TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በውጭ ሀገር የሚገኙ #ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የዕውቅና ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡ የዕውቅና ሽልማቱ የተበረከተላቸው ለመገናኛ ብዙኃንና ለኪነ ጥበብ ነፃነት መከበር ላበረከቱት አስተዋጽኦ መሆኑ ታውቋል፡፡ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ‹‹የሚገባቸውን ጥቂቶች በማበረታታት ብዙዎችን ማትጋት ይቻላል›› ብለዋል፡፡ የዕውቅና ሽልማቱ የተሰጠውም አምባሳደር ፍጹም በተገኙበት እንደሆነ ታውቋል፡፡

Via #AMMA
🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታግተዋል!

45 #ኢትዮጵያውያን#ኤርትራውያን እና #ሶማሊያውያን ስደተኞች በሊቢያ ናስማ በተባለ ቦታ በሕገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪ ታግተው እንደሚገኙ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል። ከታገቱ አንዱ «በተዘጋ ቤት ውስጥ ነው ያለንው። በጣም መጥፎ ሁኔታ ላይ ነው ያለንው» ብሏል። ስደተኞቹ እንደሚሉት የሜድትራኒያን ባሕርን በማቋረጥ አውሮፓ ለመግባት ጉዞ የጀመሩት በአንድ ኤርትራዊ የሰው አሸጋጋሪ አማካኝነት ነበር።

ኤርትራዊው ለሊቢያዊ አስረክቧቸው መጥፋቱንም ይገልፃሉ፤ ከ45 ስደተኞች 7ቱ ሴቶች 38 ወንዶች ናቸው። አንዲት ኢትዮጵያዊት «ባሕር ልሻገር ብዬ ነው የመጣሁት። 6100 ዶላር ክፈይ ተብዬ ከፍያለሁ። ከዚያ በኋላ ስልኩን አጥፍቶ ለሊቢያዊ ትቶን ሔደ። ሊቢያዊው ደግሞ 3500 ዶላር ጨምሩና ከዚህ ቤት ላስወጣችሁ ብሎናል፤ አሁን አቅሙም ያለው ሰው የለም» ብላለች።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኡጋንዳ

የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ሚንስትሮች #በኡጋንዳ ከሚኖሩ #ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ በኡጋንዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ሚንስትሮቹ ከኢትዮጵያዊያኑ ጋር የተወያዩት በሀገሪቱ እየተካሄደ ባለው ለውጥ ዙሪያ ነው ተብሏል፡፡ ውይይቱ ከ3ኛው የኢትዮ ኡጋንዳ የሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሄደ ነው።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በደቡብ አፍሪካ እስካሁን በትንሹ 10 ኢትዮጵያውያን ሞተዋል!

በደቡብ አፍሪካ እስካሁን ከ10 የማያንሱ #ኢትዮጵያውያን በኮቪድ-19 መሞታቸውን በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ፀሃፊ አቶ ፋኖስ ሃይሌ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ጁሃንስበርግ ፣ ሊንፖፖ፣ ማፑማላንጋ እንዲሁም ዌስተርን ኬፕ ኢትዮጵያውያን ከሞቱባቸው አካባቢዎች ይጠቀሳሉ።

አስክሬናቸውን ወደ ሀገር ቤት መላክ ስለማይፈቅድ የሁሉም ቀብር ስነስርዓት በዛው በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተፈፅሟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት፤ ጅዳ #ለኢትዮጵያውያን የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል። ለፅ/ቤቱ ከትላንት ምሽት ጀምሮ እየደረሱ ባሉት መረጃዎች መሠረት የሳዑዲ የፀጥታ አስጠባቂ አካላት ፦ - በጄዳ ፣ - መዲና ፣ - ጂዛን እና መካ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ዜጎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት ጉዳዩ እስኪጣራ ኢትዮጵያውያን…
#Update #SaudiArabia #Attention

"...የአካል ወይም ንብረት ጉዳት የደረሰባችሁ ዜጎች ያላችሁን ማስረጃ በመያዝ ለቆንስላ ጽ\ቤቱ ማቅረብ ትችላላችሁ" - በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ

የሳዑዲ ዓረቢያ የፀጥታ ኃይሎች በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ተከትሎ ዜጎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ማስተላለፉ ይታወቃል።

በዚህ ሂደት በተለይ ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ኖሯቸው በህግ አስከባሪ አካላት ከመጠን ያለፈ ኃይል አጠቃቀም ምክንያት የአካል ወይም የንብረት ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ያላቸውን ማስረጃ በመያዝ ለቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

አሁንም #ኢትዮጵያውያን ተገቢውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዲቀጥሉ የቆንስላ ጽ\ቤቱ በድጋሚ የጥንቃቄ መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ዛሬ ማምሻውን የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መግለጫ ከምርጫ በኋላ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያን የወደፊት አካሔድ ለመወሰን እና የአገሪቱን ዴሞክራሲ እና ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከር ጠ/ ሚ ዐቢይ አህመድ የሚመሩት መንግሥት እና መላ ኢትዮጵያውያን ከምርጫ በኋላ ለሚካሔድ አካታች የፖለቲካ ብሔራዊ ውይይት ቁርጠኛ እንዲሆኑ ነው የባይደን አስተሳደር ጥሪ ያቀረበው።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሚመሩት የአሜሪካ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለሠራተኞቹ ጥረቶች እውቅና ቢሰጥም ፤ 6ኛው አገራዊ ምርጫ የሚካሔድበት ከባቢ “አሳሳቢ ነው” ብሏል። 

የአሜሪካ መንግስትን አቋም የሚያንጸባርቀው መግለጫ ዛሬ ማምሻውን አንቶኒ ብሊንከን በሚመሩት የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በኩል ነው የወጣው።

የባይደን አስተዳደር የኢትዮጵያ ምርጫ አሉበት ያላቸው ፈተናዎች ፦
- የተቃዋሚ ፖለቲከኞች እስር፣
- የገለልተኛ ሚዲያ መዋከብ፣
- የአካባቢያዊ እና ክልላዊ መንግሥታት ወገንተኝነት እንዲሁም በመላ ኢትዮጵያ በብሔሮች እና በማህበረሰቦች መካከል የተቀሰቀሱ ግጭቶች ለነፃ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንቅፋት ናቸው ብሏል።

"በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች በክልሎች እና ብሔሮች መካከል ያለው ልዩነት መካረር የአገሪቱን አንድነት እና የግዛት ሉዓላዊነት ያሰጋል” ያለው የአሜሪካ መንግስት #ከምርጫው_በኋላ መፍትሔ ሊፈለግ እንደሚገባ አሳስቧል።

የአሜሪካ መንግስት ፥ “ከምርጫው በኋላ ያለው ጊዜ #ኢትዮጵያውያን ተባብረው እነዚህን ልዩነቶች ለመጋፈጥ ኹነኛ ወቅት ነው” ብሏል።

የአሜሪካ መግለጫ : www.state.gov/elections-in-ethiopia/

#EthiopiaInsider #SpokespersonNedPrice #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #SaudiArabia #Attention "...የአካል ወይም ንብረት ጉዳት የደረሰባችሁ ዜጎች ያላችሁን ማስረጃ በመያዝ ለቆንስላ ጽ\ቤቱ ማቅረብ ትችላላችሁ" - በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ የሳዑዲ ዓረቢያ የፀጥታ ኃይሎች በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ተከትሎ ዜጎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ…
#Update

በሳዑዲ ዓረቢያ የህግ አስከባሪ አካላት ተይዘው የነበሩ ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ከእስር እንዲፈቱ መደረጉ ተገፀ።

የሳዑዲ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነ እና ዜጎችም ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ መሰራጨቱ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ ከተለያዩ ከተሞች በህግ አስከባሪ አካላት የተያዙ የነበሩና ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ያላቸው ከጅዳና መካ ከተሞች ከአርባ በላይ ኢትዮጵያውያን ከጂዛን ዘጠና አራት ከመዲና ስድስት መቶ እንዲሁም ከአብሃ ሰላሳ ስምንት ኢትዮጵያውያን የበጅዳ የሚገኘድ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ\ቤቱ ባደረገው ክትትል እንዲፈቱ መደረጉ ተነግሯል።

ጉዳዩን አስመልክቶም የቆንስላ ጽ\ቤቱ ከሚመለከታቸው የሳዑዲ መንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በቅርበት እየተነጋገረ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን በተለይ በህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ አማካኝነት ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርስ ማንኛውም የማዋከብና እንግልት ምክንያት እንዲገለፅለትና ይሄው በአስቸኳይ እንዲቆም የቆንስላ ጽ\ቤቱ በኦፊሴል ጉዳዩ ለሚመለከተው የሳዑዲ መንግስት ተቋም እንዳመለከተ አሳውቋል።

ቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ፥ በቀጣይ ቀናት በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ክትትል በማድረግ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ እንደያደርግ እና እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

#ኢትዮጵያውያን አሁንም ቢሆን ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዲቀጥሉ የጥንቃቄ መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው የኢፌድሪ ቆንስላ ፅ/ቤት (ጅዳ) ነው።

@tikvahethiopia
#Attention

የሳዑዲ የፀጥታ አስጠባቂ አካላት በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት:-

- አስቸኳይ ጉዳይ ካልገጠማችሁ በስተቀር አሁን በሳዑዲ ያለው የአፈሳና ፍተሻ ሁኔታ እስኪረጋጋ ድረስ ሁሉም ዜጎች ወደ ቆንስላ ጽ\ቤቱ አካባቢ እንዳትሄዱ።

- የሳዑዲ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በሚወስዱት እርምጃም በተለይ ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ኖሯቸው በህግ አስከባሪ አካላት ከመጠን ያለፈ ኃይል አጠቃቀም ምክንያት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያጋጠማቸው የአካልና የንብረት ጉዳት የደረሰባቸው / ዘረፋ ያጋጠማቸው ዜጎች ተጨባጭ ማስረጃ በመያዝ ለቆንስላ ጽ\ቤቱ መጠቆም ይችላሉ። መረጃውን መሰረት በማድረግ የቆንስላ ጽ\ቤቱ ከሳዑዲ ወገን ጋር እነጋገራለሁ ብሏል።

-የመኖርያ ፈቃዳቸው ተቃጥሎ በራሳቸው ወጪ ወደአገር ለመግባት አሻራ ለመስጠት ሲጠባበቁ የነበሩ ዜጎች ከትላንት በስቲያ ጀምሮ የሳዑዲ ወገን የአሻራ አገልግሎት መስጠቱን ያቋረጠ በመሆኑ ከአገሪቱ የመንግስት ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር አገልግሎቱ ዳግም እስኪጀመር ድረስ እንዲታገሱ።

- ዜጎች በቆንስላ ጽ\ቤት አካባቢ ጨምሮ በየትኛውም አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የሳዑዲ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ ባወጣው ደንብ መሰረት የራሳቸውን እና የሌላውን ጤና ለመጠበቅ / ደንቡን ካለማክበር ከሚደርስ ቅጣት ለመዳን ሙሉ አፍና አፍንጫችሁን በማስክ ሸፍናችሁ እንድትንቀሳቀሱ አደራ ተብሏል።

አሁንም #ኢትዮጵያውያን ተገቢውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንድትቀጥሉ በጅዳ የሚገኘው ቆንስላ ጽ\ቤት የጥንቃቄ መልዕክቱን አስተላልፏል።

(የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት፣ ጅዳ)

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ALERT

ኑሯችሁን በደቡብ አፍሪካ ያደረጋችሁ የቲክቫህ - ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ሰሞኑን የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ለፖሊስ እጃቸውን መስጠታቸው ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ደጋፊዎቻቸው የተጀመረው ረብሻ አሁን መልኩን ቀይሮ የስደተኛ ንብረቶች እና የሀገሪቱ ትልልቅ ካምፓኒዎች (Checkers and Shopright ) የመሳሰሉትን ማውደም ላይ ትኩረት አድርጓል።

ስለዚህም ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የምትኖሩ #ኢትዮጵያውያን እራሳችሁን ከጥቃት እንድትጠብቁ እና የሀገሪቱን ሚዲያዎች በትኩረት እንድትከታተሉ አደራ እንላለን።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ትላንት ማታ የደ/ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ሲርል ራማፎሳ " ግጭት እያስከተሉ ያሉ ተቃውሞዎች እንዲቆሙ የጠየቁ ሲሆን፤ "ለዚህ አመጽ እና የንብረት ውድመት ምንም ዓይነት ምክንያት ሊቀርብ አይችልም" ማለታቸው የሚታወስ ነው።

Faya (Tikvah-Family)
South Africa
Limpopo

@tikvahethiopia
" ከ70 በላይ #ኢትዮጵያውያን 🇪🇹 ፖላንድ ገብተዋል " - በኢትዮጵያ የፖላንድ ኤምባሲ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የፖላንድ ኤምባሲ ሩስያ ዩክሬን ላይ ወረራ ከፈፀመች በኃላ በፖላንድ ስላለው ሁኔታ ከተማሪዎች እና ከቤተሰቦች በርካታ ጥያቄዎች እየደረሰው መሆኑን ገልጿል።

በፖላንድ ግዛት ምንም አይነት የፀጥታ ችግር የለም ያለው ኤምባሲው እንደሁል ጊዜው ዩኒቨርሲቲዎች ክፍት ናቸው ፣ ትምህርትም ቀጥሏል ፤ እንዲሁም ሆስፒታሎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት (ባቡር፣ ባስ) ፣ ሬስቶራንቶች፣ ቢሮዎች ሁሉ እንደሁልጊዜ ስራ ላይ ናቸው ብሏል።

በአሁን ሰዓት ከ1,500 በላይ ተማሪዎች በፖላንድ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተጠቁሟል።

ኤምባሲው ሩስያ በዩክሬን ላይ ህገወጥ ወረራ ከፈፀመች አንስቶ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ጦርነት ሽሽት ወደ ፖላንድ መግባታቸውን አመልክቶ ከእነዚህም መካከል በርካታ አፍሪካውያን እንደሚገኙበት እና ከ70 በላይ የሚሆኑትም #ኢትዮጵያውያን 🇪🇹 መሆናቸውን ገልጿል።

ፖላንድ ጦርነት ሸሽተው ወደ ሀገሯ የሚመጡ ሰዎች ደንበር ላይ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙና ፤ የምግብና መጠለያ ጨምሮ አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን እያደረገች እንደሆነው በአዲስ አበባ የፖላንድ ኤምባሲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#KenyaElection🇰🇪

የኬንያን ምርጫ እየታዘቡ የሚገኙ #ኢትዮጵያውያን እነማን ናቸው ?

ኬንያ እያካሄደች ያለችውን 5ኛው ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለመታዘብ ኢትዮጵያውያን ኬንያ ይገኛሉ።

🇪🇹 አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፦

የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃለማርያም ደሳለኝ መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገውን 'ብሬንትረስት ፋውንዴሽን'ን በመወከል ምርጫውን እየታዘቡ ናቸው።

አቶ ኃይለማርያም በሚመሩት ልዑክ ውስጥ እውቁ ኡጋንዳዊ ፖለቲከኛ እና ሙዚቀኛ ቦቢ ዋይን ይገኝበታል።

🇪🇹 ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ፦

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ደግሞ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) ታዛቢ ቡድንን በመምራት ኬንያ ናቸው።

🇪🇹 ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

የተቃዋሚው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ መሪ እና አንጋፋው ፖለቲካኛ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በኬንያ ተገኝተው ምርጫውን እየታዘቡ ይገኛሉ።

🇪🇹 ሌንሳ ቢየና ፦

የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ሌንሳ ቢየና የኤን ዲ አይ/አይ አር አይ (NDI/IRI) ዓለም-አቀፍ ምርጫ ታዛቢ ልኡክ አካል ሆነው በኤልዶሬት ከተማ በዩዜን ጊሹ ካዉንቲ የሚደረገዉን ምርጫ በመታዘብ ላይ ይገኛሉ፡፡

መረጃው ከቢቢሲ እና ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ያገኘነው ነው።

@tikvahethiopia