TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ዮሃንስ ቧያለው ለምን ሹመቱን አልተቀበሉትም?

አቶ ዮሃንስ ቧያለው ለአማራ ቴሌቪዥን በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የተሰጣቸውን ሹመት የማይቀበሉበትን ምክንያት እንዲህ አስረድተዋል፦

"በአሁኑ ጊዜ እራሴን ሳዳምጠውና ስመረምረው በዛ ተቋም መስራት ቢኖርብኝ እንኳን አሁን ባለው ብራንድ መስራት ምችልበት ሁኔታ ስላልሆነ የቀረበውን ሹመት ለመቀበል ያስቸግረኛል። ስለሆነም የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ፣ የአማራን ህዝብ ትግል በተለያየ መልኩ አስተዋፅኦ በማድረግ የፓርቲያችን ጉዞም እንዲጠናከር በማድረግ በተለየ ቦታ ብመደብ፣ ወይም ይሄ የተለየ ብራንድ ቢሰጠው ላገለግል እችላለሁ እንጂ አሁን ባለው ስያሜና ብራንድ በዛ ተቋም ለማገልገል ዝግጁ አለመሆኔን ገልጫለሁ በተለይም ለቦርዱ ሰብሳቢ። ትላንት ከሰማሁኝ በኃላ ዛሬ ጥዋት ምደባውን እንደማልቀበል ሪፖርት አድርጊያለሁ።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#YohannesBuayalew

አቶ ዮሃንስ ቧያለው አማራ ክልል በስልጣን በቆዩባቸው ዓመታት ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ድጋፍ እንደነበራቸው ዛሬ ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

አሁንም ቢሆን ለአማራ ክልልም ሆነ ለመላ ኢትዮጵያውያን ሰላም፣ ነፃነትና ብልፅግና እንደሚሰሩ አብራርተዋል፡፡

አዲስ የተሸሙ የአማራ ክልል አመራሮች እውቀትና ልምድ ያላቸው ታታሪ አመራሮች በመሆናቸው ህዝቡ ድጋፉን እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#PHOTO : ዛሬ ከእስር የተፈቱት የቀድሞ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደኀንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሌተናል ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአቶ ንዋይ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፅሟል...

ለረዥም ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ያገለገሉት አቶ ንዋይ ገብረአብ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፅሟል። የቀብር ሰነ ስርዓታቸው ቤተሰቦቻቸው ፣ የቀድሞ የስራ ባልደረቦቻቸው ፣ አድናቂዎቻቸው በተገኙበት ነው በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የተፈፀመው።

ከ1970ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና በፕላን ኮሚሽን ውስጥም ለረዥም ዓመታት አገልግለዋል። አቶ ንዋይ ከኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪነታቸው ባለፈ የኢትዮጵያ የልማት ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል።

#FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#attention አሁንም በአንዳድን የማንቡክ አካባቢዎች የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ እየተገለፀልን ከቤተሰቦቻችን እየተገለፅልን ነው። በአካባቢው የተፈጠረውንና እየተፈጠረው ያለውን ዝርዝር ጉዳይ ከቤተሰቦቻችን ጠይቀን፤ ተጨማሪ መረጃዎችን አካተን እንድታነቡት እናደርጋለን። ለሁሉም ግን የሚመለከታችሁ አካላት [የፀጥታ ኃይሉ] የአካባቢውን ደህንነት እንድታስጠብቁ የቲክቫህ ማንቡክ ቤተሰቦች አሳስበዋል።…
የማንቡክ ከተማ ሰላም መደፍረስ...

[በሸገር ኤፍ ኤም 102.1]

- ለማንቡክ ከተማ ፀጥታ መደፍረስ መነሻው ከቀናት በፊት የተፈፀመን ግድያ ተከትሎ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ የተፈፀመ የበቀል ግድያ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

- የበቀል ጥቃት የተፈፀመባቸው ወገኖችም አፀፋውን ለመስጠት ትናንት ረፋድ ላይ መሳሪያ ታጥቀው ወደማንቡክ ከተማ መጥተው ነበር። በመከላከያ ኃይል ምክር ወደመጡበት ተመልሰው ነበር።

- እኚሁ ሰዎች አመሻሽ ላይ በከተማው ድርቻ ላይ በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል። በጥቃቱም በከተማው ዳርቻ ያሉ ቤቶች በእሳት ጋይተዋል። ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከጥቃት ፈፃሚዎቹ መካከል የተወሰኑ ሰዎች ተገድለዋል።

- የመተከል ዞን ምክትል አስተዳዳሪ የፀጥታ መደፍረስ ምክንያቱ እውነት እንደሆነ አረጋግጠዋል። ችግሩ መከሰቱንም አምነዋል። ምክትል አስተዳዳሪው የሰው ህይወት መጥፋትን በተመለከተ ማጣራት እየተደረገ ነው ብለዋል። የተወሰኑ የሳር ቤቶችም ተቃጥለዋል ሲሉ ገልፀዋል። መከላከያ ገብቶ ሁሉንም ነገር አረጋግቷል።

#ShegerFM #ማህሌትታደለ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀላባ ቁሊቶ ውይይት፦

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሀላባ ቁሊቶ ከሀላባ ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በውይይታቸውም የአስፋልት መንገዶች ሥራ፣ የውኃ አቅርቦት አገልግሎት፣ የሆስፒታል ግንባታ እንዲሁም ሌሎች የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ተነስተውላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

ከሚኒስትሮች የተውጣጣው የልዑካን ቡድን አባላት የሀላባ ዞንን ጥያቄዎች ለመመለስ እየተሠሩ ስላሉት ሥራዎች ገለጻ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የውይይቱ ተሳታፊዎች ያነሷቸው ቁልፍ ጉዳዮች ተገቢ መሆናቸውን አመላክተው፣ ኢትዮጵያ በብልጽግና ከፍ ስትል እነርሱም በአንድነት እና በፍቅር እንዲጸኑ አበረታተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JawarMohammed

አቶ ጃዋር መሃመድ 'ኬላ' በተሰኘ የአሃዱ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ቀርበው 'ብዙ ኃይል ፖለቲካው ላይ እየባከነ ነው፤ የኢኮኖሚው ጉዳይ ተረስቷል' በሚል እይታቸውን እንዲያጋሩ ተጠይቀው ነበር። የኦፌኮ /KFO/ አባል የሆኑት አቶ ጃዋር ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና ፀጥታ ፈፅሞ የማይነጣጠሉ ገዳዮች እንደሆኑ አስረግጠው ተናግረዋል። ቁጭ ተብሎ ፖለቲካውን ማስተካከል ከተቻለ የፀጥታው ሁኔታ ይስተካከላል፣ የፀጥታው ሁኔታ ሲስተካከልም ኢኮኖሚው ይስተካከላል ሲሉም ተደምጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JawarMohammed

አቶ ጃዋር መሃመድ ከተናገሩት፦

"... 100 ሰዎች አንሆንም ይሄን ሀገር ለማረጋጋትም ፣ ለማበላሸትም እድሉ ያለን፤ አቅሙም ያለን 100 ሰዎች አንሆንም። እነዚህ 100 ሰዎች ዝም ብለው ውሸት ውስጥ ገብተው በComputer Generate በሚደረግ ገነትን ምድር ላይ እናመጣለን የሚል የማይሰራ ነገር ከማውራት፣ ቁጭ ብለን ፖለቲካውን ካስተካከልን ፀጥታው ይስተካከላል፣ ፀጥታው ከተስተካከለ ኢኮኖሚው እየተስተካከለ ነው የሚሄደው። እሱ ላይ ነው ትኩረት ማድረግ ያለብን"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአሰላ ከተማ ነዋሪዎች ብልፅግና ፓርቲን በመደገፍ ዛሬ በአሰላ አረንጓዴ ስታዲዮም ሰልፍ በማካሔድ ላይ ይገኛሉ።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ ከአሰላ ከተማ ነዋሪዎች በተጨማሪ በአርሲ ዞን ከሚገኙ 25 ወረዳዎች የመጡ በርካታ የህብተተሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎች ሆነዋል ተብሏል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ድሬዳዋ ቤት ተዘግቶባቸው በቃጠሎ በሞቱ የጂቡቲ ዜጎች ጉዳይ ተይዘው የነበሩ ተጠርጣሪዎች ላይ ውሳኔ ተላለፈ።

ድርጊቱን ፈጽመዋል ተብለው የጥፋተኝነት ብይን በተላለፈባቸው ላይ ከ3 ዓመት እስከ 25 ዓመት የሚደርስ ውሳኔ ተወስኖባቸዋል።

#VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በቢሾፍቱ በሚገኘው የኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በዛሬው ዕለት 106 ለሚሆኑ ከፍተኛ መኮንኖች ሹመት እንደሚሰጥ ታውቋል።

በተጨማሪም በዛሬው ዕለት ላለፉት 6 ወራት በስልጠና ላይ የቆዩ የአየር ኃይል ወታደራዊ ፖሊስ አባላት ምረቃ እንደሚኖር ተገልጿል። የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ ሹመቱን እንደሚሰጡ ተጠቁሟል።

የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ በስፍራው ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ባለፉት 6 ወራት በተቋሙ ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሰራተኞችም ሽልማት ይበረከታል ነው የተባለው።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2012 ዓመት፣ በስድስት ወራት ውስጥ 7ነጥብ7 ቢሊዮን ብር ማትረፉን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል። ትርፉ ከባለፈው ዓመት 6 ወራት ጋር ሲነፃፀር ተመሳሳይ እንደሆነም ተገልጿል።

#AddisMaleda
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ዓለም አቀፍ መረጃ፦ - የሟቾች ቁጥር 2,765 ከፍ ብሏል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 81,017 ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,765 የደረሰ ሲሆን 81,017 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 30,188 ደርሰዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ዓለም አቀፍ መረጃ፦

- የሟቾች ቁጥር 2,807 ከፍ ብሏል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 82,220

ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,807 የደረሰ ሲሆን 82,220 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 32,914 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthioTelecom

ኢትዮ - ቴሌኮም [ethiotelecom] የብሮድባንድ ኢንተርኔት የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉን አሳውቋል። ማሻሻያውም ለመኖርያ ቤት 69 በመቶ ቅናሽ ፣ ለድርጅቶች 65 በመቶ፣ VPN ደግሞ 72 በመቶ ቅናሽ መደረጉ ተገልጿል።

ማሻሻያው በዋጋ ብቻ ሳይሆን በፍጥነትም ጭምር መሆኑ ተሰምቷል። የኢንተርኔት አገልግሎቱ ለመኖርያ ቤት የ 3 በመቶ ፍጥነት ፣ ለድርጅቶች 4 በመቶ ፍጥነት ይጨምራል።

PHOTO : #TikvahFamily [Andinet]

#ETHIOFM #ሔኖክአስራት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ22 ተማሪዎች ላይ እርምጃ ወሰደ!

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ መማር ማሰተማሩን ለማደናቀፍ በሞከሩ 22 ተማሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡ የዩኒርቨሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ረዳት ፕሮፌሰር አበራ ባይሳ እንደገለጹት በዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ትምህርት ዘመን መማር ማስተማር ሂደትን የማደናቀፍ ሙከራ ያደረጉ 21 ተማሪዎችን ጉዳይ ሲመረምር ቆይቷል፡፡

በምርመራው መሠረት ተማሪዎቹ ብጥብጥና ሁከት ለማስነሳት በማደሪያ ቦታ ስለታማ መሣሪያ፣ ዱላ እና ፌሮ ብረት ይዘው እንደተገኙ አመልክተዋል፡፡ "በዩኒቨርሲቲው መመገቢያ አዳራሽ ለግጭት የሚጋብዙ ድርጊቶችን ፈጽመዋል"ምብለዋል፡፡

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሰሞኑን በደረሰው ውሳኔ መሠረት በእነዚህ ተማሪዎች ላይ ከከባድ ማስጠንቀቂያ እስከ ሁለት ዓመት ከትምህርት ማገድ እርምጃ መውሰዱን አስታውቀዋል። እርምጃ ከተወሰደባቸው ተማሪዎች መካከል እስከ ሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች ይገኙበታል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AssosaUniversity

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አብሮት ሲማር በነበረ ተማሪ ላይ የመግደል ሙከራ ያደረገ አንድ ተማሪ በህግ አስከባሪዎች ተይዞ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዘዳንት ረዳት ፕሮፌሰር አበራ ባይሳ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የተማሪዎችን ጥያቄዎች አቅም በፈቀደ ምላሽ በመስጠት ችግሮች ሳይከሰቱ አስቀድሞ ለመፍታት ከተማሪዎች እና መምህራን ጋር ተከታታይ ውይይቶች እየተደረጉ መሆናቸውንም ምክትል ፕሬዘዳንቱ ጠቁመዋል፡፡

በተለይ የቅሬታ ምንጭ የሆኑ የምግብ፣ መኝታ እና ተያያዥ የተማሪዎችን አገልግሎት የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በየጊዜው ድንገተኛ ጉብኝት በማድረግ ለማስተካከል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራ መቀጠሉን ገልጸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም ያደረገው ቅናሽ...

ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ ከጥዋት 4:00 ጀምሮ ደንበኞቹ እና አጋሮቹ እየተሳተፉበት የሚገኝ ልዩ ዝግጅት እያካሄደ ይገኛል።

በዚህም ፕሮግራም ላይ የብሮድባንድ ኢንተርኔት ላይ የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉን አሳውቋል። በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ የቤተሰባች አባላት የተደረገውን ስለተደረገው የታሪፍ ቅናሽ መረጃ እንዲኖራችሁ ከላይ እንደምትመለከቱት በፎቶ እያጋሯችሁ ይገኛሉ።

#TikvahFamily [Andinet]

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia