TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Audio
#JawarMohammed #DW

የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ ጀዋር መሐመድ በቅርቡ በሚደረገው ምርጫ እንደ ፖለቲከኛ እንዴት እንደሚወዳደር እስካሁን እንዳልወሰነ አስታወቀ። አቶ ጀዋር ለዶቼ ቨለ በሰጠው ቃለ ምልልስ የራሱን ፓርቲ መስርቶ ወይም ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተጣምሮ መወዳደርን በተመለከተ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ከገዥ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያይቶ እንደሚወስን ተናግሯል። የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን ውህደትንም የፌደራል ስርዓቱን የሚሸረሽር ሲል ተችቷል።

@tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopia
Audio
#JawarMohammed #ETHIOPIA

አቶ ጀዋር #የአሜሪካን ዜግነታቸውን ለመመለስ በሂደት ላይ እንደሚገኙ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ አስታውቀዋል። የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ኃላፊነታቸውን እንደሚያስረክቡም ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JAWARMOHAMMED #OFC

[በዋዜማ ሬድዮ]

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ በቅርቡ ፓርቲውን የተቀላቀለው ጃዋር መሀመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ደብዳቤ እንደፃፈለት ተሰምቷል።

የቀድሞው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሀመድ የአሜሪካ ዜግነት ያለው ሲሆን የውጪ ዜግነቱን መልሶ የኢትዮጵያ ዜግነት ለመውስድ እየሞከረ እንደነበር ከወራት በፊት ገልጿል። ይሁንና የዜግነቱ ጉዳይ እልባት ሳያገኝ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲን ተቀላቅሎ መታወቂያም ወስዷል።

ጉዳዩን በተመለከት ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ለኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ድብዳቤ ፅፎ ማስረጃ የጠየቀ ሲሆን ፓርቲው በበኩሉ ጃዋር ማስረጃ እንዲያቀርብ በደብዳቤ አሳስቧል። የፓርቲው ሊቀመንበር መረራ ጉዲና ይህን መረጃ አረጋግጠዋል። “የኛ አባል ሲሆን ለምን ይህ ጥያቄ እንደተነሳ ባይገባኝም እኛ ደብዳቤ ፅፈንለታል” ብለዋል ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና።

እንዴት ለዜግነቱ ማረጋገጫ ሳያቀርብ በህግ ባልተፈቀደ መልኩ ጃዋር መሀመድ ፓርቲውን እንዲቀላቀልና መታወቂያ እንዲወስድ እንደተፈቀደለት ለተነሳላቸው ጥያቄ መረራ ጉዲና ሲመልሱ ” እኛ የምናውቀው ኢትዮጵያዊ መሆኑን ነው፣ የሀገሩን ቋንቋ ይናገራል፣ ፊቱም ኢትዮጵያዊ ይመስላል፤ መንግስትም ይህን ያውቃል” ሲሉ ቀልድ አዘል ምላሽ ስጥተዋል።

በጃዋር ዜግነት ላይ ከመንግስት የሚነሳው ጥያቄ ፖለቲካዊ ፍላጎትንም ያካተተ ሊሆን ይችላል ያሉት መረራ ጉዲና ጃዋር በቅርብ ዜግነቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዞ እንደሚመጣ ተስፋ እንደሚያደርጉና ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድም በጊዜው ምላሽ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

[ዋዜማ ሬድዮ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#JAWARMOHAMMED #OFC [በዋዜማ ሬድዮ] የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ በቅርቡ ፓርቲውን የተቀላቀለው ጃዋር መሀመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ደብዳቤ እንደፃፈለት ተሰምቷል። የቀድሞው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሀመድ የአሜሪካ ዜግነት ያለው ሲሆን የውጪ ዜግነቱን መልሶ የኢትዮጵያ ዜግነት ለመውስድ እየሞከረ እንደነበር ከወራት…
#JawarMohammed #Election2012

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ [ኦፌኮ] አቶ ጃዋር መሃመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ተጠይቋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በፃፈው ደብዳቤ መሰረት የቀረበ እንደሆነ ነው የተረጋገጠው። ኦፌኮ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥበት የደብዳቤው ኮፒ ለአቶ ጃዋር መሃመድ ልኮለታል።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የተናገሩት፦

"መንግስት ግቡና አግዙን ባለው መሰረት ወደሀገር ቤት የገባን፣ በፓርቲ አመራርነት ያልተቀመጠንና በምርጫ ገና ያልተወዳደረን አካል እንዲህ ማለቱ ግራ የሚያጋባ ነው። ስሙም፣ መልኩም ኢትዮጵያዊ ነው።"

ምንጭ፦ አል-ዓይን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#JawarMohammed #Election2012 የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ [ኦፌኮ] አቶ ጃዋር መሃመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ተጠይቋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በፃፈው ደብዳቤ መሰረት የቀረበ እንደሆነ ነው የተረጋገጠው። ኦፌኮ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥበት የደብዳቤው ኮፒ ለአቶ ጃዋር መሃመድ ልኮለታል። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የተናገሩት፦ "መንግስት…
#Election2012 #JawarMohammed

"አቶ ጃዋር የኢትዮጵያ ዜጋ ሆነዋል" - ጠበቃ ገመቹ ጉተማ

በታኅሳስ ወር የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን [ኦፌኮ] መቀላቀላቸውን ያስታወቁት ጃዋር መሐመድ ረቡዕ ጥር 13/2012 ለኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና የወሳኝ ኩነት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት የኢትዮጵያ ዜጋ መሆናቸውን ጠበቃቸው ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ተናግረዋል።

የጃዋር መሐመድ ጠበቃ የሆኑት ገመቹ ጉተማ፤ ጃዋር በዜግነት አዋጁ የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላታቸውን እና በዚህም መሰረት ለሚመለከተው አካል ማስገባታቸውን ገልፀዋል። ‹‹በሕጉ መሰረት ዜግነትን መልሶ ለማግኘት የምንጠብቀው ምንም ዓይነት መልስ የለም። አስፈላጊ ሰነዶችን ግን አስገብተናል›› ሲሉ ተናግረዋል።

[አዲስ ማለዳ ጋዜጣ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#JawarMohammed

ትላንት አዲስ ስታንዳርድ በእንግሊዘኛ ቋንቋ መረጃዎች የሚያሰራጭ ድረ ገፁ አቶ ጃዋር መሃመድ ለኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዜግነቱ እንዲመለስለት ያስገባባትን ሁለት ገፅ ማመልከቻ ይዞ ወጥቷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiabot
#JawarMohammed #Election2012

የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ /ኦፌኮ/ አባል የሆነው ጃዋር ሞሐመድ አሜሪካዊ ዜግነቱን እንደመለሰ የሚገልጹ ሰነዶችን በሙሉ ለኢምግሬሽን እንዳስገባ ትናንት በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡ ሌሎች የውጭ ዜግነት ያላቸው ፖለቲከኞች ጥያቄ እንዳልተነሳባቸው ጠቅሶ፣ ምርጫ ቦርድ እሱ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጉ እንዳሳዘነው አክሎ ገልጧል፡፡

More https://telegra.ph/JAWAR-02-13

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JawarMohammed

ወደወለጋ፣ወደኢሉባቦር ኦፌኮ ድጋፍ የለውም፤መሪዎቹም [ጃዋርን ጨምሮ] ወደዛ ላይሄዱ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች አሉ ተብለው 'ኬላ' በተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ የተጠየቁት አቶ ጃዋር መሃመድ የሰጡት ምላሽ፦

ምንሄደው ድጋፍ ያለን ቦታ ብቻ አይደለም። ምንሄደው ድጋፍ ለማጠናከር ነው። እኛ በሁሉም ወረዳ ላይ ህዝባችንን ማነጋገር እንፈልጋለን። ግን ሰዉ ይረሳል እንጂ በጣም ነገሮች በተጧጧፉበት እና መንግስት በጣም በተዳከመበት፣ በሌለበት ወቅት እኔና በቀለ እስከ አሶሳ ድረስ ሰው ማንም በማይሄድበት፣ የመንግስት ባለስልጣን ሀገር ጥሎ በጠፋበት ወቅትም ስንሄድ ነበር። አሁንም ወደምዕራብ እንሄዳለን።

ምዕራብና ደቡብ እንደሚታወቀው ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ ህጋዊ ያልሆነ ኮማንድ ፖስት አለ። ያ ኮማንድ ፖስት እንዲነሳ በህጉ challenge እናደርጋለን። እኛ ብቻ አይደለንም ጥምረት ፈጥረን እየሰራን ነው ያለነው ከኦነግ ጋር፣ ከኦብፓ ጋር አብረን ወደፊት የምናደርገው እንቅስቃሴ ይኖራል።

የማንሄድበት ዞን አይኖርም። ኦሮሚያ ውስጥ ብቻ አይደለም ወደ ተለያዩ ክልሎች የመሄድ እቅድ አለን። ደፍሮ ለሚለውም የተያያዝነው ትግል እንጂ ዳንስ አይደለም። ስለዚህ ሁሉም ቦታ እንሄዳለን። ስንሄድ ደግሞ በተጨባጭ ይታያል።

#TikvahFamily
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JawarMohammed

አቶ ጃዋር መሃመድ 'ኬላ' በተሰኘ የአሃዱ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ቀርበው 'ብዙ ኃይል ፖለቲካው ላይ እየባከነ ነው፤ የኢኮኖሚው ጉዳይ ተረስቷል' በሚል እይታቸውን እንዲያጋሩ ተጠይቀው ነበር። የኦፌኮ /KFO/ አባል የሆኑት አቶ ጃዋር ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና ፀጥታ ፈፅሞ የማይነጣጠሉ ገዳዮች እንደሆኑ አስረግጠው ተናግረዋል። ቁጭ ተብሎ ፖለቲካውን ማስተካከል ከተቻለ የፀጥታው ሁኔታ ይስተካከላል፣ የፀጥታው ሁኔታ ሲስተካከልም ኢኮኖሚው ይስተካከላል ሲሉም ተደምጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JawarMohammed

አቶ ጃዋር መሃመድ ከተናገሩት፦

"... 100 ሰዎች አንሆንም ይሄን ሀገር ለማረጋጋትም ፣ ለማበላሸትም እድሉ ያለን፤ አቅሙም ያለን 100 ሰዎች አንሆንም። እነዚህ 100 ሰዎች ዝም ብለው ውሸት ውስጥ ገብተው በComputer Generate በሚደረግ ገነትን ምድር ላይ እናመጣለን የሚል የማይሰራ ነገር ከማውራት፣ ቁጭ ብለን ፖለቲካውን ካስተካከልን ፀጥታው ይስተካከላል፣ ፀጥታው ከተስተካከለ ኢኮኖሚው እየተስተካከለ ነው የሚሄደው። እሱ ላይ ነው ትኩረት ማድረግ ያለብን"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JawarMohammed

የቀድሞው የOMN ዳይሬክተር የአሁኑ የኦፌኮ አባል የሆኑት ፖለቲከኛ ጃዋር መሃመድ ሚዲያዎች ሚዛናዊ ዘገባ እየሰሩ እንዳልሆነ ትላንት በOMN 'ልዩ ዝግጅት' በተሰኛ ፕሮግራም ላይ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ከሰሞኑ በOMN ላይ ከፍተኛ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲደረግ ነበር፤ ይህም ሆን ተብሎ እና ዝግጅት ተደርጎበት የተደረገ ነው ብለዋል። OMN የህዝብ ድምፅ መሆኑ እንዲሁም ለገዢውና ለስርዓቱ ፈተና መሆኑ የሚያስፈራቸው አካላት ናቸው ይህንን ያደረጉት ብለዋል።

አቶ ጃዋር ሚዲያዎች በተለይም የመንግስት ልሳን የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ በሰሞኑን ክስተት ዙሪያ ተደጋጋሚ ዜናዎችን ሲሰራ ከOMN ወገን ያለውን ነገር አልጠየቀም፣ በሰራቸው ሁሉም ዘገባዎች ላይም የOMN አመራሮችን ወይም ዳይሬክተርን አስተያየት አላካተትም ሲሉ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል።

ይህ ፋና ብሮድካስቲንግ ሚዛናዊ ያልሆነ የዘገባ ተግባር የማያሳየው የብሮድካስት ህጉ በOMN ላይ ብቻ ስራ ላይ እየዋለ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ብለዋል። አሁን በአመራር ላይ ያሉት የብሮድካስት አመራሮችም ህጉን የገዢውን ፓርቲና ግብረ-አብሮቹን ፍላጎት ለማስፈፀሚያ ብቻ እንደሚተረጉሙት ማሳያነው ሲሉ ወቅሰዋል።

MARCH 8 በነበረው ፕሮግራም ላይ OMN እራሱ ተጋብዞ ነው የመጣው ያሉት አቶ ጃዋር፤ ስርጭቱ ቀጥታ ስለነበር፤ ማን ምን ይናገራል የሚለውን ለመገመት የሚያስችል ምንም ነገር አልነበረም ሲሉ በወቅቱ ስለነበረው ሁኔታ በዝርዝር አስረድተዋል። የተፈጠረው ጉዳይ በOMN ላይ ጣት የሚያስቀስር እንዳልሆነም ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#COVID19 #SafeHands #JawarMohammed

እጃችንን በመታጠብ ራሳችንን ፣ ቤተሰባችንን እና ህዝባችንን ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] እንጠብቅ /Harka keenya saamumaan dhiqachuun kornavaayrasii irraa if haa eegnu/

📹3 MB
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Election2012 በኮቪድ19 ምክንያት ቀጣዩን ምርጫ ለማካሄድ አስቸጋሪ በመሆኑ መንግስት አራት የመፍትሄ አማራጮችን አቀረበ። “ኮቪድ19 ምርጫን ማራዘም እና የህግ አማራጮች” በሚል ርዕስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መንግስት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው። ኢትዮጵያ በህገ መንግስቱ መሰረት እስከ ነሃሴ ወር ማለቂያ ድረስ አጠቃላይ ምርጫ የማካሄድ ግዴታ ቢኖርባትም…
#JawarMohammed

"አራቱም አማራጮች አያዋጡም" - አቶ ጃዋር መሀመድ

መንግስት በኮቪድ-19 ምክንያት ቀጣዩን ምርጫ ለማካሄድ አስቸጋሪ በመሆኑ ያቀረባቸው አራት የመፍትሄ አማራጮች ዙሪያ ከወዲሁ አስተያየት እየተሰጡ ነው።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባል የሆኑት ፖለቲከኛው አቶ ጃዋር መሀመድ 'አራቱም አማራጮች አያዋጡም' ሲሉ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

'አራቱም አማራጮች ህጋዊ መሰረት የላቸውም፤ መፍትሄው ህጋዊ ሳይዎን ፖሊቲካዊ ስምምነት መፍጠር ነው' ሲሉም ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JawarMohammed

አቶ ጃዋር መሀመድ በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ከተናገሩት ፦

"መኖሪያ ቤቴ ውስጥ ከ100ሺህ ብር በላይ ፣ ወርቅ ፣ የእጅ ሰዓት እና በሽልማት ያገኘኋቸው የተለያዩ ሜዳሊያዎች ፖሊስ ወስዶ የራሱ ንብረት አድርጎታል። ለምንድነው የምዘረፈው ?

ከእኔ ጋር ለአንድ ቀን ሻይ የጠጡ ሰዎች የባንክ ሂሳባቸው ታግዷል ፤ አሁን ስልጣን ላይ ካሉ ባለስልጣናት ጋር ግን አብሮ ሻይ መጠጣት ብቻ ሳይሆን፣ ብዙ ነገር አብሬያቸሁ ሰርቻለሁ። እግዱ እውነተኛ ከሆነ ለምን የእነሱ የባንክ ሂሳብ አልታገደም?"

አቶ በቀለ ገርባ በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ የተናገሩት ፦

"እኔ ለ37 ዓመታት ያህል የመንግሥት ሰራተኛ ሆኜ የሰራሁ ሰው ነኝ። ይህን ያክል ዓመት የሰራ ሰው እንዴት አሮጌ መኪና ይኖረዋል ማለት ትክክል አይደለም።

ወደ አዳማ እና ነቀምቴ በሄድኩ ጊዜም ሕዝቡ ምን ዓይነት አቀባበል እንዳደረገልኝ ታውቃላችሁ። ወደ ውጪ በሄድኩ ጊዜም መኪና ተሸልሜ ነበር። ይህችን አሮጌ መኪና ንብረት አፈራ ተብሎ ማገዱ ትክክል አይደለም"

ተጨማሪ : https://telegra.ph/BBC-10-27 (BBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#JawarMohammed #BekeleGerba

በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ጀዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ የደህንነት ስጋት አለን በሚል ምክንያት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የልደታ ምድብ ችሎት የተከሳሾች የንብረት እግድ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነበር ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው።

ይሁን እንጂ ከተከሳሾች መካከል አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ፍርድ ቤት አልተገኙም።

ፍርድ ቤቱም አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ለምን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ በጠየቀበት ወቅት፤ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ተከሳሾቹ የደህንነት ስጋት አለብን በሚል ምክንያት አለመቅረታቸውን ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል።

በእነ አቶ ጀዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ውስጥ የተከሰሱት አቶ ሐምዛ ቦረና፤ "አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለ 'አገሪቱ አሁን ያለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ስጋት ስላለን በዚህ ቀጠሮ መገኘት አንችልም' ብለዋል" ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

"አሁን ባለው ሁኔታ አይደለም ጉዳት ይቅርና ሙከራ [የግድያ] ቢደረግብን አገሪቱ ወደ ከፋ አደጋ ውስጥ ስለሚያስገባት ለአገሪቱ በማሰብ ወደ ፍርድ ቤት ከሚደረግ ጉዞ እራሳችንን ቆጥበናል" ስለማለታቸው አቶ ሐምዛ ቦረና ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አሁን አገሪቱ ውጥረት ውስጥ እያለች በንብረት ጉዳይ ላይ ለመከራከር ፍርድ ቤት መመላለስ 'ለእኛ ሃፍረት' ነው በሚል ምክንያት ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን አቶ ሐምዛ፤ አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለን ወክለው ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

ፍርድ ቤቱ በንብረት እግዱ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሕዳር 15 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል። (BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፖለቲከኞቹ የረሃብ አድማ ፦

- እነአቶ ጃዋር መሀመድ በረሃብ አድማ ዛሬ 18ኛ ቀናቸውን መያዛቸው

- የፖለቲከኞቹ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ

- እነዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ባለው ሁኔታ ተገደው ክትትል ማቆማቸው

- ጠበቃ ከድር ቡሎ በተደጋጋሚ ውስኔ የተሰጠበት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መጣሱን መግለፃቸው

- ICRC አባላት ፖለቲከኞቹ ያሉበትን ሁኔታ መጎብኘታቸው

- አቶ በቀለ ገርባ ወደግል የህክምና ተቋማ እንዳይወሰዱ መከልከላቸው

- ስንት ቀን ያለምግብ መቆየት ይቻላል ? የዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ምላሽ

https://telegra.ph/JawarMohammed-02-14
TIKVAH-ETHIOPIA
የፖለቲከኞቹ የረሃብ አድማ ፦ - እነአቶ ጃዋር መሀመድ በረሃብ አድማ ዛሬ 18ኛ ቀናቸውን መያዛቸው - የፖለቲከኞቹ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ - እነዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ባለው ሁኔታ ተገደው ክትትል ማቆማቸው - ጠበቃ ከድር ቡሎ በተደጋጋሚ ውስኔ የተሰጠበት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መጣሱን መግለፃቸው - ICRC አባላት ፖለቲከኞቹ ያሉበትን ሁኔታ መጎብኘታቸው - አቶ በቀለ ገርባ ወደግል የህክምና…
#Update

ዛሬ የካቲት 8 የነአቶ ጃዋር መሃመድ ጠበቆች በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ እስረኞች የህክምና ጉዳይ አስመልክቶ ጉዳዩን ለሚያየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቤቱታ አቅርበው ነበር።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎትም እነአቶ ጀዋር መሀመድ በግል ሀኪሞቻቸው እንዲሁም በፈለጉት የግል ህክምና ተቋም መታከም እንደሚችሉ አፅንኦት ሰጥቶ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ከቀናት በፊት አቶ በቀለ እያደረጉት በሚገኘው የረሃብ አድማ ምክንያት በጠና ታመው ወደ ህክምና ተቋም ሊወሰዱ ሲሉ እንዳይሄዱ ማረሚያ ቤቱ "ከላይ በመጣ" ትዕዛዝ ከልክሎ እንደነበር የህክምና ክትትል የሚያደርጉላቸው ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል መግለፃቸው ይታወሳል።

በተጨማሪ ሀኪሞቻቸው ባለው ሁኔታ ተገደው ለእነአቶ ጃዋር የሚያደርጉትን የህክምና ክትትል ማቋረጣቸውን እንደገለፁ ይታወቃል።

https://telegra.ph/JawarMohammed-02-15
#JawarMohammed

አቶ ጃዋር መሀመድ (የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር) ከእስር ከተፈቱ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ " ኡቡንቱ ቲቪ " ለተሰኘ የማህበራዊ መገናኛ Exclusive ቃለ ምልልስ ሰጥተዋል።

በዚሁ ቃለ ምምልስ ወቅት አቶ ጃዋር ከተጠየቁት ጥያቄዎች አንዱ እሳቸውን በተመለከተ ሲናፈሱ የነበሩ አሉባልታዎችን እንዲያጠሩ ነው " አቶ ጃዋር ከገዢው ፓርቲ ጋር መስራት ጀምሯል፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝቷል የተፈታውም ለዚህ ነው ፤ አሁንም እየሰራ ያለው የመንግስትን ስራ ነው " ስለሚባሉት ጉዳዮች ግልፅ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ጃዋር መሀመድ ፦

" እኔም ሰማቸዋለሁ አሉባልታዎቹን ። እኔ ከማንም ጋር የግል ቁርሾ የለኝም። የታሰርኩትም ቢሆን በፖለቲካ ልዩነት እንጂ በግል ፀብ አይደለም።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር አልተገናኘንም፤ ሊያገኘኝ ከፈለገ ግን ሁሌም ዝግጁ ነኝ። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ብቻ ሳይሆን / ከዐቢይ ጋር ብቻ ሳይሆን ከመሮም ጋር፣ ከደብረፅዮንም ጋር ከሁሉም በአሁን ወቅት በሀገራችን ባለው ግጭት ውስጥ እየተሳተፉ ካሉ ኃይሎች ጋር ተገናኝቶ ሀገራችንን ከጦርነት አስወጥቶ ወደ ሰላም እና ልማት ለመመለስ እድሉ ከተገኘ ከማናቸውም ጋር ለመስራት፣ ከማናቸውም ጋር ለመተባበር ፣ ከማናቸውም ጋር ለመነጋገር በማንኛውም ቦታ እና ሁኔታ ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ።

እኔ ማልፈቅደው ግን ከማናቸውም ጋር አብሬ ጦርነት ማፋፋም አልፈልግም፤ ከማናቸውም ጋር።

ሁሉም በጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ይሁኑ በጦርነት ውስጥ እያልተሳተፉ ያሉ ምሁራን እና ሊህቃን ወደ ሰላም ጠረጴዛ መምጣት አለባቸው ብዬ አምናለሁ፤ ከአንዳቸውም ጋር ግላዊ ጠብ የለኝም።

ስለዚህ ገዥው ፓርቲ ሀገር እየገዛ ነው ያለው ፤ ሀገር እያስተዳደረ ነው ያለው ፣ ሀገሪቷ ለገባችበት ችግር ትልቁን ድርሻ የሚወስደው ገዢው ፓርቲ ነው፤ እንደመሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው ፤ ወደመፍትሄ የምንገባ ከሆነ የእነሱ ተሳትፎ፣ የእነሱ ፍቃደኝነት ወሳኝ ነው።

ስለዚህ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ አመራርም እንደ እዚህች ሀገር ዜጋም በሰላም ጉዳይ ላይ የሀገራችንን እጣፈንታ ወደፊት ማስተካከል ላይ ከገዢው ፓርቲም ጋር ሆነ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ሆነ፣ የተለያዩ ድርጅቶች ከሚመሩ ቅድም እንዳልኩት ከደብረፅዮን ሆነ ፣ ከፃድቃን ሆነው፣ ከመሮም ሆነ፣ ከገመቹ ሆነ፣ ከተፈራ ማሞ ሆነ ፣ ከይልቃል ከፋለ ጋርም ሆነ ከማንኛውም ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ፤ የሀገራችን አመራርም ለዚህ መዘጋጀት መቻል አለበት።

ሀገራችን ያለችበት ሁኔታ ለምን ከእከሌ ጋር ተነጋገርክ፣ እከሌ ሳይጣን ነው እከሌ መልአክ ነው በማለት እንደማያዋጣ ላለፉት 4 ፣ ላለፉት 2 ዓመታት ግልፅ ሆኗል።

ስለዚህ አሁንም ደግሜ የምለው ከማንኛውም የፖለቲካ ኃይል ጋር ፣ ከማንኛውም የፖለቲካ አመራር ጋር ህዝባችንን አሁን ከገባበት መቀመቅ እና ሰቆቃ ለማውጣት መስራት ያስፈልጋል።

እዚህ ላይ ግልፅ ማድረግ የምፈልገው ከማኛውም ኃይል ጋር እንሰራለን እንደ ድርጅትም እንደ ግለሰብም እንደ አመራርም፤ ሀገራችንን እና ህዝባችንን ወደ ሰላም መንገድ ወደ ልማት እንዲመለሱ ባለኝ እውቀት እና ባለኝ ተሰሚነት መጥቀም እፈልጋለሁ።

ነገር ግን ለማንም ድርጅት ሆነ ግለሰብ መጠቀሚያ መሆን አልፈልግም ፤ ለማንም የጦር ማገዶ መሆን አልፈልግም ፣ የማንንም አንባገነናዊ አካሄድን፤ የማንም ጦረኛ አካሄድን መደገፍ አልፈልግም።

ወደ ሰላም መምጣት ከሚፈልግ አካል ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ፣ ይሄ ደግሞ ኩነኔ አይደለም ይሄ ትክክለኛ ነው ብዬ የማምነው ፤ ስለዚህ ጦርነቱ መቆም አለበት ጦርነት ቆሞ ወደ ድርድር መምጣት አለብን ቴክኒካል ነገሮች መነሳት አለባቸው ስለዚህ ለመነጋገር ጋሬጣ ሆነው ያሉ ነገሮች ተሰባብረው ድልድይ ተመስርቶ ሁላችንም ወደመነጋገር መግባት አስፈላጊ ነው። "

@tikvahethiopia
#JawarMohammed

ኦፌኮ በብሄራዊ ምክክር ላይ አልሳተፍም ብሏል ?

አቶ ጃዋር መሀመድ (ምክትል ሊቀመንበር) ፦

" ትንሽ የግንዛቤ ችግር አለ። እኛ እንደ ኦፌኮ አንሳተፍም አይደለም ያልነው ቅድመ ሁኔታዎችን ነው ያስቀምጥነው። ብሄራዊ መግባባት (National Dialogue) የኦፌኮ አጀንዳ ነው።

... ስለዚህ ኦፌኮ የብሄራዊ ድርድርን ወይም የብሄራዊ መግባባትን አይፈልግም የሚለው የተሳሳተ አመለካከት ነው፤ እንፈልጋለን፤ አሁንም ቢሆን እንፈልጋለን ፤ አሁንም ቢሆን ለሀገራችን የሚጠቅመው እሱ ነው ብለን ነው የምናምነው።

ነገር ግን ብሄራዊ መግባባት ሲባል ፕሮሰስ አለው ፤ ብሄራዊ መግባባት በሁለት ደረጃ ነው በአንድ ሀገር ውስጥ ሊካሄድ የሚችለው።

አንዱ የፖለቲካ ልዩነቶች ወደ ጦርነት እንዳያመሩ የቅድመ ጦርነት ንግግር የሚባል ነው የፖለቲካ ልዩነቶች ፣ የፖለቲካ ሽኩቻዎች ሀገርን እና የፖለቲካ ኃይሎችን ወደ ጦርነት እንዳያስገቡ በንግግር እና በድርድር ለመፍታት የሚደረግ ብሄራዊ መግባባት አንድ አለ፤ ያ ሳይደረግ እድል አምልጦ ሀገር ወደ ጦርነት ከገባች በኃላ ደግሞ ጦርነት ቆሞ ከጦርነት በኃላ ለጦርነት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችም ሆኑ በጦርነት የተፈጠሩ ክስተቶች ለሌላ ጦርነት እንዳይጋብዙ ከስር መሰረቱ ለመፍታት የሚደረግ ክንውን ነው ፤ ይሄን መገንዘብ አስፈላጊ ነው።

ብሄራዊ መግባባት በጦርነት መካከል ሊካሄድ አይችልም። ሀገራችን በጦርነት መሀከል ነች፤ 2019/20 መጀመሪያ አካባቢ ቢሆን 2019/18 ጥሩ ጊዜ የነበረው ለውጡ እንደመጣ የመጀመሪያ ወራት መጀመር ነበረበት ያ አምልጧል አሁን ጦርነት ውስጥ ነው ያለነው።

ብሄራዊ መግባባት ሲባል የመጀመሪያው criteria ሁሉንም ያሳተፈ መሆን አለበት።

በተለይ ጦርነት ከተገባ ፣ ከሁሉም የበለጠ ብሄራዊ መግባባት ውስጥ መግባት እና መሳተፍ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባው በጦርነት ውስጥ የተሳተፉት ቡድኖች ናቸው። ጦርነት እየተካሄደ እነዚህ በጦርነት የተሳተፉ ቡድኖች ማሳተፍ አልቻልም። Legally ሆነ በ Security wise ማሳተፍ አይቻልም። ይህ ስለሆነ ዋናው እኛ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ብሄራዊ መግባባት ጥሩ ነው መንግስት ረጅም ጊዜ አልሰማም ብሎ አሁን የብሄራዊ መግባባት ማለቱ ጥሩ ነው ደስ ብሎናል ነገር ግን ይሄን ነገር በአግባቡ እንስራው ስለዚህ ጦርነት ይቁም ፤ ጦረኞቹ ሙሉ በሙሉ ይታረቁ አይደለም እያልን ያለነው ብሄራዊ መግባባቱ ላይ ሊታረቁ ይችላሉ ነገር ግን active fighting እንዲቆም ማድረግ በሰሜንም ፣ በትግራይ ድምበርም ፣ በቤኒሻንጉልም፣ በኦሮሚያም በተለያየ አካባቢ እየተደረገ ያለው ጦርነት መጀመሪያ መቆም አለበት... "

#ያንብቡ ➡️ https://telegra.ph/Jawar-Mohammed-05-27
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " Galatoomaa Tour " የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሐመድ ጀርመን ይገኛሉ። ዛሬ በጀርመን ኑርንበርግ በነበረ ህዝባዊ ስበስባ በእስር ላይ በቆዩባቸው ጊዜያት ለሳቸው እና አብረዋቸው ለታሰሩ ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ደጋፊዎቻቸው አድርገዋል ላሉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል። የእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዞ አንደኛው አላማ ምስጋና…
#JawarMohammed

አቶ ጃዋር መሐመድ (የኦፌኮ ም/ሊቀመንበር) በዛሬው የጀርመኑ ህዝባዊ ስብሰባ ወቅት ካነሷቸው ነጥቦች ጥቂቶቹ ፦

➡️ አቶ ጃዋር አጠቃላይ ኢትዮጵያም ሆነ ኦሮሚያ በብዙ ውጥንቅጥ ውስጥ መሆናቸውን ገልፀው ፤ ከዚህ ውጥንቅጥ ተወጥቶ #ሰላም እንዲሰፍን የማድረግ ጥረት መጀመራቸውን ገልፀዋል።

➡️ አቶ ጃዋር ለጀመሩት ሰላም የማስፈን ጥረት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ደጋፊዎቻቸው አብረዋቸው ሆነው ጦርነት እንዲቆም ፣ ሰላም እንዲሰበክ፣ ሰላም እንዲፈጠረ በአንድ እና ሁለት ክልል የተወሰነ ሳይሆን በመላው ሀገሪቱ ሰላም እንዲፈጠር ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

➡️ ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሆን በመሰረታዊነት ኦሮሚያ ውስጥ ያለው ችግር ከመሰረቱ መፈታት አለበት የሚል እምነት እንዳላቸው ገልፀው ለዚህም ጦርነት በማቆም ሁሉም ወደ ሰላም የሚመለስበት እድል እንዲፈጠር እሻለሁ ብለዋል።

Credit- መረጃው ስብሰባውን በአካል የተካፈለው የዶቼቨለ ሬድዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ታምራት ዲንሳ ነው ያጋራው።

@tikvahethiopia