TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ATTENTION

የአንበጣ መንጋ በአዳማ ከተማ መታየቱን የቲክቫህ አዳማ ቤተሰቦች አሳውቀዋል። የአዳማ ቤተሰቦቻችን የሚመለከተው ሁሉ መንጋው ጉዳት እንዳያደርስ ጥንቃቄ እንዲያደርግም መልዕክት አስተላልፈዋል። የአንበጣ መንጋውን የመከላከል ስራን በተመለከተት መረጃዎች ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ATTENTION

ተጨማሪ ፎቶዎች ከአዳማ ቲክቫህ ቤተሰቦች ተልከውልን እየተመለከትን ነው። በከተማይቱ የተለያዩ አካባቢዎች የአንበጣ መንጋ በስፋት ይታያል። የሚመለከተው ሁሉ ትኩረት እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የአንበጣ መንጋ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ስጋት ነው...

ከየመንና ከሶማሊያ የሚነሳው የአንበጣ መንጋ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ስጋት መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ መከላከል ድርጅት አስታውቋል። የግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ የአንበጣ መንጋን ለመከላከል ከ160 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልገኛል ብሏል።

[ኢዜአ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ መከላከል ድርጅት የመረጃ አሰባሰብና ትንበያ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ፈለገ ኤልያስ የተናገሩት፦

ከሁለቱ አገራት ሊገባ የሚችል የአንበጣ መንጋ ለኢትዮጵያ ስጋት ነው። የመንና ሶማሊያ በጸጥታ ችግር ሳቢያ መንጋውን በአግባቡ መከላከል ስለማይችሉ ለአጎራባች አገራት በተለይም ለኢትዮጵያ አስጊ ይሆናል። የአንበጣ መንጋው የመራቢያ ጊዚውን ሳይጨርስ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚያደርሰው ጉዳት የበረታ ሊሆን ይችላል።

ኢትዮጵያ ከድርጅቱ ጋር በመተባበር ከአሁን በፊት ወደ አገር ውስጥ የገባውን የአንበጣ መንጋ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መከላከል ችላለች። የአገራት ትብብር ዝቅተኛ መሆንና የመከላከል አቅም ማነስ ለአካባቢው አገራት ስጋት ነው።  አንበጣው ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ኬንያ በምግብ እህል ራሳቸውን ለመቻል በሚያደርጉት ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል።

ባለፉት አራት ወራት በኢትዮጵያ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ሁለት አውሮፕላን በማሰማራት የመከላከል ስራ ተስርቷል። በቀጣይም በምስራቅ አፍሪካ ባሉ አጋራት የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ አስቀድሞ የመከላከል ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
ከቻይና የመጡት 4ቱ ኢትዮጵያውያን... ከቻይና የመጡ 4 ኢትዮጵያዊያን የኮሮና ቫይረስ ይኖርባቸዋል በሚል ተጠርጥረው ወደ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል መግባታቸው ተነግሯል። ከአራቱ ኢትዮጵያዊያን መካከል 2 ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰበት ውሃን ከተማ የመጡ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ለ4 ተጠርጣሪ ግለሰቦች በአገር ቤት በተደረገ ምርመራ ከ5 ዓይነት የኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል ተብሏል፡፡ ይሁንና አሁን ወደ…
4ቱ ኢትዮጵያውያን ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል...

በኮሮና ቫይረስ በመያዝ የተጠረጠሩ አራት ኢትዮጵያውያን ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ኢትዮጵያውያኑ ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ በተደረገላቸው ምርመራ ነፃ መሆናቸው የተረጋገጠ ቢሆንም ለተጨማሪ ምርመራ ናሙናቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ መላኩ ይታወሳል።

በዚህም በደቡብ አፍሪካ በተደረገው ምርመራ. አራቱም ኢትዮጵያውያን ከኖቭል ኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል ብሏል ሚኒስቴሩ።

[ኤፍ ቢ ሲ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
«ግጭቶችና የመብት ጥሰቶች ያልተመለሱ የፖለቲካ ጥያቄዎች ውጤቶች ናቸው» - ዶክተር ዳንኤል በቀለ [የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽ ኮሚሽነር]

በኢትዮጵያ የተከሰቱት ግጭቶች እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች የሕዝቦች ያልተመለሱ የፖለቲካ ጥያቄዎች እና ፍላጎቶች ውጤቶች መሆናቸውን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ገልፀዋል።

ኮሚሽነሩ ዶክተር ዳንኤል በቀለ ከዘ-ኢትዮጵያን ሄራልድ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ የሕዝቡ የፖለቲካ ፍላጎት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከአስተዳደራዊ፣ ከሉዓላዊነት፣ ከማንነት እና ሌሎች ካልተመለሱ እና ከተወሳሰቡ የፖለቲካ ፍላጎቶች ጋር የተዛመዱ ናቸው፤ እነዚህ ፍላጎቶች በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች እየተከሰቱ ላሉት ግጭቶች ዋና መንስኤዎች ናቸው ብለዋል።

More https://telegra.ph/EPA-01-30

[ዘ-ኢትዮጵያን ሄራልድ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
ምክር ቤቱ የ3 ሚኒስትሮችን ሹመት አፅድቋል... የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጉባኤው የ3 ሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ አፅድቋል። በሹመቱም ዶ/ር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ የትምህርት ሚኒስትር፣ ዶክተር አብርሃ በላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እንዲሁም አቶ መላኩ አለበል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ሹመቱን በማፅደቁ ሂደትም ጥር…
ከዩኒቨርሲቲዎች ሁከት ጋር በተያያዘ 1,207 ሰዎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል!

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6 ወራት የስራ ሪፖርት አቅርበዋል።

- ከህዳር 30/2012 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ሁከቶች መቀስቀሳቸውን ተገልጿል። ለዚህ ምክንያት ተደርጎ የቀረበው ተዛባ የሚዲያዎች ዘገባ አንዱ ሆኖ ተጠቅሷል። ሚዲያዎች ግጭቱ የብሄር እና የሃይማኖት መልክ እንዲይዝ ሲሰሩ ነበር ተብሏል።

- በተጨማሪ ለሁከቶች መቀስቀስ ምክንያት የመሰረተ ልማት አለመሟላት እንደ ዋነኛ ችግር ተጠቅሷል። ግጭቶች ሲፈጠሩ መንግስት በአፋጣኝ ደርሶ እርምጃዎችን እንዳይወስድ የመሰረተ ልማት ችግሮች በዋነኛነት ተጠቅሷል።

- የአካባቢ ፖለቲካ ሁኔታ ለግጭቶች መባባስ ከፍተኛ አስተዋፆ እንደነበረው ተገልጿል።

- የዩኒቨርሲቲ አመራር ድክመት፣ አስተዳደራዊ እርምጃ አለመውሰድ፣ ዝቅተኛ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ፣ ተቀናጅቶ አለመስራት..ግጭቶች እንዲባባሱ እንዳደረገ ተገልጿል።

- ሚኒስቴሩ ችግሮችን ለመፍታት ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከ20 ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ምክክር ካደረገ በኃላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግል አመራር እንዲሰጡበት መደረጉ ተገልጿል። በዚህም ዩኒቨርሲቲዎች በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ፣ የግቢ አጠባበቅ በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ መመሪያ መተላለፉ ተገልጿል።

- 1,207 ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ ቅጣት ተላልፏል። 921 ተማሪዎች የተለያዩ ቅጣቶች ተወስኖባቸዋል ተብሏል።

- 421 ተማሪዎች ከ1 ዓመት አንስቶ ሙሉ በሙሉ እስከ ማባረር እርምጃ ተወስዷል።

- 140 ተማሪዎች እና መምህራን የተለያየ ቅጣት ተላልፎባቸዋል፤ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ እንደሚገኝ ተገልጿል።

More https://telegra.ph/FBC-01-30

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - ባልታወቁ ሰዎች የታገቱት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ጉዳይ የሚያጠራ የምርመራ ቡድን መቋቋሙ ተገልጧል። የምርመራ ቡድኑ ሦስት እንደኾነ ነው የተሰማው። - ተማሪዎቹ በታገቱበት አካባቢ የተደራጁ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱ መኾናቸውን በመግለጥ መንግስት እርምጃ እየወሰደ ነው። - የታጋቱት ተማሪዎች ሦስት ወላጆች ከሚኖሩበት ዞን ጽ/ቤቶች ተደውሎላቸው አዲስ አበባ ገብተዋል። - የጀርመን ድምፅ…
#UPDATE

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በቅርቡ ከታገቱት የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወላጆች ጋር ተወያዩ።

በውይይቱም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚልና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በተጨማሪ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተማሪዎቹ የትውልድ ቦታ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

የተማሪ ወላጆች በዚህ ወቅት የልጆቻቸው አድራሻ እስከጠፋበት ዕለት ድረስ የነበራቸው የስልክ ልውውጥ ምን እንደሚመስልም ጉዳዩን በሚመለከት የተቋቋመው ግብረ-ሃይልን ለሚመሩት ኃላፊዎች አብራርተዋል።

[ENA]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ሰሞኑን በመቐለ/ትግራይ የሚገኙ ሁሉም የኢ/ያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ገንዘብ ወጪ በሚያደርጉ ደንበኞች ባልተለመደ ሁኔታ ተጨናንቀዋል፡፡ በገንዘብ ኖት እጥረት ምክንያት ባንኩ ከ2ሺህ ብር በላይ ለደንበኞች ለመስጠት ተቸግሮ መቆየቱም ተገልፆል፡፡

[ጋዜጠኛ ሚሊዮን ኃይለስላሴ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሞጣ ድጋፍ ማሰባሰቢያ አካውንቶችን ይፋ አድርጓል፦ አካውንት ስም: በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሞጣ ድጋፍ ማሰባሰቢያ የሂሳብ ቁጥሮች 1/ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000315148457 ቀራንዮ ቅርንጫፍ 2/ ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1000054280428 አባነፍሶ ቅርንጫፍ 3/አዋሽ ባንክ 01304069690301…
ለሞጣ ሙስሊሞች የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገ ነው...

የማህበራዊ ሚዲያውን ዞር ዞር እያልን እየተመለከትን እንገኛለን፤ ከሰሞኑን ይፋ በተደረጉ የድጋፍ ማድረጊያ የባንክ አካውንቶች በርካታ ሰዎች ለሞጣ ሙስሊሞች ድጋፍ እያደረጉ እንደሆነ እየተመለከትን ነው። ይኸው የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ነገ ዓርብ በስፋት እንደሚቀጥልም ተረድተናል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

በኢትየጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ሲካሄድ የነበረው ውይይት ከምን ላይ እንደደረሰ ከተሳታፊዎቹ አልተሰማም።

የሶስቱ አገራት የውጪ ጉዳይ እና የውሃ ሚንስትሮች በዋሽንግተን ዲሲ ተገናኝተው የመከሩ ሲሆን፤ ቀድሞ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ሦስቱ አገራት የደረሱትን ስምምነት ትናንት ይፋ እንደሚያደርጉ ተጠብቆ ነበር።

ከሁለት ሳምንታት በፊት ሦስቱ አገራት እንዲሁም አሜሪካ እና የዓለም ባንክ በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ በሕዳሴው ግድብ ሙሊት እና ሌሎች መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት በሚያደርሱ ነጥቦች ላይ ተግባብተናል ብለው ነበር።

በአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ እንደሆነ በተነገረለት የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ አሞላል ዙሪያ የተፈጠረውን ልዩነት ለማጥበብ በተከታታይ ዋሽንግተንን ጨምሮ በሦስቱ አገራት መዲናዎች ሲካሄድ ቆይቷል።

የሦስቱ አገራት የውጪ ጉዳይና የውሃ ሚኒስትሮች ግድቡ ውሃ የሚሞላበትን እና ሥራ የሚያከናውነትን ሁኔታ ላይ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ ባለፉት ሁለት ቀናት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴርና በዓለም ባንክ በታዛቢነት በተገኙበት የቀረበው ረቂቅ የስምምነት ሰነድ እንደሚያመለክተው በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው ግድብ በዝናብ ወቅት በተለያዩ ደረጃዎች በውሃ እንዲሞላ የሚመክር ነው።

More https://telegra.ph/BBC-01-30

[BBC]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
CARD FoE and Legitimate Restrictions.pdf
1.2 MB
7ቱ የተዛቡ መረጃ ዓይነቶች!

1ኛ - ስላቅ ወይም ቀልድ (Satire or Parody) - እነዚህኞቹ አንባቢውን ለመጉዳት ወይም ለማሳሳት የተፈጠሩ ሳይሆን ለማስገረም፣ ለማዝናናት ወይም ባለታሪኩ ላይ ለማላገጥ የተዘጋጁ መረጃዎች ናቸው፤ ነገር ግን በተደራሲዎቹ እንደ እውነት ሊቆጠሩ ይችላሉ።

2ኛ - አሳሳች ይዘት (misleading content) - እነዚህኞቹ መረጃዎቹ ስህተት ባይሆኑም የቀረቡበት መንገድ ግን ተደራሲያኑን በማሳሳት ሌላ ነገር እንዲገምቱ ወይም እንዲያምኑ የሚያደርግ ነው።

3ኛ - የተፈበረከ ይዘት (fabricated content) - ጉዳት ለማስከተል በማሰብ ሙሉ ለሙሉ የተፈጠረ የሐሰት መረጃ።
4ኛ - ለምድ ለባሽ ይዘት (Imposter content) - መረጃው ከታማኝ ምንጭ ወይም ቢሮ የተገኘ ለማስመሰል የተደረገ ነገር ግን የተፈበረከ የሐሰት መረጃ።

5ኛ - የውሸት ግንኙነት (False connection) - ሁለት የማይገናኙ ነገሮችን (ፎቶ እና ታሪኩ፣ ርዕሱና ዝርዝሩ…) እንደሚገናኙ አስመስሎ ማቅረብ።

6ኛ - የውሸት ዐውድ (False context) - እውነተኛ ታሪኮችን እና ምስሎችን እየተጠቀሙ ነገር ግን ከአገባቡ ውጪ በመጥቀስ መረጃ ማዛባት።

7ኛ - አላግባብ የተተረጎመ ይዘት (manipulated content) - መረጃው ብዙ ተመልካች እንዲያገኝ ሲባል ብቻ አዛብቶ ማቅረብ።

[ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነትና ቅቡልነት ያላቸው ገደቦች]

#CARD
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot