TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Live stream started
Live stream finished (29 minutes)
Audio
AudioLab
#ምርጫ2013

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማህበር ሥራ አስፈጻሚዎች በ #ምርጫ2013 የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ተሳትፎና የሚዲያዎች ሚና ላይ ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሰጡት ገለፃ።

- ጋዜጠኛ ሲሳይ ሳህሉ
- ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ
- ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ ፣ ትግራይ ክልል የተነሳው ግጭት እንሆ 8 ወር አስቆጥሯል። ግጭቱ የሺዎችን ህይወት እንደቀጠፈ፣ ሺዎችንም እንዳሰደደ ቤት ፣ በርካቶች አካል እንዳጎደለ፣ በርካታ ሴቶችን ለፆታዊ ጥቃት እንደዳረገ፣ በርካታ ህፃናትን በአካልም በስነልቦናም እንደጎዳ፣ እንደተመድ ሪፖርት መቶ ሺዎችን ለረሃብ እንዳጋለጠ ይታመናል። የፌዴራል መንግስቱ የትግራይ ሁሉንም ከተሞች በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኃላ በተለያዩ…
ፎቶ፦ በመቐለ አይደር ሆስፒታል ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 16/2013 ዓ/ም ጉዳት ስለደረሰባቸው የቶጎጋ ነዋሪዎች ቤተሰቦቻቸው መረጃ ሲጠባበቁ።

ዛሬ ጥዋት በተለዋወጥነው መረጃ ትላንት ከመቐለ ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ቶጎጋ በነበረ ጥቃት የሰዎች ህይወት አልፏል፣ የአካል ጉዳት ደርሷል (እስካሁን ትክክለኛ የተጎጂ ዜጎች ቁጥር አይታወቅም) ።

የአየር ድብደባ የተፈፀመው እና ሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰው በገበያ ቀን በተፈፀመ ጥቃት መሆኑን የአይን እማኞች ይገልፃሉ። ከጥቃቱ በኃላ አምቡላሶች ሌሎች ተሽከርካሪዎች ወደቦታው እንዳይሄዱ ተከልክለው እንደነበር ከአካባቢው የወጡት ሪፖርቶች ያመላክታሉ።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጌትነት "በገበያ ቦታ ላይ ፈጽሞ የአየር ጥቃት አልፈጸምንም። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ? ሠራዊቱ ኢላማውን በትክክል የመምታት አቅም አለው" ጥቃቱን ሀሰት ብለውታል።

ኮሎኔሉ ፥ "... የአየር ጥቃቶችን ፈጽመናል ነገር ግን በተመረጡ ውስን ኢላማዎች ላይ ያነጣጠሩ ናቸው። ስለዚህ በገበያ ስፍራ ላይ ጥቃት ተፈጽሟል የተባለው ሙሉ ለሙሉ ውሸት ነው" ሲሉ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ክሱን ውድቅ አድርገውታል።

(ከሰሞኑ በትግራይ ስላሉት ሁኔታዎች ሙሉ መረጃው ከላይ በReply ተያይዟል)

Photo Credit : AFP

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የ24 ሰዓት የኮቪድ ሪፖርት :

• የላብራቶሪ ምርመራ - 4,406
• ቫይረሱ የተገኘባቸው - 111
• ህይወታቸው ያለፈ - 2
• ከበሽታው ያገገሙ 825

አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 275,502 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 4,292 ህይወታቸው ሲያልፍ 256,787 ሰዎች አገግመዋል። ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,987,301 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የታገደው የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ቃለምልልስ ዛሬ ይሰራጫል ተብሏል። የ "ጥሞና ወቅት" ላይ እንዳይተላለፍ የተባለው የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ቃለ ምልልስ ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት ላይ ነው በተለያዩ ሚዲያዎች ይተላለፋል የተባለው። ቃለምልልሱ ዛሬ እንደሚተላለፍ የሰማነው ከጠ/ሚር ፅ/ቤት ይፋዊ ከሆነው…
የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ ፡

ከሱዳን ድንበር ጋር ያለው ችግር በንግግር እና ውይይት ይፈታል ብለው እንደሚያምኑ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናግሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ሲናገሩ የተደመጡት የምርጫ 2013 የጥሞና ወቅት መተላለፍ የለበትም ተብሎ የታደውና ዛሬ በተላለፈው ቃለምልልስ ላይ ነው።

ከኢትዮ - ሱዳን ድንበር ጋር በተያያዘ ስላውን ችግር ተጠይቀው ምላሽ የሰጡት ዶ/ር ዐቢይ ፥ ችግሩን በዴፕሎማቲክ መንገድ ማየት ቅድሚያ እንደሚሰጠው ፣ ችግሩን ለመፍታት ከውይይት እና ንግግር ውጭ ያለው መንገድ ለሱዳንም ለኢትዮጵያም የሚበጅ እንዳልሆነ ገልፀዋል።

የድንበርን ጉዳይ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ሞክረዋለች ሲሉ ያስታወሱት ዶ/ር ዐቢይ ፥ "በጦርነት አሸንፋ ወደፍርድ ቤት ከሄደች በኃላ የተፈጠረውን ውጤት የምናውቀው ነው ፤ አሁንም ሰው ገድለን ሰው ሞቶብን ፣ መሬት ከያዝን በኃላ ሄዶ ጉዳዩ በዓለም አቀፍ ህግጋቶች የሚታይ ከሆነ ቀድሞ ለውጊያ መሽቀዳደም ጠቃሚ ነው የሚል ሃሳብ የለንም" ብለዋል።

ችግሩን በሰከነ መንፈስ በውይይት፣ ንግግር ፣ በሰጥቶ መቀበል መርህ የሚፈታበትን መንገድ ማየት ይበጃል ከዚህ ውጭ ግን ያለው መንገድ ጉዳቱ ለኢትዮጵያም ለሱዳንም እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም ሲሉ ተናግረዋል።

ከሱዳን ጋር ያለው ችግር በንግግር፣ በውይይት፣ በህግ አግባብ ይፈታል ብለው እንደሚያምኑ የተናገሩት ዶ/ር ዐቢይ፥ "ነገር ግን ሁሉም መንገድ ፣ በሁሉም ሙከራ ዝግ ከሆኑ ፣ ሁሉም ትዕግስት የማይመልሳቸው ከሆነ ሱዳን ብቻ ሳይትሆን ማንም ሀገር ከህግ አግባብ ውጪ የኢትዮጵያን አንድ ስንዝር መሬት ወስዶ መቀመጥ አይችልም ፤ ይህንን ሱዳኖችም ያውቁታል እኛም እናውቀዋለን" ሲሉ ተደምጠዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Ethio-Sudan-06-23

@tikvahethiopia
#አስቸኳይ

የሳዑዲ አረቢያ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነና ዜጎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፎ ነበር።

የሳዑዲ ፀጥታ ኃይሎች በሰሩት ኦፕሬሽን ተይዘው በሹሜሲ የማቆያ ጣብያ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ የውሃ የምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች እጥረት እንዳጋጠማቸው ተሰምቷል።

በመሆኑም:-

1ኛ. ከ10 ቀን እስከ 3 ዓመት ዕድሜ ላላቸው ህፃናት የሚሆን ወተት

2ኛ. ከ1 ቁጥር እስከ 5 ቁጥር የሆኑ የህፃናት ዳይፐር/ሃፋዛ/

3ኛ. ለታዳጊ ህፃናት እና ለአዋቂዎች የሚሆኑ ደረቅ ምግቦች

4ኛ. ለሴቶች እና ለሕፃናት የሚሆኑ የመፀዳጃ ቁሳቁሶች በተለይ ዋይፕ እና ሞዴስ

5ኛ. የሚጠጣ ውሃ እጥረት ያጋጠመ በመሆኑ ዜጎቻችን ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል።

ዕርዳታ ማድረግ የምትፈልጉ ግለሰቦች/ አደረጃጀቶች በጄዳ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ (ኮሚዩኒቲ) የስራ ኃላፊነቱን ወስዶ እንቅስቃሴ የጀመረ በመሆኑ ዕርዳታችሁን በኮሚኒቲ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ማድረስ እንደሚቻል በጄዳ የሚገኘው ቆንስላ ፅ/ቤት ዛሬ ማምሻውን ገልጿል።

ይህ መልዕክት የደረሳችሁ ጅዳ አካባቢ የምትገኙ የቲክቫህ አባላት በመሉ የምትችሉትን ሁሉ ታደርጉ ዘንድ መልዕክት እናስተላልፋለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ...ጥቃቱ ምግበይ በተባለ ግለሰብ የሚመራ የወንበዴ ኃይል ላይ የተወሰደ እርምጃ ነው ፤ ሰላማዊ ሰው ላይ ጥቃት አልተፈፀምም" - ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ

ከትላንት በስቲያ ከመቐለ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ 25 ኪ.ሜ በምትገኝ እንደርታ ወረዳ ደብረናዝሬት ቀበሌ ተቶጋግ እዳጋ ሰሉስ በምትባል መንደር ለገበያ ተሰብስበው የነበሩ ሰዎች በነበሩበት ወቅት ተፈፅሟል የተባለውን የአየር ጥቃት መነጋገሪያነቱ ቀጥሏል።

ቶጎጋ እዳጋ ሰሉስ ላይ ተፈፅሟል በተባለው የአየር ድብደባ እስካሁን ቁጥራቸው ያልታወቀ ዜጎች ህይወት አልፏል፤ በርካቶችም ቁስለኛ ሆነዋል።

የአይን እማኞች ድብደባው ማክሰኞ ከቀኑ ስድስት ሰዓት አካባቢ ለገበያ ተሰብስቦ በነበረ ህዝብ ላይ ነው የተፈፀመው ብለዋል። በድብደባው በሰዎች ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በእንስሳት ላይ ጉዳት ደርሷል።

የአይን እማኞቹ በቅድሚያ የተመታው ገበያው እንደሆነ በኃላም በቤቶች ላይ እንደነበር አስረድተዋል።

ከቦታው ጉዳት ደርሶባቸው መቐለ አይደር ሆስፒታል የገቡት 5 ሰዎች ሲሆኑ ከእነሱ መካከል አንዷ የ2 ዓመት ከአራት ወር ህፃን ትገኛለች።

ህፃኗ ከፍተኛ የሆኑ ጉዳት የደረሰባት ሲሆን በአሁን ሰዓት መተንፈስ ስለማትችል የመተንፈሻ ቱቦ ተገጥሞላት ይገኛል። በሌላ በኩል የህፃኗ አባት ጉዳት ደርሶበት ወደ ህክምና እንዳይገባ በወታደሮች ተከልክሏል ተብሏል።

አንድ የአይን እማኝ ደግሞ አጠገቡ ሶስት ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል። አህዮች ጨምሮ ብዙ እንስሶችም ሞተዋል ብሏል ፤ በአካባቢው ታጣቂዎች እንደነበሩ ተጠይቆ ምንም ታጣቂ አላየሁም ብሏል።

ጉዳት የደረደባቸውን ሰዎች ለማምጣት የአምቡላንስ ሹፌሮች አምስት ጊዜ ተጉዘው አይቻልም ተብለው መመለሳቸውን ገልፀዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tgoga-Tigray-06-24

@tikvahethiopia
"..ህዝቡን እያሽበርኩ በዚህ እቀጥላለሁ የሚል ከሆነ ዳግም በተጠናከረ መልኩ የሀይል እርምጃ ይወሰድበታል" - ሀገር መከላከያ ሰራዊት

ከሰሞኑን ትግራይ ክልል የነበረው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለምርጫው ሰላማዊነት ሲባል ወደሌላ የአገሪቱ አካባቢዎች መንቀሳቀሱን ተከትሎ በሽብርተኝነት የተፈረጀው የህውሓት ሚሊሻዎች ከተደበቁበት በመውጣት ሰላማዊውን የትግራይ ህዝብ ሲያሸብሩ ነበር አለ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ በሰጠው መግለጫ።

የሰራዊቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮ/ል ጌትነት አዳነ ፥ ሀገራዊ ምርጫውን ተከትሎ ከውጭም ከውስጥም ስጋት ስለነበር ሰራዊቱ በመንግስት ትዕዛዝ መሰረት ከትግራይ ወደ ማዕከል፣ ምስራቅ፣ ምእራብና የደቡብ የሀገራችን ክፍል እንዲንቀሳቀስ ተደርጎ ነበር ብለዋል።

"ይህን ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ በየጢሻው ተደብቆ የነበረው የህወሓት ሚሊሻ ህዝቡን ሲያስገድድና ሰላማዊ እንቅስቃሴውን ሲያስተጓጉል ነበር" ሲሉ ተናግረዋል።

መከላከያ ሰራዊቱ በወሰደው እርምጃ ህዝብን ወደ ሰላማዊ ኑሮው መመለስ ተችሏል ሲሉም ተደምጠዋል።

ዳይሬክተሩ ፥ በክልሉ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን በፍጥነት በመስራት ገበሬው እንዲያርስ፣ ነጋዴው እንዲነግድ፣ ተማሪዎች እንዲማሩ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ ገልጸዋል።

ይህ መልሶ የማቋቋም ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተደረገ ባለበት ወቅት የህወሓት ሀይል ህዝቡ ተጠቃሚ እንዳይሆን ፋይዳ ቢሲ ትንኮሳዎችን ከተደበቀበት እየወጣ እየተነኮሰ ይገኛል ብለዋል።

በሽብርተኝነት የተፈረጀው ቡድን ህዝቡን እያሽበርኩኝ በዚህ እቀጥላለሁ የሚል ከሆነ ዳግም በተጠናከረ መልኩ የሀይል እርምጃ እንደሚወሰድበት አስጠንቅቀዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-06-24

#ኢፕድ
@tikvahethiopia
#Update

በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን በ2 ሳምንታት ሙሉ በሙሉ ወደ አገራቸው ለማስገባት የሚያስችል ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

ቃል አቀባዩ ፥ በሳውዲ የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ በሁለት ሳምንት ውስጥ ምላሽ ያገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

በሳዑዲ የሚገኙ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን እንግልትና ስቃይ ለማስቆም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተካተቱበት ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ሥራውን እንደጀመረ ገልፀዋል።

ግብረ ሀይሉ በቀጣይ 2 ሳምንት ውስጥ በ ሳዑዲ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ይመልሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopia
"...በምርጫው ዕለት በአገሪቱ ደም ለማፋሰስ የሚፈልጉ ኃይሎች ነበሩ ነገር ግን ሴራቸው ከሽፏል" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫውን #በሰላማዊ መንገድ በማከናወን በእለቱ ደም ለማፋሰስ ያቀዱ ኃይሎችን ሴራ አክሽፏል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።

ቃል አቀባዩ ይህን ያሉት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።

አምሳባሳደሩ በምርጫው ወቅት እና ከምርጫ በኋላ በአገሪቱ ደም እንዲፋሰስ የሚፈልጉ ኃይሎች እንደነበሩ አስታውሰዋል።

በምርጫው እለት የነበረውን ሂደት በርካታ አገር አቀፍ እና አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በስፋት ሽፋን የሰጡት መሆኑንም ገልጸዋል።

የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫው ታማኝና ሰላማዊ እንደነበር ማረጋገጡንም አክለው መናገራቸውን ኢዜአ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
CANAL+ ለልጆችዎ ካዘጋጃቸው ሁለት የአማረኛ ቻናሎች በተጨማሪ አምስት ከዓለም የተወጣጡ አዝናኝ እና አስተማሪ የልጆች ቻናሎችን ይዞ መምጣቱን ያውቁ ኖሯል?

ስለ ሰባቱ የCANAL+ የልጆች ቻናሎች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ሊንኩን በመጫን የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ! https://publielectoral.lat/canalplusbusiness
#PressBriefing

ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እለታዊ የሚዲያ ማብራሪያ ይሰጣል።

ቦርዱ ማብራሪያውን ከቀኑ 10:30 ከስካይላይት ሆቴል ነው የሚሰጠው።

ውድየቲክቫህ አባላት መግለጫውን ሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላት በስፍራው ይገኛሉ።

መግለጫውን በቀጥታ በ ቴሌግራም Voice Chat ማዳመጥ እንደምትችሉ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
ያሶን ጨምሮ 5 እስረኞች ከእስር ተፈተዋል።

በእስር ላይ ከነበሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (OLF) አመራር እና አባላት መካከል ያሶ ከበበውን ጨምሮ 5 እስረኞች ትላንት ተፈተዋል።

በእነ አቶ ያሶ መዝገብ ስር በተከሰሱት ስድስት ተከሳሾች ላይ የቀረበባቸው ማስረጃ እውነት መሆኑም ማረጋገጥ ባለመቻሉ ፍርድ ቤት ስድስቱም ተከሳሾች በነፃ እንዲሰናበቱ መወሰኑን የተከሳሽ ጠበቆች ለኦ ኤም ኤን ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎም በትንትናው ዕለት 6ቱም ተከሳሾች ከእስር ተለቀዋል።

ከመስከረም 2/2011 ዓ/ም ጀምሮ ማስረጃ ሳይቀርብባቸው በእስር ላይ እንደነበሩ ጠበቆቻቸው አስታውሰዋል።

@tikvahethiopia
አቶ ዳገቶ ኩምቤ ከእስር ተፈቱ።

ለ10 ወር ያህል በእሥር የቆዩት የቀድሞ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ከእስር መፈታታቸው ተሰምቷል።

ከእሳቸው በተጨማሪም ምክትላቸው የነበሩት አቶ ገበዜ ጎዳና ዛሬ ሰኔ 17 /2013 ዓ.ም ዎላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎታ በነፃ አሰናብቷቸዋል።

የቀድሞው የዎላይታ ዞን አመራሮች የተከሰሱት ስልጣናቸውን አላግባብ የመገልገል ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ነበር።

Video Credit : Woldetsaadiqa

@tikvahethiopia