላም እየተከበረ ሲሆን ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች የተውጣጡ ታዳሚያንም በበዓሉ ላይ ተካፋይ ሆነዋል።

ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ ስርዓቱን ጠብቆ እየተከበረ መሆኑን ታዳሚዎች እየገለፁ ይገኛሉ።

ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ምድር እና ሰማይን ለፈጠረው ፈጣሪው ዋቃ ምስጋናውን ለማድረስ የኢሬቻ በዓልን ያከብራል።

የኦሮሞ ሕዝብ ከዘመን ወደ ዘመን በሰላም ላሸጋገረው አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው።

ማኅበራዊ ደረጃ እና የእድሜ ልዩነት ሳይፈጠር የኦሮሞ ሕዝብ የኢሬቻ በዓልን ለዘመናት በጋራ ሲያከብር ቆይቷል።

የበዓሉን አከባበር የሚያሰዩ ፎቶዎች ከላይ ተያይዘዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Irreecha2014

ዛሬ በቢሾፍቱ የሆራ ሀርሰዲ ኢሬቻ በዓል በመከበር ላይ ይገኛል።

በዓሉ ባለፈው ዓመት ልክ እንደ ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ሁሉ በኮቪድ-19 ምክንያት በአነስተኛ የሰው ቁጥር የተከበረ ሲሆን የዛሬው በዓል ላይ ከፍተኛ የሰው ቁጥር ተገኝቷል።

የበዓሉ ተሳታፊዎች ከለሊት ጀምሮ በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ በማቅናት በዓሉን እየከበሩት ይገኛሉ። የበዓሉ ታዳሚዎች በባህላዊ ልብስ ተውበው ፥የተለያዩ ባህሉን የሚገልፁ ዜማዎችን በማዜም በዓሉን በድምቀት እያከበሩት ነው።

ኢሬቻ የሰላም፣ የእርቅ፣ የይቅርታ መገለጫ በዓል ነው።

Baga ayyaana Irreecha nagaan geessan !
እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

@tikvahethiopia