TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ፤ " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ " ሲል ውድቅ አድርጎታል።

ህወሓት ባወጣው መግለጫ ፥ " የስራ ኃላፊዎቼ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማካሄድ ሕጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል።

" በአፍሪካ ህብረት ፓናል ውይይትም ይህ ጉዳይ ተነስቶ ህጋዊ ሰውነቱ መመለስ እንዳለበት ስምምነት ተደርሶበታል " ሲል ገልጿል።

ይህን ተከትሎ " ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ ሰውነታችን ወደነበረበት እንዲመለስልን ብቻ በሀምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጥያቄ አቅርበናል " ብሏል።

ሆኖም " ቦርዱ የፕሪቶሪያውን ስምምነት፣ ከዚህ በፊት በሌሎች የፌደራል ተቋማት የተሰጡትን ውሳኔዎች፣ ሌሎች ህጎችና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደረሱ መግባባቶች ወደጎን በመተው ጥያቄውን ' በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ' መልሷል " ሲል ገልጿል።

ይህን ተከትሎ ህወሓት " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ ሆኗል " በማለት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ " አልቀበልም " ሲል አሳውቋል።

" በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ የተካተቱት ዝርዝር ይዘቶች አዲስ በወጣው ማሻሻያ ህግ መሰረት የተቀመጡና ካቀረብነው ጥያቄ ጋር የማይገናኙ ናቸው " ሲልም አክሏል።

" የቦርዱ ውሳኔ ህጋዊ ሰውነቴን ወደነበረበት እንዲመለስ የቀረበውን ጥያቄ የማይመልስ ፤ የነበሩ ውይይቶችን የሚቃረኑ ዝርዝር ይዘቶች የሚጭንብን በመሆኑ አልተቀበልኩትም " ያለው ህወሓት " ጥያቄያችን እስኪመለስ ድረስ የፓርቲው ሕገ ደንብ በሚፈቅድልን መልኩ ተያያዥ ስራዎችን እናከናውናለን " ብሏል።

የፌደራል መንግስቱም የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመከሩበት ወቅት ፦

-
TPLF እና መሰል ፓርቲዎች በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ሕጋዊ ፓርቲ እንዲሆኑ አዋጅ መሻሻሉ፤
- አቃቤ ህግ ለምርጫ ቦርድ መጻፍ የነበረበትን ማለትም ስራውን ሰርቶ የሚያጣራውን አጣርቶ በሕጋዊ መንገድ እንዲፈቅድላቸው፤
- የአስፈጻሚውን ስራ 100% መሰራቱን፤
- ፓርቲ ለፓርቲ ፤ የመንግሥት ለመንግሥት ውይይቶች ላይ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ እንደተሰጠ፤
-
TPLF ምርጫ ቦርድ ሄዶ የሚጠበቅበትን ዶክመንት አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ጉባኤ ማድረግ እንዳለበት ፤ ይህን ባያደርግ ምርጫ ቦርድም ካልተቀበለው፤ TPLFን ሕጋዊ ፓርቲ ካላለው ፦
በምርጫ ሊሳተፍ እንደማይችል ፤
መንግሥትም ሊሆን እንደማይችል ይህ ደግሞ ተመልሶ ጦርነት ውስጥ የሚያስገባ እንደሆነ፤
- ተመልሶ ጦርነት ውስጥ ከመግባት በተበጀው ሕግ ፤ በተደረሰው ስምምነት ህወሓት የቀረውን ጉዳይ አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ጉባኤ አካሂዶ ፓርቲውን መልሶ ወደ ፖለቲካ ስርዓት መመለስ እንዳለበት መግለጻቸው ይታወሳል።

#Ethiopia #TPLF #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

" ህወሓት 50 ዓመታታት ያስመዘገበ እንደ አዲስ መመዝገብ የሌለበት አንጋፋ የፓለቲካ ድርጅት ነው " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)


የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር)  ዛሬ እሁድ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም " ህወሓት 50 ዓመታታት ያስመዘገበ እንደ አዲስ መመዝገብ የሌለበት አንጋፋ የፓለቲካ ድርጅት ነው " ብለዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ " የህወሓት ህጋዊነት የመመለስ ጉዳይ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ጎን ለጎን እንጂ አሁን የተጀመረ አይደለም " ያሉ ሲሆን " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሁለቱ ተፈራራሚዎች እርስ በራሳቸው እውቅና እንደሚሰጣጡ ይደነግጋል " ብለዋል።

የህወሓት ህጋዊነትን ለመመለስ የተካሄደ በርካታ ውይይቶችን ተከትሎ ድርጅቱና ሌሎች የሚያካትት አዲስ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ የሚመለከት የተሻሻለ አዋጅ እስከ ማውጣት መደረሱ አብራርተዋል።

" የተሻሻለው በአመፅ ድርጊት የተሳተፉ የፓለቲካ ፓርቲዎች መልሶ ስለ መመዝገብ የሚመለከት አዋጅ ህወሓት ወደ ቀደመው እውቅናዋ ሊመልስ አይችልም " ያሉት ደብረፅዮን (ዶ/ር) ፥ " ስለሆነም ህወሓት ወደ ነባር እውቅናው ይመለሳል እንጂ እንደ አዲስ አይመዘገብም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ህወሓት እንደ አዲስ መመዝገብ ማለት የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ማፍረስ ማለት ነው " በማለትም ተናግረዋል።

" የአፍሪካ ህብረት ታዛቢዎች በተገኙበት ህወሓት ወደ ነባሩ እውቅና ለመመለስ ነው ስምምነት የተደረሰው " ሲሉ ገልፀዋል። 

ሊቀመንበሩ ህወሓት ጉባኤ ስለሚያካሂድበት ጊዜ ቁርጥ ያለ ቀንና ቦታ በመግለጫቸው አልጠቆሙም።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ፥ ከቀናት በፊት ለህወሓት " በልዩ ሁኔታ " ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ መስጠቱ ይታወሳል።

ቦርዱ ነሀሴ 3 ባወጣው መግለጫ ድርጅቱ በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን የሚገልጸው ድብደቤ ከደረሰው ቀን አንስቶ ባሉት 6 ወራት የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ ያዛል።

ህወሓት ግን ነሀሴ 4/2016 ዓ.ም " የተሰጠኝ የምዝገባ ውሳኔ ከተካሄዱት የሁለትዮሽ ወይይቶችና መግባባት ወጪ ነው ስለሆነ ወደ ነባሩ እውቅናዬ የማይመልስ ውሳኔ አልቀበልም " ብሎ መግለጫ አውጥቷል።

ዛሬ ደግሞ የድርጅቱ ሊቀመነንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ " ህወሓት 50 ዓመታታት ያስመዘገበ እንደ አዲስ መመዝገብ የሌለበት አንጋፋ የፓለቲካ ድርጅት ነው፤ ህጋዊ ሰውነታችን ይመለሳል እንጂ እንደ አዲስ አንመዘገብብም " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #TPLF "ሊካሄድ በታቀደው ጉባኤ አልሳተፍም ! " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስታዳደር ፕሬዜዳንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ ዛሬ ዓርብ ነሀሴ 3/2016 ዓ.ም ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፣ ለድርጅቱ የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ተኽለብርሃን ኣርኣያ በፃፉት ደብዳቤ በጉባኤው እንደማይሳተፉ አረጋግጠዋል። ፕሬዜዳንቱ በደብዳቤያቸው…
#TPLF

" ህወሓትን ለማፍረስ አልሞ በሚካሄደው ጉባኤ አንሳተፍም !! " - የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት

ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 14 የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በህወሓት ጉባኤ ላይ እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል።

" ህወሓት ለማፍረስ አልሞ በሚካሄደው ጉባኤ አንሳተፍም " ሲሉ አቋማቸውን ገልጸዋል።

" በጥቂት ቡድኖች ማን አለበኝነት የተዘጋጀና የጉባኤው ከፍተኛ ስልጣን ያለው የማእከላዊ ኮሚቴ አመራር ያልወሰነው፣ የድርጅታችን የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ውድቅ ያደረገው ፣ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ መግባባት ያልተደረሰበትና ትግራይ ከጫፍ አስከ ጫፍ ያልተወከለበት የጠባብ ቡድን ጥቅም ለማስከበር ብቻ ባለመ ጉባኤ አንሳተፍም " ብለዋል።

በጉባኤው " አንሳተፍም " ያሉት 14ቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ፦
1. ጌታቸው ረዳ
2. በየነ ምክሩ
3. ክንደያ ገ/ህይወት
4. ሓጎስ ጎዶፋይ
5. ሰብለ ካህሣይ
6. ብርሃነ ገ/የሱስ
7. ሰለሞን መዓሾ
8. ሺሻይ መረሳ
9. ሃፍቱ ኪሮስ
10. ረዳኢ ሓለፎም
11. ነጋ ኣሰፋ
12. ገ/ሕይወት ገ/ሄር
13. ሩፋኤል ሽፋረ
14. ርስቁ ኣለማው ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF : " ህወሓትን ለማፍረስ አልሞ በሚካሄደው ጉባኤ አንሳተፍም " ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት " ጉባኤውን ተከትሎ ለሚመጣው ነገር እኛ የለንበትም " ብለዋል።

ጉባኤው " በጥቂት ቡድኖች ማን አለበኝነት " የተዘጋጀ ፦
- የጉባኤው ከፍተኛ ስልጣን ያለው የማእከላዊ ኮሚቴ አመራር ያልወሰነው
- የድርጅቱ የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ውድቅ ያደረገው
- ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ መግባባት ያልተደረሰበትና
- ትግራይ ከጫፍ አስከ ጫፍ ያልተወከለበት፤ ነጻ ያልወጡ አካባቢዎች ባሉበት ነው ብለዋል።

" ጉባኤው የጠባብ ቡድን ጥቅም ለማስከበር ብቻ ያለመ ነው ፤ እኛ ደግሞ በዚህ ላይ አንሳተፍም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ህወሓትን እና የትግራይ ህዝብ ወደ ከፋ አደጋ የሚያጋልጥ ያልተረጋጋ ጉባኤ ማካሄድ የጠባብ ቡድኑ ጥቅምን ከማረጋገጥ ያለፈ እርባና የለውም " ሲሉም ገልጸዋል።

14ቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት " ህወሓትን እና የትግራይ ህዝብ ወደ ሌላ የተወሳሰበ ቀውስ በሚከት በጠባብ ቡድን የተዘጋጀው ጉባኤ አንሳተም " ብለው " ጉባኤውን ተከትሎ ለሚፈጠረው ማንኛውም ነገር ተጠያቂው ይኸው ቡድን መሆኑ እናስታውቃለን " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ያሉበት 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት " ጠባብ ቡድን " እያሉ የገለጻቸውን ጥቂት ቡድኖች በስም አልገለጿቸውም።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF : " ህወሓትን ለማፍረስ አልሞ በሚካሄደው ጉባኤ አንሳተፍም " ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት " ጉባኤውን ተከትሎ ለሚመጣው ነገር እኛ የለንበትም " ብለዋል። ጉባኤው " በጥቂት ቡድኖች ማን አለበኝነት " የተዘጋጀ ፦ - የጉባኤው ከፍተኛ ስልጣን ያለው የማእከላዊ ኮሚቴ አመራር ያልወሰነው - የድርጅቱ የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ውድቅ ያደረገው…
 #TPLF : የህወሓት የፅህፈት ቤት ሃላፊና የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ብሔር  የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት በጉባኤ እንዲሳተፉ በፃፉት ደብዳቤ " 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ነሃሴ 7/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00  ጀምሮ በመቐለ የሰማእታት ሓወልት አዳራሽ ይካሄዳል " ይላል።

ይሁን እንጂ የደርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ከ2 ሳምንት በፊት ከሚካሄደው ጉባኤ ራሱ ማግለሉ ይታወሳል።

የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበርና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት " ማንአለበኝነት የተጠናወተው ጠባብ ቡድን " ያሉት አካል " ጉባኤ ንድሕነት ! "  በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው ጉባኤ እንደማይሳተፉ አስታወቀዋል።

" ጉባኤውን ተከትሎ ለሚመጣ ነገር እኛ የለንበትም " ብለዋል።

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣  ምክትል ሊቀ-መንበሩ የሚገኙባቸው 14 ፒቲሽን የፈረሙ የማእከላይ ኮሚቴ አባላት ጨምሮ በመስዋእት ፣ ከደርጅቱ በመልቀቅ ፣ በህመም እና በሌሎችም ምክንያቶች ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ጉባኤ በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት አይሳተፉም።

በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ ማለትም ከ50 በመቶ በላይ አለመሳተፍ ደግሞ የደርጅቱ ህልውና እጅጉ የሚጎዳ የሚሉ በርካታ አስተያየቶች በመንሸራሸር ላይ ናቸው።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
 
TIKVAH-ETHIOPIA
 #TPLF : የህወሓት የፅህፈት ቤት ሃላፊና የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ብሔር  የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት በጉባኤ እንዲሳተፉ በፃፉት ደብዳቤ " 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ነሃሴ 7/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00  ጀምሮ በመቐለ የሰማእታት ሓወልት አዳራሽ ይካሄዳል " ይላል። ይሁን እንጂ የደርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ከ2 ሳምንት በፊት ከሚካሄደው ጉባኤ ራሱ…
#TPLF

ሰባት የመቐለ ከተማና ሁለት የትግራይ ማእከላዊ ዞን ከፍተኛ ካድሬዎች " ጠባብ ቡድን " ሲሉ በጠሩ አካል ተጠርቷል ባሉት የህወሓት ጉባኤ እንደማይሳተፉ አስታወቁ።

አመራሮቹ ፤ " ባሁኑ ወቅት የሚካሄደው ጉባኤ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ላለመሳተፍ ወስነናል " ብለዋል።

በጉባኤው እንዳማይሳተፉ በደብዳቤ ያስታወቁ የህወሓት ከፍተኛ ካድሬዎች ፦

1. ነጋሽ ኣርኣያ - የመቐለ ጀተማ የህወሓት ፅህፈት ቤት ሃላፊ 
2. ሓለፎም ገ/ህይወት  - የሓድነት ክፍለ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ (መቐለ)
3. ኤልያስ ኪሮስ  -  የዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ (መቐለ)
4. እያሱ ተካ  -  የዓይደር ከፍለ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ (መቐለ)
5. ኣስመላሽ ብርሃኑ  - የዓዲ ክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ (መቐለ)
6. ፍጹም ለገሰን - በትግራይ ማእከላዊ ዞን የዓዴት ወረዳ አስተዳዳሪ 
7. ሓጎስ ንጉስ - የዓዴት ወረዳ የአደረጃጀት ሃላፊ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#FederalGovernment #TPLF

" አላስፈላጊ እና ሕዝብን የማይጠቅም፣ ትርጉም አልባ ንትርክን አስወግደን ለሕዝብ ረብ ያላቸው ጉልህ የሰላም እና የልማት አጀንዳዎች ላይ ልናተኩር ይገባል " - የፌዴራል መንግሥት ኮሚኒኬሽን

የፌዴራል መንግሥት ኮሚኒኬሽን በህወሓት ጉዳይ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ መግለጫ ፦

- ህወሓት እንዴት ሕጋዊ ሰውነቱን ሊያጣ እንደቻለ ወደኃላ መለስብሎ አስታውሷል ፤

- የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲፈጸም የፌዴራል መንግሥት በስምምነቱ የገባው ግዴታ የህወሓት የሽብርተኝነት ፍረጃ እንዲነሣ ሂደቱን የማሣለጥ ኃላፊነት (የስምምነቱ አንቀጽ 7 (2) (C)) እንደሆነ ፤

- የፌዴራል መንግሥት የህወሓትን የሕግ ሰውነት እና የምዝገባ ጉዳይ በተመለከተ በፕሪቶሪያ ስምምነት ውስጥ የወሰደው የተለየ ኃላፊነት ወይም ግዴታ እንዳልነበር፤

- ህወሓት በፕሪቶሪያ ስምምነት እንቀጽ 7 (1) (A) መሠረት የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት፣ ሕጎች፣ የፌዴራል ተቋማትን እና ሌሎች ሕገ መንግሥታዊ ተቋማትን ሥልጣን የማክበር ግዴታ መግባቱም ፤ ስለዚህ ሕወሐት የሀገሪቱን የፖለቲካ ፖርቲዎች የምዝገባ ሕግ እና የምርጫ ቦርድን ሥልጣን በማክበር የመሥራት ግዴታ እንዳለበት ... ገልጿል።

የፌዴራል መንግሥት በመግለጫው ፤ ህወሓት ወደ ህጋዊ መስመር ለማምጣት ስለተኬደባቸው መንገዶች ፣ ውይይቶች ፤ በህወሓት እና ምርጫ ቦርድ በኩል ስለተነሱት ልዩነቶች አብራርቷል።

ድርጅቱ ሕጋዊ ሰውነት እና ዕውቅና እንዲኖረው ለቦርዱ የትብብር ጥያቄ ስለማቅረቡም አስታውሷል።

እንዲሁም አዋጅ እስከማሻሻል በደረሰ እርምጃ ድርጅቱ ወደ ህጋዊ መስመር እንዲገባ ለማድረግ የተኬደበትን ርቀት ገልጿል።

ይህን ተከትሎ ህወሓት ሕጋዊ ሰውነት እና ዕውቅና ለማግኘት የሚጠበቅበት የፓርቲ ሰነዶቹን ማለትም የፓርቲውን ፕሮግራም እና ሕገ ደንብ፣ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ሰነዶችን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማቅረብ በተሻሻለው አዋጅ መሠረት ተመዝግቦ ሕጋዊ ሰውነት እንዳገኘ አሳውቋል።

በመሆኑም " የምዝገባ እና የህግ ሰውነትን ጉዳይ በዚህ በመቋጨት፤ የሁሉም ባለድርሻ አካል ርብርብ ሰላምን በማጽናት፣ በመልሶ ግንባታ እና በልማት አጀንዳ ላይ ሊሆን ይገባል " ብሏል።

ፌዴራል መንግሥት"  አላስፈላጊ እና ሕዝብን የማይጠቅም፣ ትርጉም አልባ ንትርክን አስወግደን ለሕዝብ ረብ ያላቸው ጉልህ የሰላም እና የልማት አጀንዳዎች ላይ ልናተኩር ይገባል " ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

" ጠቅላላ ጉባኤው ከቦርዱ ፍቃድ ውጭ ከተካሄደ  ቦርዱ ለዚህ ጉባኤም ሆነ በጉባኤዎቹ ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ዕውቅና አይሰጥም "- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከህወሓት ጉባኤ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለድርጅቱ ደብዳቤ ጽፏል።

ቦርዱ ፥ ነሐሴ 3/2016 ዓ/ም ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ ፖርቲው በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን እና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትም እንደሰጠው አስታውሷል።

ፓርቲው የቦርዱ ደብዳቤ እና የምስክር ወረቀት ከደረሰው ቀን ጀምሮ የሚተዳደረው የኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011ና ይህን አዋጅ ባሻሻለው አዋጅ ቁጥር 1332/2016 እንዲሁም እነዚህን አዋጆች መሰረት ተደርገው በወጡ መመሪያዎችና የቦርዱ ውሳኔዎች መሰረት እንደሆነ አስገንዝቧል።

ቦርዱ ውሳኔ የሰጠባቸውና በደብዳቤ ከገለፃቸው በፓርቲው መተግበር ካለባቸው ተግባራት መካከል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ከማድረጉ ከ21 ቀን በፊት ለቦርዱ ማሳወቅና ፖርቲው በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባኤ የቦርዱ ታዛቢዎች መገኘት በዋናነት የተገለፁ ግዴታዎች እንደሆኑ አመልክቷል።

ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት ፖርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ሊያደርግ መሆኑን ቦርዱ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን እየተዘገበ መሆኑ መመልከቱን ገልጿል።

በዚህም ቦርዱ " ለአንድ ጠቅላላ ጉባኤ መደረግ አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እንዲያውቅ ባልተደረገበት፣ ባልተከታተለበትና ባላረጋገጠበት እንዲሁም የቦርዱ ታዛቢዎች ባልተገኙበት ተጠራ የተባለው ጠቅላላ ጉባኤ ሊካሄድ አይችልም " ሲል አሳውቋል።

ጠቅላላ ጉባኤው ከቦርዱ ፍቃድ ውጭ ከተካሄደ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዚህ ጉባኤም ሆነ በጉባኤዎቹ ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ዕውቅና የማይሰጥ መሆኑን ለህወሓት በጻፈው ደብዳቤ ላይ ገልጿል።

#TPLF #NEBE

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

ህወሓት ጉባኤውን ለማድረግ መዘጋጀቱ ታውቋል።

የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የሚገኙባቸው በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተቃውሞ እና በሌሎችም ምክንያቶች የማይሳተፉበት ፤  የድርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና የነፈጉት 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ዛሬ ማክሰኞ ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በይፋዊ የመክፈቻ ስነ-ሰርዓት በመቐለ መካሄድ እንዲጀምር ቀን፣ ቦታና ሰዓት ተቆርጦለታል።

ጉባኤውን አስመልክቶ የተሰራጨው መርሃ ግብር እንደሚጠቁመው ከዛሬ ነሀሴ 7 እስከ 12 / 2016 ዓ.ም ባሉት 6 ቀናት ይከናወናል።

የህወሓት ፅህፈት ቤት እና ማህተም የተቆጣጠረውና በሊቀመንበሩ ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመራው ሃይል ጉባኤውን በመቐለ በሰማእታት የሓወልቲ አዳራሽ " ጉባኤ ድሕነት!" ማለትም " የመዳን ጉባኤ! " በሚል መሪ ቃል ነው የሚያካሂደው።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንትና በድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ የሚመሩት 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ደግሞ " ጉባኤው ህወሓት የሚያጠፋ ፣ ለትግራይ ህዝብ ሌላ ችግርና የእርስ በርስ ግጭት የሚጋብዝ አደገኛ ጉባኤ " በማለት በይፋ ባወጡት መግለጫ ተቃውሞውታል።

በእነ ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ክንፍ ግን በከፍተኛ ተቃውሞ ታጅቦ ከነሀሴ 7 - 12/2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በሚቀጥሉት 6 ተከታታይ ቀናት ጉባኤውን ማካሄድ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፍቃዱ ውጭ ለሚካሄድ ለዚህ ጉባኤ ምንም አይነት እውቅና እንደማይሰጥ አሳውቋል።

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-08-13

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ህወሓት ጉባኤውን ለማድረግ መዘጋጀቱ ታውቋል። የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የሚገኙባቸው በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተቃውሞ እና በሌሎችም ምክንያቶች የማይሳተፉበት ፤  የድርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና የነፈጉት 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ዛሬ ማክሰኞ ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በይፋዊ የመክፈቻ ስነ-ሰርዓት በመቐለ…
#TPLF : ህወሓት የጉባኤ መክፈቻ እያደረገ ይገኛል።

ድርጅቱ " 14ኛው ጉባኤ መክፈቻ እየተካሄደ ነው " ብሏል።

በሊቀመንበሩ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ቡድን ነው ጉባኤውን በመቐለ በሰማእታት የሓወልቲ አዳራሽ " ጉባኤ ድሕነት ! / የመዳን ጉባኤ ! " በሚል መሪ ቃል የጀመረው።

እንደወጣው መርሀ ግብር ጉባኤው ከነሀሴ 7 - 12/2016 ዓ.ም እንደሚቆይ ነው የተነገረው።

የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተቃውሞና በሌሎችም ምክንያቶች አይሳተፉም።

የድርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና ነፍገዋል።

በተለይ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉና ከቦርዱ ፍቃድ ውጭ በሚደረግ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ዕውቅና የማይሰጥ መሆኑን ለህወሓት በጻፈው ደብዳቤ ቀድሞ አሳውቋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

ፎቶ፦ TPLF

@tikvahethiopia