TIKVAH-ETHIOPIA
ምክር ቤቱ የ3 ሚኒስትሮችን ሹመት አፅድቋል... የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጉባኤው የ3 ሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ አፅድቋል። በሹመቱም ዶ/ር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ የትምህርት ሚኒስትር፣ ዶክተር አብርሃ በላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እንዲሁም አቶ መላኩ አለበል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ሹመቱን በማፅደቁ ሂደትም ጥር…
ከዩኒቨርሲቲዎች ሁከት ጋር በተያያዘ 1,207 ሰዎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል!

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6 ወራት የስራ ሪፖርት አቅርበዋል።

- ከህዳር 30/2012 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ሁከቶች መቀስቀሳቸውን ተገልጿል። ለዚህ ምክንያት ተደርጎ የቀረበው ተዛባ የሚዲያዎች ዘገባ አንዱ ሆኖ ተጠቅሷል። ሚዲያዎች ግጭቱ የብሄር እና የሃይማኖት መልክ እንዲይዝ ሲሰሩ ነበር ተብሏል።

- በተጨማሪ ለሁከቶች መቀስቀስ ምክንያት የመሰረተ ልማት አለመሟላት እንደ ዋነኛ ችግር ተጠቅሷል። ግጭቶች ሲፈጠሩ መንግስት በአፋጣኝ ደርሶ እርምጃዎችን እንዳይወስድ የመሰረተ ልማት ችግሮች በዋነኛነት ተጠቅሷል።

- የአካባቢ ፖለቲካ ሁኔታ ለግጭቶች መባባስ ከፍተኛ አስተዋፆ እንደነበረው ተገልጿል።

- የዩኒቨርሲቲ አመራር ድክመት፣ አስተዳደራዊ እርምጃ አለመውሰድ፣ ዝቅተኛ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ፣ ተቀናጅቶ አለመስራት..ግጭቶች እንዲባባሱ እንዳደረገ ተገልጿል።

- ሚኒስቴሩ ችግሮችን ለመፍታት ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከ20 ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ምክክር ካደረገ በኃላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግል አመራር እንዲሰጡበት መደረጉ ተገልጿል። በዚህም ዩኒቨርሲቲዎች በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ፣ የግቢ አጠባበቅ በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ መመሪያ መተላለፉ ተገልጿል።

- 1,207 ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ ቅጣት ተላልፏል። 921 ተማሪዎች የተለያዩ ቅጣቶች ተወስኖባቸዋል ተብሏል።

- 421 ተማሪዎች ከ1 ዓመት አንስቶ ሙሉ በሙሉ እስከ ማባረር እርምጃ ተወስዷል።

- 140 ተማሪዎች እና መምህራን የተለያየ ቅጣት ተላልፎባቸዋል፤ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ እንደሚገኝ ተገልጿል።

More https://telegra.ph/FBC-01-30

@tikvahethiopia