TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አርባ ምንጭ🔝

ዘረኝነትን #እጠየፋለሁ፤ ከተማዬን አፀዳለሁ! #ETHIOPIA #ኢትዮጵያ #አርባምንጭ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech በአርባ ምንጭ ዛሬ!

በአርባምንጭ ዩንቨርስቲ የStopHateSpeech እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ለ3 ቀናት የሚቆይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች ተዘጋጅቷል።

ፕሮግራሞቹ፦

•ዛሬ ምሽት 12 ሠዓት #በኩልፎ_ካምፓስ
•ቦታ - Old Cafe

•ነገ ምሽት 12 ሠዓት #በአባያ_ካምፓስ
•ቦታ - የመመገቢያ ካፌ

•አርብ ከቀኑ 8 ሠዓት #በዋናው_ግቢ ሁሉም ካምፓስ የሚሳተፍበት የግቢው ማህበረሰብ የሚሳተፍበት እንዲሁም የአስተዳደር አካላት የሚሳተፉበት መድረክ
•ቦታ - በአዲሱ አዳራሽ

#TIKVAH_ETHIOPIA
#አርባምንጭ_ዩንቨርስቲ
#የአርባምንጭ_ዩኒቨርስቲ_ተማሪዎች_ህብረት
#ሰላም_ፎረም
#የተለያዩ_ክበባት

ማንም የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል እንዳይቀር!! ኑ ኢትዮጵያን በፍቅር እንገንባ!! ኢትዮጵያ ያንቺም፤ የሱም፤ የኔም የሁላችንም ናት!!

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech~በኩልፎ ካምፓስ👆

#በአርባምንጭ_ዩኒቨርሲቲ /ኩልፎ ካምፓስ/
የStop Hate Speech የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአሁን ሰዓት እየተካሄድ ይገኛል። #አርባምንጭ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech-ኩልፎ ካምፓስ👆

#በኩልፎ_ካምፓስ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ከTIKVAH-EHT ጋር በመተባበር ያዘጋጀው #የStopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። የStopHateSpeech አስተባባሪዎችን #ቴዎድሮስ_ዮሴፍ የተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለው ተቀብለዋል። በዝግጅቱ ላይ ዶ/ር #ይስሀቅ_ከቸሮ የኮሌጅ ዲን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ የተቋማቸው ተማሪዎች የሀገሪቱን #አንድነት ከሚሸረሽሩ ግለሰቦች ጋር #መታገል እንዳለባቸዉ እና በቀጣይም የሀገሪቱ እጣ ፈንታ #በወጣቶች ላይ መሆኑን አውቀው የሚዲያ አጠቃቀማቸውን እንዲያስተላካክሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ማስታወሻ🗓በነገው ዕለት #ተመሳሳይ መድረክ #በአባያ_ካምፓስ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል!! #አርባምንጭ_ዩንቨርስቲ

የአርባምንጭ ተማሪዎች ተቀላቀሉ👇 @tikvahethamu @tikvahethamu

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🎂TIKVAH ETHIOPIA~2 ዓመት🎂

#ደብረ_ብርሃን #ወሎ #ጅማ #ሀረማያ #ሀዋሳ #ወልቂጤ #መቐለ #ወልዲያ #ወላይታ_ሶዶ #አርባምንጭ #ሆሳዕና/#ዋቸሞ/

📎የሰውልጅ በሰውነቱ የሚከበርበት፤ የግለሰቦች አመለካከት፣ እምነት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ የኔ ነው የሚሉት ሁሉ የሚከበርበት፤ ፍቅር፣አንድነትና መተባበር የነገሰበት፣ የሰው ልጅ ሁሉ መሰብሰቢያ የሆነች ከጥላቻ የራቀች ሀገር እንገነባለን!! ተባብረን እንሰራለን፤ ለመጭው ትውልድ ኢትዮጵያን እናወርሳለን!!

እኛ ስንኖር ኢትዮጵያ ትኖራለች፤ ኢትዮጵያ ስትኖር እኛም እንኖራለን!

#ድፍን_ሁለት_ዓመት_በፍቅር_በመተባበር!

ነገ 6:00 አበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤ እና ልማት ድርጅት እንገናኝ፤ ከእናታችንም ምርቃት እንቀበል!! ሁላችሁም የዚህ ገፅ ባለቤቶች ናችሁ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሻሸመኔ
#ሀዋሳ
#ነቀምት
#አሰላ
#አዲስአበባ
#ሽሬ
#ደብረብርሃን
#ወላይታሶዶ
#አርባምንጭ
#ጅግጅጋ
#አዳማ
#ድሬዳዋ
#ባህርዳር
#መቐለ
#ሀረር
#ጎንደር

ከሌሎች በርካታ ከተሞች ከሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች የSAT ውጤት ያልጠበቁት እንደሆነ በመግለፅ ቅሬታቸው እያሰሙ ይገኛሉ። የሚመለከተው አካል ማብራሪያ እንዲሰጥበትም ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸በ2011 #አርባምንጭ ከቱሪስት ፍሰት ከ82 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘቷን ሸገር ራድዮ ዘግቧል። #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የTIKVAH-ETH #የStopHateSpeech ሀገር አቀፍ ዘመቻዎች/በዩኒቨርሲቲ ደረጃ/ና በየተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ የተደረጉ ጉብኝቶችን ለመከታተል #የዩትዩብ ቻናላችንን ይጎብኙ!

#ሀረማያ #ጅማ #ወልቂጤ #ሀዋሳ #ወላይታ_ሶዶ #አርባምንጭ #መቐለ #ዋቻሞ #ወሎ #ደብረብርሃን #ወልዲያ

Watch ""የአንድ እናት ልጆች ነን" በመቐለ ዩኒቨርሲቲ #TIKVAH_ETHIOPIA" on YouTube
https://youtu.be/qjyt56okb3U
#አርባምንጭ

የደቡብ ብ/ብ/ክ/መ ምክትል ርዕሰ መስተደድር አቶ ርዕስቱ ይርዳው፣ የመከላከያ ሚኒስተር ደኤታ አምባሳደር ሌላዓለም ገ/ዮሐንስ፣ የቀድሞ ቀዳማዊትእመቤት ሮማን ተስፋዬ እና የጋሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በዮ ጋሞ ማስቃላ በዓል ላይተገኝተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አርባምንጭ

በወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ #ዳጋቶ_ኩምቤ የተመራ ከፍተኛ አመራር በጋሞ "ዩ-ማስቃላ" ክብረ-በዓል ላይ ለመታደም አርባ ምንጭ ከተማ ገብቷል፡፡ አመራሮቹ አርባ ምንጭ ሲገቡ የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ ደማቅ አቀባበል አደርገውላቸዋል፡፡ የሁለቱም ዞን አስተዳዳሪዎች የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ የተገለፀ ሲሆን በህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ዙሪያ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡ የጋሞ ዞን አቻቸው በተመሣሣይ በወላይታ የጊፋታ በዓል ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

Via #GMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ

ቲክቫህ ኢትዮጵየ ከፒስ ሞዴል እና ከጋሞ ዞን አስተዳደር ጋር በመተባበር "ኡቡንቱ" በሚል ርዕስ ያዘጋጀው የአንድ ሳምንት የግንዛቤ ማስጨበጫ ከዛሬ ጀምሮ መካሄድ ይጀምራል። በተለያዩ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ከጋሞ አባቶች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን አብሮ ስለመኖር፣ ስለመከባበር፣ የአንዱ ለአንዱ የመኖር ዋስትና ስለመሆኑ የተለያዩ መልዕክቶች ይተላለፋሉ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ኡቡንቱ - 'እኔ ነኝ ምክንያቱም እኛ ነን'

ቲክቫህ ቤተሰቦች - አርባ ምንጭ❤️

ኡቡንቱ - እኛ አንድ ሰብዓዊ ቤተሰብ መሆናችን ላይ የተመሠረተ የአፍሪካ ጥንታዊ ፍልስፍና ነው። እኛ ወንድምና እህት ነን። እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን፡፡ አንድ ሰው የሚበላው ሲያጣ ሁሉም ሰዎች በዚህ ረሃብ ይሰቃያሉ። አንዱ ሲበደል ሁላችንም ህመሙን ይሰማናል፡፡ አንድ ልጅ በሚሰቃይበት ጊዜ እንባዎች በሁሉም ሰው ጉንጮዎች ላይ ይፈስሳሉ፡፡ የእኛን ተቀዳሚ ሰብአዊነት በመገንዘብ፣ እኛን አንድ የሚያደርግ ጠንካራ ትስስር፣ የሰው ልጆችን በሙሉ የሚያስተሳስር የማይጠፋ ቦንድ ነው።

#Ubuntu #ኡቡንቱ #አርባምንጭ #Day2

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ጋሞዞን #ፒስሞዴል

(AFRIKHPRI FOUNDATION)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Day2 #Ubuntu #ኡቡንቱ #አርባምንጭ

በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከናወነ ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል፦ የሃሳቡ ደጋፊዎች፣ ተካፋዮች ፣ አስተባባሪዎች የሆኑ እጅግ የምናከብራቸው የሀገራችን ወጣቶች በተለያዩ የከተማው ክፍሎች በመዘዋወር ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ብሮሸሮችን በመበተንና ስለ ዓላማው በማስረዳት ስራቸውን ሲሰሩ ውለዋል። ለአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎችና ለአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልዩ ምስጋናችንን እናቀርባለን!

ነገ የ3ኛው ቀን ስራ ይቀጥላል!

ሃሳብ፣ መልዕክት የላችሁ፣ አስተያየት መስጠት የምትፈልጉ ልታግዙን የምትፈልጉ የቤተሰባችን አባላት ካላችሁ እነዚህ አድራሻዎች ተጠቀሙ፦ @tikvahethiopiaBot @tsegabwolde 0919743630

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል
#Day3 #አርባምንጭ #ኡቡንቱ

ዛሬ በአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርኃግብር እጅግ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።

"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"

"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"


ለሁሉም አካላት ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን!

#TIKVAH_FAMILY

#ፒስሞዴል #ቲክቫህኢትዮጵያ

#ጋሞዞን #አርባምንጭፖሊቴክኒክኮሌጅ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Day3 #አርባምንጭ #ዊዝደምአካዳሚ

"የነገ ተስፋችሁ እኛነንና ፍቅርን አስተምሩን"

ዛሬ ከሰዓት በኃላ በነበረን መርኃግብር "በዊዝደም አካዳሚ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት" ተማሪዎች ጋር ጥሩ ጊዜ አሳልፈናል። ተማሪዎቹ ልዩ ልዩ የባህል ፕሮግራሞችን አዘጋጅተው የጠበቁን ሲሆን በህጻናት ግጥሞች ቀርበዋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ አባቶች ተገኝተው ልጆቹን የመረቁ ሲሆን የአርባ ምንጭ የህክምና ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ለተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል #ጋሞዞን

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት

የ"ኡቡንቱ አርባ ምንጭ" የማጠቃለያ መርሃ ግብር በአሁን ሰዓት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተገኙበት በሃይሌ ሪዞርት እየተካሄደ ይገኛል።

"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"

"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"

ዝርዝር መረጀዎች ይኖሩናል!

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል #ጋሞዞን

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት የ"ኡቡንቱ አርባ ምንጭ" የማጠቃለያ መርሃ ግብር በአሁን ሰዓት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተገኙበት በሃይሌ ሪዞርት እየተካሄደ ይገኛል። "በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!" "እኛ ወንድምና…
#አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት #ቲክቫህ #ፒስሞዴል

የኡቡንቱ የማጠቃለያ ፕሮግራም በሀገራችን ብሔራዊ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን የጋሞ ዞን አስተዳደር ተወካይ አቶ እሸቱ አልቶ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

በዚሁ ንግግራቸው ወቅት የዝግጅቱ አስተባባሪዎች በሙሉ ወጣቶች መሆናቸው መርኃግብሩን ለየት እንደሚያደርገው ገልፀዋል፡፡ አቶ እሸቱ አክለውም 500,000 ቤተሰቦችን ስለ ፍቅር እና አንድነት ብቻ እየሰበከ ላሰባሰበን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ቀጥሎም የኃይማኖት አባቶች፣የጋሞ አባቶች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ በተለይ ለወጣቱ ባስተላለፉት መልዕክት፦ እርስ በእርስ መከባበር እና ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን ማስቀደም እንደሚገባ አበክረው ገልፀዋል፡፡

አሁን "ስለ እርቅ ለመወያየትና ለማስታረቅ እድሜ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?" በሚል ርዕስ ወጣቱም ስለ ዕርቅ፣ ስለ ሰላም የበኩሉን እንዲወጣ በፈጣሪ አሰፋ አማካኝነት ምክክር እየተደረገ ይገኛል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ቲክቫህ #ፒስሞዴል

በዛሬው የውይይት ዝግጅት ላይ በስፋት ከተነሱት ሀሳቦች መካከል ሰው በሰውነቱ፡ብቻ ሊከበር እንደሚገባውና ሰላምን የሚያስቀድም ትውልድ ለመገንባት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ በውይይቱ የተሳተፉ ወጣቶች ደግሞ የጋሞ አባቶች ሰላም ወዳድነት ከአንድም ሁለት ጊዜ በተግባር የተገለጠ መሆኑን ጠቅሰው እንዲህ በአንድ መድረክ ስለ ሰላም አብረው መምከራቸው ትልቅ ትምህርት እንደሚሰጣቸው አንስተዋል፡፡ በአጠቃላይ ከውይይቱ በኀላ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው ስለ ሁሉም ሰው ልጆች ክብር የድርሻቸውን ለመወጣትና ይህን ለማድረግ እድሜ እንደማይገድበው በማመን የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት ሁሉ ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዛሬው መርኃ ግብራችን ላይ ታዳጊ ህጻናት እንዲህ በማለት መልዕክታቸውን አቅርበዋል፡-

"እኛ ህጻናት የእናንተው ልጆች ነን ለሀገራችንም ተምረን ተስፋ የምንሆናት ትውልዶች እኛ ነን፡፡ በፍቅር አድገን ወላጆቻችንንና ሀገራችንን ማገዝ እንመኛለን፡፡"

"እኛ ህጻናት ፍቅር ያስፈልገናል፡፡ የወደፊት የሀገራችን ተስፋዎች እኛ ነንና ታላላቆቻችን ፍቅር ልታስተምሩን ይገባል"

"መልካምነትን የምንማረው ከታላላቆቻችን ነውና እባካችሁ መልካምነትን በተግባር አስተምሩን"

"አባቶቻችን ትላንት እርጥብ ሳር ይዘው ለሰው ልጅ እንዴት ክብር መስጠት እንዳለብን አስተምረውናልና እኛ ህጻናት ከልባችን እናመሰግናቸዋለን"

ይህንን መልዕክት በኮልታፋ አንደበታቸው ካቀረቡ በኀላ በትህትና ዝቅ ብለው የአባቶችን ጉልበት ስመዋል አባቶችም ህጻናቱን መርቀው የሰላም ምልክት የሆነውን ነጭ ባንዲራ አበርክተውላቸው ልጆቻቸው በሰላም እንዲኖሩ በሙሉ አቅማቸው ለሰው ልጅ ክብርና ለሰላም እንደሚተጉ ቃል ገብተውላቸዋል፡፡

#ጋሞዞን #አርባምንጭ #ቲክቫህ #ፒስሞዴል #ሃይሌሪዞርት

@tikvahethiopia @tsegabwolde