TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የሚመሩት ስብሰባ በድርጅቱ ዋና መቀመጫ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ዛሬ ይካሄዳል። የድርጅቱ የጤና ባለሙያዎች ለዶክተር ቴድሮስ የኮሮና ቫይረስን አሁን ያለበትን ሁኔታ አስመልክቶ ገለጻና ምክረ ሀሳብ ያቀርባሉ። ከውይይቱ በኋላ የዓለም የጤና ድርጅት የሚያሳልፈውን ውሳኔ ይፋ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል። በተጨማሪም የጤና ባለሙያዎች…
#UPDATE

የዓለም ጤና ድርጅት በቻይና የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው በሚል አወጀ።

ድርጅቱ ቫይረሱን በዓለም አቀፍ የጤና ስጋትነት ያወጀው ከቻይና ውጭ ወደ ሌሎች ሀገራት መዛመቱን ተከትሎ ነው ተብሏል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እንዳስታወቁት፥ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ጤና ስጋትነት የታወጀበት ዋነኛው ምክንያት በቻይና እየሆነ ባለው ሳይሆን በሌሎች የዓለም ሀገራት ላይ መሰራጨት በመጀመሩ ነው።

በተለይም የኮሮና ቫይረስ አሁን ባለበት ሁኔታ ደካማ የጤና ስርዓት ባላቸው ሀገራት ከተሰራጨ እጅግ አሳሳቢ መሆኑንም ነው ድርጅቱ የገለፀው።

ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ቻይና በሽታውን ለመቆጣር እያደረገች ያለውን ሁሉን አቀፍ ጥረት በማድነቅ፥ ሀገራት ከቻይና ጋር የንግድ እና የጉዞ ግንኙነታቸውን የሚያቋርጡበት ምንም ምክንያት የለም ብለዋል።

ሆኖም ግን በርካታ ሀገራት ከቻይና ጋር ድንበራቸውን መዝጋታቸው እና የአውሮፕላን በረራ ያቋረጡ ሲሆን፥ እንደ ጎግል፣ ስታርባክስና ቴስላን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችም በቻይና ያላቸውን ቢሮ እየዘጉ ነው። የአሜሪካ መንግስትም ዜጎቹ ወደ ቻይና ከመሄድ እንዲቆጠቡ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ማውጣቱ ነው የተገለፀው።

[BBC, ኤፍቢሲ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot