መፍትሄ ያልተገኘለት የቴፒ ጉዳይ...

"እንደምታውቀው አመት ያለፈው የቴፒ ውጥረት እስካሁን መፍትሄ አላገኘም። በግጭቱ ሳቢያ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ይኸው በአንድ አዳራሽ ውስጥ ተጠልለው ስምንት ወር አለፋቸው። ይህ ሁሉ ሲሆን አንድም የመንግስት አካል ሌላው ቀርቶ ሰብዓዊ እርዳታ እንኳን አላደረገላቸውም። በዚሁ ከቀጠለ የቡና ምርት ወቅት ስለደረሰ ተፈናቃዮቹ ወደቀያቸው ካልተመለሱ ሌላ ቀውስ መፈጠሩ አይቀሬ ነው።...የሚያሳዝነው ነገር ግጭቱ ከጀመረ አንስቶ ከቀን ቀን እየጨመረ የመጣውና እስከ ሰው ህይወት መጥፋት የተደረሰ የዝርፊያ ተግባር ነው። መጠኑ ይለያይ እንጂ አንድም ቀን የተኩስ ድምፅ ሳይሰማ ቀርቶ አያውቅም። ሰው ይሞታል፤ ንብረት ይዘረፋል።...አሁንም ቢሆን መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ነገሮች ካልተስተካከሉ ግጭቱ እንዳዲስ አገርሽቶ ሌላ ጥፋት እንዳያስከትል ስጋቴ ነው።" ከቴፒ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ

@tsegabwolde @tikvahethiopia