TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ባህር_ዳር

ከግድያው ቀደም ብሎ የክልሉ የጸጥታና የደህንነት ሀላፊዎች ተሰበሰቡበት፣ ቀጥሎም እገታ ተፈጸመባቸው የተባለው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስርያቤት ከፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት ቢያንስ በ3 ወይም በ4 ፌርማታ ይርቃል። በዚሁ ህንጻ በጸጥታ ሀይሎች መካከል ለሰዐታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። ሕንጻው የሚገኝበት አካባቢ የአማራ ቴሌቪዥንና ራዲዮን ጨምሮ አብዛኞቹ የክልሉ መንግስት ቢሮዎች ይገኛሉ።

Via #elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

በቅዳሜ ከፍተኛ ጥቃት ካስተናገዱ የከተማው አካባቢዎች፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚኖሩበት ቀበሌ ሶስት የሚገኝ በአጥር የተከለለ የመኖሪያ መንደር (gated community) አንዱ ነው። በፒካፕ መኪኖች የተጫኑ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ግቢውን ከሚጠብቁ የክልሉ ልዩ ሀይል አባላት ቢያንስ 6 ተገለዋል። በግቢው ከሚኖሩ ባለስልጣናት ጋርም የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል።

Via #elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው የተገደሉባት #ዘንዘልማ 'ከገስት ሀውሱ' በ6 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የምትገኝ 'ሳተላይት' ከተማ ናት። በከተማዋ የግብርና ኮሌጅ የሚገኝ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ በአብዛኛው ጫት በማምረት የሚተዳደሩ ናቸው። አካባቢውም በጫት ማሳ የተሸፈነ ነው። በከተማው ምዕራባዊ ዳርቻ የኢ.መ.ሠ ምዕራብ ዕዝ ዋና መስሪያቤትና የኢ.አ.ሀ ሰሜን ምድብ ዋና ጣቢያን ጨምሮ የወታደርና የፌ. ፖሊስ ካምፖች የሚገኙ ሲሆን፣ ቃል አቀባይ ንጉሱ ጥላሁን እንዳሉት በክልሉ ም/ፕሬዝደንት ግብዣ ወደ ከተማው እንዲገቡ ሆኗል። ካምፖቹ ለሰዐታት የተኩስ ልውውጥ ከተደረገበት የፖሊስ ኮሚሽን ህንጻ በቅርብ ዕርቀት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የፌድራል ሀይሎች ስንት ሰዐት ላይ ወደ ከተማ እንደገቡ አቶ ንጉሱ አልተናገሩም። ካምፖቹ ለሰዐታት የተኩስ ልውውጥ ከተደረገበት የፖሊስ ኮሚሽን ህንጻ በቅርብ ዕርቀት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የፌድራል ሀይሎች ስንት ሰዐት ላይ ወደ ከተማ እንደገቡ አቶ ንጉሱ አልተናገሩም።

Via #elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

ባለፈው ቅዳሜ ጥቃት ከደረሰባቸው ተቋማት መካከል የአዴፓ ጽህፈት ቤት፣ የክልሉ ምክርቤት እና የአማራ መገናኛ ብዙሐን ኤጀንሲ የሚገኙበት ሲሆን፣ "መፈንቅለ መንግስት" ሞካሪ የተባሉ ሀይሎች የአዴፓን ጽህፈት ቤት መቆጣጠር ችለው ነበር።

Via #elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ዳግማዊ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ‹ዲያስፖራ ሰፈር› እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የግለሰብ መኖሪያ ቤትን በመከራዬት ከኑግ ተረፈ ምርት (ፋጉሎ) ዘይት ሲመረት በማኅበረሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሠራተኞች እንደተናገሩት ሕገ-ወጥ ሥራው የሚሠራው በሌሊት እንደሆነና ቀን ደግሞ ለእንስሳት መኖ አገልግሎት የሚውል ተረፈ ምርት ሲያመርቱ ይውላሉ፡፡ ሠራተኞቹ በቀን 120 ብር እንደሚከፈላቸውም ተናግረዋል፡፡ የሚመረተውን ዘይትም ጧት እና ማታ ወደ ሌላ አካባቢ በመውሰድ እንደሚሸጡም ገልጸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/BDR-07-10
#ባህር_ዳር የአዴፓ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ስብሰባ ጀምሯል፡፡ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን እያካሄደ የሚገኘው በባሕር ዳር ከተማ ነው፡፡

Via አብመድ
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

በባህር ዳር በተለምዶ #አባይ_ማዶ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ረፋዱን በነበረ የተኩስ ልውውጥ ሰዎች መሞታቸውን የዓይን እማኞች ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ዛሬ ከምሳ ሰዓት በፊት የጸጥታ ኃይሎች “ተጠርጣሪ ለመያዝ” ተኩስ ከፍተው ነበር። ከዚያ በኋላ በነበረ የተኩስ ልውውጥ ተጠርጣሪውን ጨምሮ ቁጥራቸው በወል ያልታወቀ የጸጥታ ኃይሎች #ተገድለዋል ብለዋል። ስለጉዳዩ የተጠየቁት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኃላፊ አቶ አበረ አዳሙ “ስብሰባ ላይ እንደነበሩ እና ሪፖርት እንዳልደረሳቸው” ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

Via #የጀርመን_ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

ትናንት እሁድ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ አባይ ማዶ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በአካባቢው ሚሊሻዎችና ሲፈለግ በነበረ በአንድ ግለሰብ መካከል በተደረገ የተኩስ ለውውጥ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የባህር ዳር ፖሊስ አባል ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ተፈጸሞ ከቆየ ሌላ የግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ ሲፈለግ የቆየ ነው የተባለን ግለሰብ ሊይዙ ሲከታተሉት የነበሩ የአካባቢው ሚሊሻዎች ላይ ተኩስ በመክፈቱ ነው ጉዳት የደረሰው።

ሸፍቶ ነበር የተባለውን ግለሰብ ሲከታተሉ የቆዩት ሁለት የሚሊሻ አባላት፤ እሁድ ምሳ ሰዓት አካባቢ ተጠርጣሪው አለበት ወደተባለው ቤት በሄዱበት ጊዜ ተተኩሶባቸው ህይወታቸው ሲያልፍ ተጠርጣሪው በሌሎች የጸጥታ አባላት እንደተተኮሰበት ለማወቅ ተችሏል።

በተኩስ ለውውጡ የተመቱት ሁለቱ ሚሊሻዎች ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ ተፈላጊው ግለሰብ ግን ከቆሰለ በኋላ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ነው ህይወቱ ያለፈው ተብሏል።

ከሳምንታት በፊት መንግሥት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ነው ካለው ግድያ ጋር በተያያዘ ከገባችበት ድንጋጤ በማገገም ላይ በምትገኘው የባህር ዳር ከተማ ውስጥ እሁድ ዕለት ያጋጠመው የተኩስ ልውውጥ በነዋሪዎች ላይ ስጋትን ፈጥሮ ነበር።

#BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር_ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 8 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች የፊታችን ቅዳሜ ያስመርቃል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ዶክተር ፍሬው ተገኘ ለአብመድ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ሐምሌ 13/2011 ዓ.ም የሚያስመርቀው፡፡

በዕለቱም የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጦፋ ሙሃመድ ዑመር ለተመራቂዎች መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል፡፡ ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጦፋ ከሀይማት አባቶች፣ ከጎሳ መሪዎች፣ ከመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ከልዩ ልዩ የኅብረሰተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ 100 የልዑክ አባሎቻቸውን ይዘው ወደ ባሕር ዳር እንደሚመጡ ነው የሚጠበቀው፡፡

የልዑኩ አባላትም የባሕር ዳርና አካባቢዋን የመስህብ ሥፍራዎች እንደሚጎበኙና የሕዝብ ለሕዝብ ትሥሥርን የሚያጠናክሩ ውይይቶችን እንደሚያካሂዱ ይጠበቃል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር_ዩኒቨርሲቲ

"በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው በነርቭ እና ድንገተኛ ህክምና ላይ ያተኮረው አለምዓቀፍ ኮንፈረንስ ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል።" A.ነኝ ከ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ዑመር የተመራው ልዑክ ባሕር ዳር ገብቷል፤ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ወኪሎችም በአውሮፕላን ማረፊያው በመገኘት በድምቀት ተቀብለዋቸዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጦፋ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከጎሳ መሪዎች፣ ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ከ100 በላይ አባላት ያሉት ልዑክ እየመሩ ነው ባሕር ዳር የገቡት፡፡

በባሕር ዳር በሚኖራቸው ቆይታም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ ላይ ይገኛሉ፤ የአማራ- ሶማሌ ሕዝቦችን ለማጠናከር ባለመው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ውይይት ላይም ይሳተፋሉ፡፡ አቶ ሙስጦፋ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በዓለ ሲመት ይገኛሉ፣ የልዑኩ አባላት ደግሞ ከሕዝብ ለሕዝብ ውይይቱ ባለፈ የተለያዩ ታሪካዊ ቦታዎችን ይጎበኛሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

"የሕዝብ ለሕዝብ #ትስስሩ የተዘራውን #የውሸት ትርክት ማርከሻ መድኃኒት ነው!" አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ ዑመር

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/BC-07-20
#ባህር_ዳር /ጣና/

በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር #ሙስጠፌ ሙሐመድ ዑመር የተመራው የክልሉ የልዑክ ቡድን አባላት የጣና ላይ ታሪካዊ ሥፍራዎችን ጎብኝተዋል፡፡ #ባህርዳር #ጣና

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

የአማራ ክልልና የሱማሌ ክልሎች ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ በባህርዳር ከተማ የክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አዳራሽ ተካሄደ፡፡ በምክክር መድረኩ የሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ዑመር፣ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚደንት ላቀ አያሌው የተሳተፉ ሲሆን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው የሕዝብ ለሕዝብ ውይይቱ ለሶማሌ ክልል የልዑክ አባላት #ሥጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡ የአማራ ክልል ለሶማሌ ክልል ሁሉም የልዑክ አባላት አገልግል እና የዘጌ ቡና በስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጦፋ ሙሐመድ ዑመር የተመራው የሶማሌ ክልል ልዑክ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ትሥሥር የሚያጎለብት ውይይት ተካሂዷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መሥራችነት የተጀመረው የባሕር ዳር የሳይንስ ኢንኩቤሽን ማዕከል ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ የሳይንስ ማዕከሉ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን የሳይንስ ትምህርቶችን ያስተምራል፡፡ ተማሪዎቹ በ8ኛ ክፍል ውጤታቸው ተመርጠው ነው ማዕከሉን የሚቀላቀሉት፡፡ ማዕከሉ የመጀመሪያዎቹን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ዛሬ ሐምሌ 14 2011ዓ.ም አስመርቋል፡፡ ማዕከሉ በቴክኖሎጂ የላቁ ተማሪዎችን ለማፍራት ዓላማ አድርጎ ነበር የተቋቋው፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር #አበረ_አዳሙ ለክልሉ ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በአማራ መገናኛ ብዙኻን ዛሬ ባስተላለፉት ማብራሪያ የሰኔ 15ቱ የባለ ሥልጣናት ግድያ ወንጀል ምርመራ እስካሁን ያልተጠናቀቀው ወንጀሉ ውስብስብና ምርመራው ዘርፈ ብዙ ስለሆነ መሆኑን ጠቅሰው፣ በቅርብ ዝርዝር ሪፖርት እናቀርባለን ብለዋል፡፡ ሴራውን በማክሸፋችን ክልላችን ከመፍረስ አድነነዋል፤ ባንቆጣጠረው ኖሮ ግን የባሰ ትርመስ ይፈጠር ነበር ብለዋል፡፡ እስካሁን በተደረሰበት ድምዳሜ ከጀርባ ስላሉ አካላት ይህ ነው ተብሎ የሚቀርብ ድምዳሜ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ አማራን በጎጥ ለመከፋፈል #ፌስቡክ ላይ የሚሰሩ ሃይሎች ግን ከባድ ችግር ስለፈጠሩብን መንግሥት ያግዘን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል፡፡

Via #wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰኔ_15 #ባህር_ዳር

የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ እና ፍትሕ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም ለተፈጠረውን ችግር የፀጥታ ተቋማት መደማመጥ አለመቻል እና ወጥ የሆነ የአመራር ሂደት አለመስጠታቸው እንደሆነ አመለከተ፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ እና ፍትሕ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ በጋራ የተስማማባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በክልሉ ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ አቅርቧል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ሰኔ 15/2011 ዓ.ም የተፈጠረውን ችግር የተመለከተ ጉዳይ አቅርቧል፡፡ የጥፋት መንስኤው የፀጥታ ተቋማት አመራሮች መደማመጥ አለመቻል እና ወጥ የሆነ የአመራር ሂደት ባለመኖሩ መሆኑን ለምክር ቤት አባላቱ ግልጽ አድርጓል፡፡

በክልሉ መንግሥት የሠላም እና ደኅንነት ተቋም ላይ ችግሮች ከመከስቱ በፊት የፖለቲካ አመራሩ አስቀድሞ ዋነኛ መንስኤዎችን እየለዬ መፍታት ባለመቻሉ የተከሰተ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ ሰኔ 15/2011ዓ.ም የተፈፀመው ድርጊት የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት በመቆጣጠር በወቅቱ ስብሰባ ላይ የነበሩ ከፍተኛ መሪዎችን በመክበብ ግድያ መፈጸሙ፤ በቡድን መሳሪያ ጭምር በመጠቀም ስልጣን ለመያዝ የተፈፀመ መሆኑን ነው ቋሚ ኮሚቴው ያቀረበው፡፡ የክልሉ ሕዝብ፣ የክልሉ እና የፌዴራል ፀጥታ አካላት ችግሩን ለመፍታት ባስተዋይነት ለወሰዱት ፈጣን እርምጃ እና መሰዋዕትነት ለከፈሉት ወዳጅ ዘመዶቻቸው የክልሉ ምክር ቤት መፅናናትን እየተመኘ በማንኛውም ወቅት ከጎናቸው መሆኑን አረጋግጧል፡፡

አሁንም ቢሆን በወቅቱ የተፈጸመውን ድርጊት ለመሸፋፈን መሞከር እና የድርጊቱ ፈፃሚዎችን ከተጠያቂነት እንዲያመልጡ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተቀባይነት እንደሌለው አስረድቷል፡፡

ተጨማሪ👇
https://telegra.ph/AM-07-23

@tikvahethiopia