TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር!

በአዲሱ ዓመት በዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ መማር ማስተማርን እውን ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ዩኒቨርሲቲዎች የ2011 የትምህርት ዘመንን በአስቸጋሪ ሁኔታ ማሳለፋቸውን ነው  ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ የተናግረዋል። ተማሪዎች በሀሳብ ልዕልና በመከራከር መተማመን ሲችሉ ከውጭ የሚነሱ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን ምክንያት በማድረግ ትምህርታቸውን ማስተጓጎል፣ በቡድን መደባደብና መገዳደል አሳዛኝ ክስተት ነበርም ብለዋል።

“በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ታሪክ እንደ 2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ብዙ ልጆቻችንን ያጣንበት ዓመት ታይቶ አይታወቅም” ያሉት ፕሮፌሰር አፈወርቅ፤ ከዚህ በመማርም ከሁሉም የክልል አመራሮችና ከዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢዎች ጋር በ2012 የትምህርት ዘመን ሊወሰዱ በሚገቡ #ጥንቃቄዎች ላይ ውይይት መደረጉን ገልፀዋል። በዚህም እያንዳንዱ ወላጅ፣ ተማሪ፣ በየደረጃው ያለ አስተዳደር ለሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል ነው ያሉት።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-14-4