TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ካርቱም ሊያቀኑ ነው። የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል አብድል ፋታ አል ቡርሃን ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራ የኤርትራ ልኡካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ሱዳን ይገባል ተብሏል። ፕትሬዚዳንት ኢሳያስ በቆይታቸው የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች እንዲሁም ባለፉት አመታት የነበረውን መልካም ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ፕሬዚዳንቱ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው እና የደህንነት አማካሪያቸው ጋር በዛሬው ዕለት ሱዳን ካርቱም ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል አብድል ፋታ አል ቡርሃን በቅርቡ በኤርትራ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ምንጭ ፦የሱዳን ዜና አገልግሎት/ebc/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥቆማ በአንዳድ የሀገሪቱ ከተሞች የ10ኛ ክፍል የብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት እደተቸገሩ እየገለፁ ይገኛሉ። የሚመለከተው አካል ችግሩን እንዲፈታም ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ዕውቀት እና ሃሳብ ያላቸውን ሰዎች ንድፍ ወደተግባር እንዲቀይሩ በማድረግ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራን መሰረት ያደረጉ ሁለት ሺ አነስተኛ ተቋማት ሊያቋቋቁም መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አስታወቁ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጀማል በከር በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ሁለት ሺ አነስተኛ የሳይንስና ፈጠራ ንግድ እና አገልግሎት ተቋማትን በማቋቋም እና ድጋፍ ይደረጋል።

በስራቸውም 20 ሺ ሰዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ ለማድረግ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በሚኒስቴሩ ተጀምሯል። እንደ አቶ ጀማል ገለጻ፤በተለይ በተንቀሳቃሽ ስልክ እና በኮምፒውተር በመተግበሪያዎች፣ በሮቦት እና ሌሎች ፈጠራ ስራዎች እንዲሁም በማምረቻ እና አገልግሎት ዘርፉ ውስጥ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ችግር ፈቺ ንግድ ለሚጀምሩ ሰዎች የገንዘብ ድጋፍም ይደረጋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዚምቧብዌ የቀድሞ ፕሬዝዳንቷን ሥርዓተ ቀብር ከመፈፀሟ በፊት፤ ሮበርት ሙጋቤን ለመሰናበት የአፍሪካ መሪዎች በዋና ከተማዋ ሐራሬ ይሰባሰባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የደቡብ አፍሪካው ሲሪል ራማፎሳን ጨምሮ በርካታ በስልጣን ላዩ ያሉና የቀድሞ የአፍሪካ ርዕሰ ብሄሮችም በስንብቱ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መፍትሄ ያልተገኘለት የቴፒ ጉዳይ...

"እንደምታውቀው አመት ያለፈው የቴፒ ውጥረት እስካሁን መፍትሄ አላገኘም። በግጭቱ ሳቢያ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ይኸው በአንድ አዳራሽ ውስጥ ተጠልለው ስምንት ወር አለፋቸው። ይህ ሁሉ ሲሆን አንድም የመንግስት አካል ሌላው ቀርቶ ሰብዓዊ እርዳታ እንኳን አላደረገላቸውም። በዚሁ ከቀጠለ የቡና ምርት ወቅት ስለደረሰ ተፈናቃዮቹ ወደቀያቸው ካልተመለሱ ሌላ ቀውስ መፈጠሩ አይቀሬ ነው።...የሚያሳዝነው ነገር ግጭቱ ከጀመረ አንስቶ ከቀን ቀን እየጨመረ የመጣውና እስከ ሰው ህይወት መጥፋት የተደረሰ የዝርፊያ ተግባር ነው። መጠኑ ይለያይ እንጂ አንድም ቀን የተኩስ ድምፅ ሳይሰማ ቀርቶ አያውቅም። ሰው ይሞታል፤ ንብረት ይዘረፋል።...አሁንም ቢሆን መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ነገሮች ካልተስተካከሉ ግጭቱ እንዳዲስ አገርሽቶ ሌላ ጥፋት እንዳያስከትል ስጋቴ ነው።" ከቴፒ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለማሳያነት⬆️

በሻኪሶ፣ በማጀቴ፣ እንዲሁም በምዕራብ ወለጋ ከተሞችና በሌሎችም አካባቢዎች የብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪ ወላጆች የልጆቻቸውን ውጤት ማየት እንዳልቻሉ እየገለፁልን ይገኛሉ። ከትላንት ጀምረው ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም ከድረገፁ የሚያገኙት መልስ "undefined" የሚል ነው።

•እኛም ይህንኑ የተለያዩ የመፈተኛ ቁጥሮችን በማስገባት አረጋግጠናል። ይህን መልእክት የምታነቡ የሚመለከታችሁ የስራ ኃላፊዎች ችግሩን ለይታችሁ #መፍትሄ ትፈልጉ ዘንድ በወላጆች ስም ጥሪ እናቀርባለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በ2011 በጀት ዓመት ብቻ 186 እና እስካሁን ደግሞ የ2011ዱንም ጨምሮ በጠቅላላው 425 አምቡላንሶች በላይ ተሰራጭተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ቢሆኑም ችግሮች እየተስተዋሉባቸው ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-14-3
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር!

በአዲሱ ዓመት በዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ መማር ማስተማርን እውን ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ዩኒቨርሲቲዎች የ2011 የትምህርት ዘመንን በአስቸጋሪ ሁኔታ ማሳለፋቸውን ነው  ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ የተናግረዋል። ተማሪዎች በሀሳብ ልዕልና በመከራከር መተማመን ሲችሉ ከውጭ የሚነሱ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን ምክንያት በማድረግ ትምህርታቸውን ማስተጓጎል፣ በቡድን መደባደብና መገዳደል አሳዛኝ ክስተት ነበርም ብለዋል።

“በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ታሪክ እንደ 2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ብዙ ልጆቻችንን ያጣንበት ዓመት ታይቶ አይታወቅም” ያሉት ፕሮፌሰር አፈወርቅ፤ ከዚህ በመማርም ከሁሉም የክልል አመራሮችና ከዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢዎች ጋር በ2012 የትምህርት ዘመን ሊወሰዱ በሚገቡ #ጥንቃቄዎች ላይ ውይይት መደረጉን ገልፀዋል። በዚህም እያንዳንዱ ወላጅ፣ ተማሪ፣ በየደረጃው ያለ አስተዳደር ለሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል ነው ያሉት።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-14-4
ኢዜማ ነገ በመቐለ ህዝባዊ ስብሰባ ያደርጋል!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የ2012 ዓ.ም የመጀመሪያ ህዝባዊ ስብሰባውን ነገ መስከረም 4 ቀን 2012 ዓ.ም በመቐለ ያካሂዳል፡፡ ህዝባዊ ስብሰባውን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋና የፓርቲው ም/መሪ አንዱዓለም አራጌ የሚመሩት ሲሆን ስብሰባውም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በመቐሌ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ እንደሚካሄድ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ናትናኤል ፈለቀ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ የፓርቲውን አላማና ግብ፣ ፕሮግራሙንና አጀንዳውን በስፋት ለህዝብ እንደሚያስተዋውቅ የገለፁት አቶ ናትናኤል፤ ከህዝቡ ለሚነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ይሰጥበታል ብለዋል፡፡ ኢዜማ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የተመረጡ ከተሞች ተመሳሳይ ህዝባዊ ስብሰባዎችን በተከታታይ እንደሚያደርግም ተገልጿል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BAHIRDAR

የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት በየአጥቢያዎቹ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ጸሎተ ምህላ አወጀ፡፡ ሀገረ ስብከቱ ለመስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ከፊታችን ሰኞ መስከረም 5 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ጸሎተ ምህላ አውጇል፤ ለመስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም ደግሞ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ ሀገረ ስብከቱ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመላከተው የፀሎተ ምህላው ዓላማ በቤተ ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ የሚደርሰውን መከራ፣ ግፍ እና መሰደድ አስመልክታ ለፈጣሪዋ መልዕክት ለማቅረብ ነው፡፡

ከጸሎተ ምህላው እና ከሰልፉ በኋላ በእለቱ 10፡00 ሰዓት ላይ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ስለወቅታዊው የቤተ ክርስቲያን ጥያቄ ውይይት ይደረጋል ተብሏል በመግለጫው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀዋሳ ከተማ የሚኖሩ የአለታ ወንዶ የመረዳጅ #ዕድር አባላት በአለታ ወንዶ ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ800 ሺህ ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

Via #SRTA
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
ፎቶ📸በእድሳት ምክንያት ላለፉት ሁለት ዓመታት አገልግሎት ሳይሰጥ የቆየው የአበበ ቢቂላ ስታዲዮም አሁን ላይ ዕድሳቱ ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቁ ስራ እንደሚጀምር ተገለጸ። በተያዘው አዲስ ዓመት የውድድር ዘመን እስከሚጀመርበት ጊዜ ድረስ ስታዲዮሙ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተብሏል። የአበበ ቢቂላ ስታዲዮም በ1995 ዓ .ም ስራ ጀመረ ይሁን እንጂ ደረጃውን የጠበቀ አልነበረም። አሁን ላይ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከፍተኛ በጀት በመመደብ ለስታዲዮሙ ሙሉ እድሳት አድርጓል።

Via #EPA

ስፖርታዊ ጉዳዮችን👇
https://publielectoral.lat/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
‹‹ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኢሬቻ በዓል ላይ እንዲገኝ ጥሪ አስተላልፋለሁ››

/የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ም/ርዕሰ መስተዳድር፤ ሽመልስ አብዲሳ/

የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ #እድል አግኝቷል፤ ይሄን እድል በአግባቡ ካልተጠቀመ ትልቅ ኪሳራ ነው የሚሆነው። አገሪቱ ከፍተኛ ችግር ላይ ትወድቃለች።

ብዙ አገሮች እንደዚህ አይነት እድሎችን ባለመጠቀማቸው፣ የለውጥ እቅድ ተጨናግፎ፣ ብዙ ጥፋቶች ደርሰዋል፡፡ አገራቸው የማትወጣበት ማጥ ውስጥ ተዘፍቃ ኑሮ መከራ የሆነባቸው ብዙ አገሮችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

በአገራችንም ብዙ ለውጦች ከሽፈዋል፡፡ አሁን ያገኘነው ለውጥ ግን ከፍተኛ ውጤት የተገኘበት ነው። ወደ ኋላ አንድ አመት ተኩል ተመልሰን ብናስታውስ፤ አስገራሚ የሆነ ለውጥ ተካሄዷል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለውጡን ማስቀጠል ይገባዋል።

ሁላችንም፤ መንግስትም ሕዝብም ተባብረን በአንድ ላይ ይሄንን ለውጥ ማስቀጠል ከቻልን፣ የምንናፍቃትን ኢትዮጵያን እንፈጥራታለን፡፡ ሁሉንም እኩል የምታከብር፣ ብሔር ብሔረሰብ እኩል የሚከበርባት፣ ሁሉም የሚተሳሰብባት፣ ወንድማማችነት የሚጠነክርባት አገር መፍጠር እንችላለን፡፡

እኔን እንቅልፍ የሚነሳኝ ይሄንን እድል እየተጠቀምንበት ነው አይደለም? በየቀኑ ለውጡን የሚያስቀጥል ሥራ እያከናወንን ነው አይደለም? የሚለው ነው፡፡ ተግዳሮቶችን በትዕግስትና ከስሜት በፀዳ አስተሳሰብ እየተጋፈጥን ከሄድን፣ ነገሮች በፍጥነት ይቀየራሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-14-5
#update የራያ ቆቦ ወረዳ አስተዳደርና ፀጥታ ፅ/ቤት ከቀበሌ አመራሮች፣ ከፀጥታ ሀይሎችና አጋር አካላት በተገኙበት የ2011 ዓ.ም ተግባራት አፈፃፀም ግምገማና የ2012 ዓ.ም የእቅድ ትውውቅ በፀጥታ ተቋማት አዘጋጅነት በቆቦ ከተማ እየተካሄደ ነው።

Via እስክንድር ሞላ ከራያ ቆቦ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BREAKING የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ9/11 ጥቃት /ማስተር ማይንድ/ እና የአልቃይዳ መሪ የነበረው ኦሳማ ቢላደን ልጅ #ሀምዛ_ቢላደን መገደሉን አረጋገጡ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
27 ሚሊዮን ብር የሚገመት አደንዛዥ ዕፅ ወደ አገር ውስጥ ሊገባ ሲል ተያዘ!

የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን በቦሌ አለም አቀፍ አየርመንገድ በኩል ወደ አገር ሊገባ የነበረ 27 ሚሊዮን ብር የሚገመት 10.8 ኪ.ግ የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

የጉምሩክ ተቆጣጣሪዎች ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ስር ያዋሉት #ሄሮይን እና #ኮኬን የተባሉ አደንዛዥ እፆችን ነው፡፡ አደንዛዥ እፆቹን አንድ ናይጄሪያዊ ዜጋ በያዘው ቀላል ሻንጣ ውስጥ ደብቆ ለማለፍ ሲሞክር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ የቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ተገኔ ደረሰ ለኢቢሲ ገልፀዋል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁላችሁም ድምፅ እድትሰጡ ጥሪ እናቀርባለን!!

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአለም ከሚታወቁ ምርጥ 20 ውድድሮች ውስጥ አንዱ በመሆን እጩ ሆኖ ቀርቧል!

ይህን ውድድር ለማሸነፍ የተሳታፊዎች ድምፅ እየተሰበሰበ ይገኛል፡፡ ድምፅ መስጠቱ ነገ ስለሚያበቃ እርሶም የበኩልዎን ያድርጉ! ድምፅ ለመስጠት ይህንን ሊንክ ይከተሉ

https://www.letsdothis.com/challengeawards/best-international/run-international
የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት "ለታላቁ የኢትዮጵያ ሩጫ" ድምፅ በመስጠት ኃላፊነታችንን እንወጣ!

•ይህንን ውድድር ማሸነፋችን ለሀገራችንን ትልልቅ እድሎችን ይዞ ይመጣል!

The link for the vote is⬇️
https://www.letsdothis.com/challengeawards/best-international/run-international
የቤተሰባችን አባላት በድምፅ መስጠቱ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ። ሁላችንም በዚህ መልክ ድምፅ በመስጠት ሀገራችንን በዓለም መድረክ እናስተዋውቅ!!

The link for the vote is⬇️
https://www.letsdothis.com/challengeawards/best-international/run-international
#VOTE ሁላችሁም ድምፃችሁን በመስጠት "ታላቁ ሩጫን እናስመርጥ" ኢትዮጵያንም በዓለም መድረክ እናስተዋውቅ!!

The link for the vote is⬇️
https://www.letsdothis.com/challengeawards/best-international/run-international
39℅👍ድምፅ መስጠታችሁን ቀጥሉ!!

The link for the vote is⬇️
https://www.letsdothis.com/challengeawards/best-international/run-international