TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ምክር ቤቱ የ3 ሚኒስትሮችን ሹመት አፅድቋል... የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጉባኤው የ3 ሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ አፅድቋል። በሹመቱም ዶ/ር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ የትምህርት ሚኒስትር፣ ዶክተር አብርሃ በላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እንዲሁም አቶ መላኩ አለበል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ሹመቱን በማፅደቁ ሂደትም ጥር…
ከዩኒቨርሲቲዎች ሁከት ጋር በተያያዘ 1,207 ሰዎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል!

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6 ወራት የስራ ሪፖርት አቅርበዋል።

- ከህዳር 30/2012 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ሁከቶች መቀስቀሳቸውን ተገልጿል። ለዚህ ምክንያት ተደርጎ የቀረበው ተዛባ የሚዲያዎች ዘገባ አንዱ ሆኖ ተጠቅሷል። ሚዲያዎች ግጭቱ የብሄር እና የሃይማኖት መልክ እንዲይዝ ሲሰሩ ነበር ተብሏል።

- በተጨማሪ ለሁከቶች መቀስቀስ ምክንያት የመሰረተ ልማት አለመሟላት እንደ ዋነኛ ችግር ተጠቅሷል። ግጭቶች ሲፈጠሩ መንግስት በአፋጣኝ ደርሶ እርምጃዎችን እንዳይወስድ የመሰረተ ልማት ችግሮች በዋነኛነት ተጠቅሷል።

- የአካባቢ ፖለቲካ ሁኔታ ለግጭቶች መባባስ ከፍተኛ አስተዋፆ እንደነበረው ተገልጿል።

- የዩኒቨርሲቲ አመራር ድክመት፣ አስተዳደራዊ እርምጃ አለመውሰድ፣ ዝቅተኛ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ፣ ተቀናጅቶ አለመስራት..ግጭቶች እንዲባባሱ እንዳደረገ ተገልጿል።

- ሚኒስቴሩ ችግሮችን ለመፍታት ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከ20 ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ምክክር ካደረገ በኃላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግል አመራር እንዲሰጡበት መደረጉ ተገልጿል። በዚህም ዩኒቨርሲቲዎች በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ፣ የግቢ አጠባበቅ በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ መመሪያ መተላለፉ ተገልጿል።

- 1,207 ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ ቅጣት ተላልፏል። 921 ተማሪዎች የተለያዩ ቅጣቶች ተወስኖባቸዋል ተብሏል።

- 421 ተማሪዎች ከ1 ዓመት አንስቶ ሙሉ በሙሉ እስከ ማባረር እርምጃ ተወስዷል።

- 140 ተማሪዎች እና መምህራን የተለያየ ቅጣት ተላልፎባቸዋል፤ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ እንደሚገኝ ተገልጿል።

More https://telegra.ph/FBC-01-30

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - ባልታወቁ ሰዎች የታገቱት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ጉዳይ የሚያጠራ የምርመራ ቡድን መቋቋሙ ተገልጧል። የምርመራ ቡድኑ ሦስት እንደኾነ ነው የተሰማው። - ተማሪዎቹ በታገቱበት አካባቢ የተደራጁ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱ መኾናቸውን በመግለጥ መንግስት እርምጃ እየወሰደ ነው። - የታጋቱት ተማሪዎች ሦስት ወላጆች ከሚኖሩበት ዞን ጽ/ቤቶች ተደውሎላቸው አዲስ አበባ ገብተዋል። - የጀርመን ድምፅ…
#UPDATE

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በቅርቡ ከታገቱት የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወላጆች ጋር ተወያዩ።

በውይይቱም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚልና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በተጨማሪ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተማሪዎቹ የትውልድ ቦታ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

የተማሪ ወላጆች በዚህ ወቅት የልጆቻቸው አድራሻ እስከጠፋበት ዕለት ድረስ የነበራቸው የስልክ ልውውጥ ምን እንደሚመስልም ጉዳዩን በሚመለከት የተቋቋመው ግብረ-ሃይልን ለሚመሩት ኃላፊዎች አብራርተዋል።

[ENA]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ሰሞኑን በመቐለ/ትግራይ የሚገኙ ሁሉም የኢ/ያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ገንዘብ ወጪ በሚያደርጉ ደንበኞች ባልተለመደ ሁኔታ ተጨናንቀዋል፡፡ በገንዘብ ኖት እጥረት ምክንያት ባንኩ ከ2ሺህ ብር በላይ ለደንበኞች ለመስጠት ተቸግሮ መቆየቱም ተገልፆል፡፡

[ጋዜጠኛ ሚሊዮን ኃይለስላሴ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሞጣ ድጋፍ ማሰባሰቢያ አካውንቶችን ይፋ አድርጓል፦ አካውንት ስም: በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሞጣ ድጋፍ ማሰባሰቢያ የሂሳብ ቁጥሮች 1/ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000315148457 ቀራንዮ ቅርንጫፍ 2/ ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1000054280428 አባነፍሶ ቅርንጫፍ 3/አዋሽ ባንክ 01304069690301…
ለሞጣ ሙስሊሞች የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገ ነው...

የማህበራዊ ሚዲያውን ዞር ዞር እያልን እየተመለከትን እንገኛለን፤ ከሰሞኑን ይፋ በተደረጉ የድጋፍ ማድረጊያ የባንክ አካውንቶች በርካታ ሰዎች ለሞጣ ሙስሊሞች ድጋፍ እያደረጉ እንደሆነ እየተመለከትን ነው። ይኸው የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ነገ ዓርብ በስፋት እንደሚቀጥልም ተረድተናል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

በኢትየጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ሲካሄድ የነበረው ውይይት ከምን ላይ እንደደረሰ ከተሳታፊዎቹ አልተሰማም።

የሶስቱ አገራት የውጪ ጉዳይ እና የውሃ ሚንስትሮች በዋሽንግተን ዲሲ ተገናኝተው የመከሩ ሲሆን፤ ቀድሞ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ሦስቱ አገራት የደረሱትን ስምምነት ትናንት ይፋ እንደሚያደርጉ ተጠብቆ ነበር።

ከሁለት ሳምንታት በፊት ሦስቱ አገራት እንዲሁም አሜሪካ እና የዓለም ባንክ በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ በሕዳሴው ግድብ ሙሊት እና ሌሎች መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት በሚያደርሱ ነጥቦች ላይ ተግባብተናል ብለው ነበር።

በአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ እንደሆነ በተነገረለት የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ አሞላል ዙሪያ የተፈጠረውን ልዩነት ለማጥበብ በተከታታይ ዋሽንግተንን ጨምሮ በሦስቱ አገራት መዲናዎች ሲካሄድ ቆይቷል።

የሦስቱ አገራት የውጪ ጉዳይና የውሃ ሚኒስትሮች ግድቡ ውሃ የሚሞላበትን እና ሥራ የሚያከናውነትን ሁኔታ ላይ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ ባለፉት ሁለት ቀናት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴርና በዓለም ባንክ በታዛቢነት በተገኙበት የቀረበው ረቂቅ የስምምነት ሰነድ እንደሚያመለክተው በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው ግድብ በዝናብ ወቅት በተለያዩ ደረጃዎች በውሃ እንዲሞላ የሚመክር ነው።

More https://telegra.ph/BBC-01-30

[BBC]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
CARD FoE and Legitimate Restrictions.pdf
1.2 MB
7ቱ የተዛቡ መረጃ ዓይነቶች!

1ኛ - ስላቅ ወይም ቀልድ (Satire or Parody) - እነዚህኞቹ አንባቢውን ለመጉዳት ወይም ለማሳሳት የተፈጠሩ ሳይሆን ለማስገረም፣ ለማዝናናት ወይም ባለታሪኩ ላይ ለማላገጥ የተዘጋጁ መረጃዎች ናቸው፤ ነገር ግን በተደራሲዎቹ እንደ እውነት ሊቆጠሩ ይችላሉ።

2ኛ - አሳሳች ይዘት (misleading content) - እነዚህኞቹ መረጃዎቹ ስህተት ባይሆኑም የቀረቡበት መንገድ ግን ተደራሲያኑን በማሳሳት ሌላ ነገር እንዲገምቱ ወይም እንዲያምኑ የሚያደርግ ነው።

3ኛ - የተፈበረከ ይዘት (fabricated content) - ጉዳት ለማስከተል በማሰብ ሙሉ ለሙሉ የተፈጠረ የሐሰት መረጃ።
4ኛ - ለምድ ለባሽ ይዘት (Imposter content) - መረጃው ከታማኝ ምንጭ ወይም ቢሮ የተገኘ ለማስመሰል የተደረገ ነገር ግን የተፈበረከ የሐሰት መረጃ።

5ኛ - የውሸት ግንኙነት (False connection) - ሁለት የማይገናኙ ነገሮችን (ፎቶ እና ታሪኩ፣ ርዕሱና ዝርዝሩ…) እንደሚገናኙ አስመስሎ ማቅረብ።

6ኛ - የውሸት ዐውድ (False context) - እውነተኛ ታሪኮችን እና ምስሎችን እየተጠቀሙ ነገር ግን ከአገባቡ ውጪ በመጥቀስ መረጃ ማዛባት።

7ኛ - አላግባብ የተተረጎመ ይዘት (manipulated content) - መረጃው ብዙ ተመልካች እንዲያገኝ ሲባል ብቻ አዛብቶ ማቅረብ።

[ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነትና ቅቡልነት ያላቸው ገደቦች]

#CARD
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የሚመሩት ስብሰባ በድርጅቱ ዋና መቀመጫ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ዛሬ ይካሄዳል። የድርጅቱ የጤና ባለሙያዎች ለዶክተር ቴድሮስ የኮሮና ቫይረስን አሁን ያለበትን ሁኔታ አስመልክቶ ገለጻና ምክረ ሀሳብ ያቀርባሉ። ከውይይቱ በኋላ የዓለም የጤና ድርጅት የሚያሳልፈውን ውሳኔ ይፋ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል። በተጨማሪም የጤና ባለሙያዎች…
#UPDATE

የዓለም ጤና ድርጅት በቻይና የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው በሚል አወጀ።

ድርጅቱ ቫይረሱን በዓለም አቀፍ የጤና ስጋትነት ያወጀው ከቻይና ውጭ ወደ ሌሎች ሀገራት መዛመቱን ተከትሎ ነው ተብሏል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እንዳስታወቁት፥ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ጤና ስጋትነት የታወጀበት ዋነኛው ምክንያት በቻይና እየሆነ ባለው ሳይሆን በሌሎች የዓለም ሀገራት ላይ መሰራጨት በመጀመሩ ነው።

በተለይም የኮሮና ቫይረስ አሁን ባለበት ሁኔታ ደካማ የጤና ስርዓት ባላቸው ሀገራት ከተሰራጨ እጅግ አሳሳቢ መሆኑንም ነው ድርጅቱ የገለፀው።

ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ቻይና በሽታውን ለመቆጣር እያደረገች ያለውን ሁሉን አቀፍ ጥረት በማድነቅ፥ ሀገራት ከቻይና ጋር የንግድ እና የጉዞ ግንኙነታቸውን የሚያቋርጡበት ምንም ምክንያት የለም ብለዋል።

ሆኖም ግን በርካታ ሀገራት ከቻይና ጋር ድንበራቸውን መዝጋታቸው እና የአውሮፕላን በረራ ያቋረጡ ሲሆን፥ እንደ ጎግል፣ ስታርባክስና ቴስላን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችም በቻይና ያላቸውን ቢሮ እየዘጉ ነው። የአሜሪካ መንግስትም ዜጎቹ ወደ ቻይና ከመሄድ እንዲቆጠቡ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ማውጣቱ ነው የተገለፀው።

[BBC, ኤፍቢሲ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 170 ደርሷል - በቫይረሱ የተጠየቁ 7736 ሰዎች - ከቻይና ውጭ የተጠቁ 75 ሰዎች - 124 ሰዎች ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል የዓለም የጤና ድርጅት በኮሮና ቫይረስ ዓለማቀፍ ስጋትነት ዙሪያ ዛሬ አስቸኳይ ስብሰስባ እንደሚያደርግ ተሰምቷል። ቫይረሱ ከተዳረሰባቸው ሀገራት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑንም ድርጅቱ ገልጿል። በሌላ መረጃ፦ የዓለም አትሌቲክስ ፌደሬሽን…
#UPDATE

- የሟቾች ቁጥር 213
- በቫይረሱ የተያዙ ከ10,000 በላይ
- ከቻይና ውጪ በ18 ሀገራት ታይቷል
- ከቻይና ውጪ 98 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል

በቻይና ብቻ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 213 ደርሷል። በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቁጥራቸው ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተሰምቷል።

የኮሮና ቫይረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በ18 ሀገራት የታየ ሲሆን፥ በእነዚህ ሃገራት 98 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ይላል የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ።

ከእነዚህ ሃገራት ውስጥ በታይላንድ እና በጃፓን በ14 ሰዎች ላይ፣ በሲንጋፖር በ13 ሰዎች ላይ፣ በአውስትራሊያ እና ማሌዢያ በ8 ሰዎች ላይ፣ በደቡብ ኮሪያ 6 ሰዎች ላይ እንዲሁም በፈረንሳይ እና አሜሪካ በ5 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱም ነው የተገለፀው።

[WHO, ኤፍቢሲ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ይቅርታ፣ እርቅ እና ይቅርታ!

የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ዛሬ በእርቀ ሰላም ሂደት ውስጥ የጋዜጠኞች ሚና በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የውይይት መርሃግብር አዘጋጅቷል፡፡

በፕሮግራሙ የግጭት አፈታት ክህሎት እና ይቅርታ በሚል ርዕስ በዚህ ዘርፍ በርካታ ሥራዎችን በሰሩትና ስድስተኛ መጽሐፋቸውን በዚው ርዕሰ ጉዳይ ላይ በሰሩት ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ አማካኝነት እየቀረበ መነሻ ጹሑፍ እየቀረበ ይገኛል፡፡

በዝግጅቱ ከተለያዩ ሚዲያዎች የተጋበዙ ጋዜጠኞች የተገኙ ሲሆን ለሁለት ቀናት ይቆያልም ተብሏል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
Vaayirasii Koronaa: Dursanii Ittisuuf Ergaa Fayyadu

#share
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኮሮና ቫይረስ: አስቀድሞ ለመከላከል ጠቃሚ መልዕክት!

#share #ሼር
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ኢትዮጵያስ ቫይረሱን ለመከላከል ምን ዝግጅት አድርጋለች?

• ወደ አምስት የቻይና ከተሞች በረራ እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ተጓዦቹንና የበረራ ሰራተኛዎቹን በዓለም አቀፍ መስፈርት ጥንቃቄ በማድረግ በረራውን ወደ ቻይና እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል፡፡

• ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ወደ አምስቱም የቻይና መዳረሻዎቹ ማለትም ወደ ቤጂንግ፣ ሻንሃይ፣ ጓንዡ፣ ቼንጉ እና ሆንግ ኮንግ በረራውን በማድረግ ላይ መሆኑን ነው ዓየር መንገዱ የገለጸው፡፡

• የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ደግሞ ከቻይና እና አጎራባች አገሮች ለሚመጡ መንገደኞች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሙቀት ልየታ ተግባር እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል፡፡

• ተቋሙ እስከ ጥር 18/2012 ዓ.ም ድረስ ለ20 ሺህ 802 መንገደኞች የቅድመ ልየታ ማድረጉን ገልጧል፡፡

• የቅድመ ምርመራ ከተደረገላቸው መካከልም 552 ያክሉ የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ካለባቸው ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ናቸው፡፡

• ከነዚህም ውስጥ ከቻይና የመጡ አራት የበሽታው አስጊ ምልክት ይኖርባቸዋል የተባሉ ሰዎች በለይቶ ማከሚያ ማእከል ሆነው ክትትል እንደተደረገላቸው ታውቋል፡፡

• ከአራቱ ተጠርጣሪዎች የላብራቶሪ ናሙና ተወስዶ በደቡብ አፍሪካና በሀገር ውስጥ ምርመራ እንደተደረገና ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

• በበሽታው ለተጠረጠሩ መንገደኞች ክትትል ለማድረግም የጊዜያዊ ማቆያ ማእከል በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተቋቁሟል፡፡

• በበሽታው የተጠረጠሩና የተረጋገጠባቸው ሰዎች ከተገኙ ተለይቶ ክትትል የሚያገኙባቸው ክፍሎች ተዘጋጅተዋል፡፡

More https://telegra.ph/ETH-01-31

[AMMA]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
Audio
AMH-Nakur-WesternOromia-1-30-2020
"ህብረተሰቡ ለሁለት ጌቶች መገዛት አንገሽግሾታል"

በምዕራብ ኦሮምያ በሚስተዋለው የፀጥታ ችግር ተማረው ወደ ጋምቤላና ሌሎችም ከተሞች እየሸሹ እንደሆነ አንዳንድ የቄለም ወለጋ ነዋሪዎች ተናገሩ።

በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎችና ራሳቸውን የነፃነት ተዋጊዎች ነን ብለው በሚጠሩ ሸማቂዎች መካከል የሚደረገው ተኩስ ልውውጥ ህይወታቸው ላይ አደጋ መጋረጡንም አነዚህ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ሰብዓዊ መብት መምህራን የምዕራብ ኦሮምያ አለመረጋጋት የኅብረተሰቡን ኑሮ አስቸጋሪ ማድረጉን ተናግረው ለኅብረተሰቡ ሰላም ሲባል ሁለቱም አካላት ያሉበትን መንገድ ቆም ብለው ማጤን እንዳለባቸው አሳስበዋል።

[VOA]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 213 - በቫይረሱ የተያዙ ከ10,000 በላይ - ከቻይና ውጪ በ18 ሀገራት ታይቷል - ከቻይና ውጪ 98 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል በቻይና ብቻ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 213 ደርሷል። በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቁጥራቸው ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተሰምቷል። የኮሮና ቫይረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በ18 ሀገራት የታየ ሲሆን፥…
#UPDATE

የኬንያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የቻይና በረራዎችን ለጊዜው ማገዱን አስታወቀ። አየር መንገዱ ከኬንያ ቻይና እንዲሁም ከቻይና ኬንያ የሚደረጉ በረራዎችን ማገዱን አስታውቋል።

የእገዳውን የጊዜ ርዝመት ለመወሰን ከጤና እና ከውጭ ጉዳዮች ሚኒስትሮች ጋር ምክክር እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል። ከቻይና ውጭ ወደ ታይላንድ ባንኮክ የሚያደርገው ጉዞ ግን ይቀጥላል ብሏል አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ።

ባለፈው ማክሰኞ ከቻይናዋ ውሃን ከተማ ወደ ኬንያ የተመለሰ ኬንያዊ ተማሪ ሆስፒታል ውስጥ በገለልተኛ ክፍል ምርመራ ሲደረግለት ቆይቷል።

በአፍሪካ በቫይረሱ ተይዘዋል በሚል የተጠረጠሩ ስድስት ሰዎች ቢገኙም በተደረገላቸው ምርመራ ሁሉም ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል። ከቫይረሱ ስርጭት ጋር በተያያዘ የተወሰኑ ሃገራት ወደ ቻይና የሚደረጉ በረራዎችን ማገዳቸው ይታወሳል፡፡

[Elias Meseret]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia