TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከአሜሪካ #የጥላቻ_ንግግርን የሚያሠራጩ ኢትዮጵያዊያን እንዴት በህግ ይጠየቃሉ
.
.
በአሜሪካ የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩ ኢትዮጵያዊያንን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢትዮጵያ አሜሪካዊያን የዜጎች ምክር ቤት አስታውቋል።

ያነጋገርናቸው የምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነት አቶ አምሳሉ ፀጋዬ፤ ወንድም ወንድሙን በማጣላት፤ ብሔር ከብሔር በማጋጨት እንደ ሃገር ለመቀጠል ፈታኝ ሆኗል፤ ይህንን የሚያደርጉ ግለሰቦችን ለማስተማር ብዙ እየተሞከረ ቢሆንም ነገሩ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ስለመጣ ምክር ቤቱ ግለሰቦቹን ወደ ህግ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ይናገራሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት በአሜሪካ የጥላቻ ንግግር በሌላ ማህበረሰብ በማሰራጨት፤ ሞትና መፈናቀልን ማስከተል በሕግ እንደሚያስቀጣ ይገልፃሉ።በዚህ ረገድ የሚጠቅሱት ፈርስት አመንድመንት የተሰኘው የአሜሪካ ህግን ነው።

እሳቸው እንደሚሉት ምንም እንኳን በፈርስት አመንድመንት የመናገር ነፃነት የተጠበቀ ቢሆንም በዚሁ ህግ ላይ በመናገር ነፃነት የማይካተቱ ድርጊቶችም ተዘርዝረው ይገኛሉ።

"ግድያ፣ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ፣ ብሔርን ከብሔር (ማኅበረሰብን ከማኅበረሰብ) የሚያጋጭ ከሆነ፤ የጥላቻ ንግግሩ ያስከተለው የጉዳት መጠን ተለይቶ ግለሰቦቹን ተጠያቂ ለማድረግ ይቻላል" ይላሉ አቶ አምሳሉ።

የሕግ ሂደቱን የሚከታተል የጠበቆች ቡድን ያለ ሲሆን በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ማስረጃዎችን በማቅረብ የጥላቻ ንግግርን የሚያሰራጩ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ እንደሚያደርጉም ያክላሉ።

"አብዛኞቹ እዚህ የሚኖሩ ለአገር የሚያስቡ ናቸው፤ ነገርግን የመጡበትን ማህበረሰብ በመርሳት ያ - ማህበረሰብ ቢፈርስ ደንታ የሌላቸው ጥቂቶች አሉ " የሚሉት አቶ አምሳሉ በህጉ መሰረት ቅጣቱ ከእስር ወደ አገር ተጠርንፎ እስከመመለስ የሚደርስ እንደሆነ ይናገራሉ።

በሕጉ መሠረት ጥላቻን መንዛት ፤ የግድያ ዛቻና ቅስቀሳ፣ የወሲብ ፊልም፤ ወንጀል ለመፍጠር መደራጀትን መሠረት ያደረገ ቅስቀሳን የሚያደርግ ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ ያስረግጣሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት እንቅስቃሴው አሜሪካን አገር ብቻ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ትኩረት ያደረገ ነው። ይሁን እንጂ በሌሎች አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ እየተነጋገሩ መሆናቸውንም ገልፀውልናል።

ጉዳዩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ንግግር አድርገው ከሆነ ጥያቄ ያነሳንላቸው አቶ አምሳሉ" ምንም ምክክርም ሆነ ንግግር አላደረግንም" በማለት የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ብቻ እንቅስቃሴውን እንደጀመሩ ነግረውናል።

ከምክር ቤቱ ጋር ግንኙነት ባይኖራቸውም በሚኖሩበት ሜኒሶታ ግዛት ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደ ጀመሩ የነገሩን ደግሞ የአንድ ጥብቅና ቢሮ ባልደረባ የሆኑት አቶ ነጋሳ ኦዱዱቤ ናቸው።

እርሳቸውም ከአቶ አምሳሉ ጋር ተመሳሳይ ኃሳብ ነው ያላቸው፤ 'ፈርስት አመንድመትን' ጠቅሰው የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩን ከሕግ ፊት ማቅረብ እንደሚቻል ያረጋግጣሉ።

"በአሜሪካ የመናገርና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ለብዙ ዘመናት የተከበረ ነው፤ ይሁን እንጂ 'ፈርስት አሜንድመንት' ላይ የተወሰኑ ገደቦች አሉበት" ይላሉ።

ከእነዚህም መካከል የሀሰት ንግግር፣ ስም ማጥፋት፣ ለወንጀል የሚያነሳሱ ንግግሮች፣ ወደ ኃይል ተግባር የሚያነሳሱና የሌላውን መብት የሚጥሱ ንግግሮች በሕጉ ተገድበው ይገኛሉ።

ተፅዕኖው ኢትዯጵያ ውስጥ በሚታይ ድርጊት ግለሰቦችን አሜሪካ ላይ ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚያዋጣ ክርክር ነው ወይ? ስንል የጠየቅናቸው አቶ ነጋሳ " የጁሪዝዲክሽን (የፍርድ ቤቶች የማየት ስልጣን) ጉዳይ አከራካሪ ነው። ነገር ግን ከሶ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ መከራከር ይቻላል፤ ውጤቱ ኢትዮጵያ ነው ብሎ መከላከል ይቻላል" ሲሉ ይህ በፍርድ ሂደት እንደሚታይ ይናገራሉ።

ከዚህም ባሻገር አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚኖረው ጥገኝነት ጠይቆ በመሆኑ ይህንን ከሚቆጣጠረው 'አሜሪካ ኢምግሬሽን ሰርቪስ' (ዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ) በክስ ሂደቱ ሊካተት እንደሚችል ይናገራሉ።

"እንደ ኢትዮጵያዊያን አገሪቷ ወደ ፍቅርና ሰላም እንድታመራ የሞራል ግዴታ አለብን" የሚሉት አቶ ነጋሳ ነገሩን ወደ ህግ ከመውሰድ ይልቅ የሚያዋጣው የኢትዮጵያ ደህንነት ግድ እንደሚለው ዜጋ መመካከር ነው ይላሉ።

Via #BBC
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠርንፈው ይመጣሉ...

"ወንድምን ከወንድሙ #በማጣላት፤ ብሔር ከብሔር #በማጋጨት እንደ ሃገር ለመቀጠል ፈታኝ ሆኗል፤ ይህንን የሚያደርጉ ግለሰቦችን ለማስተማር ብዙ እየተሞከረ ቢሆንም ነገሩ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ስለመጣ ምክር ቤቱ ግለሰቦቹን ወደ ህግ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል።" የኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ዜጎች ምክር ቤት/የህዝብ ግንኙነት አቶ #አምሳሉ_ፀጋዬ/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ብ/ጄኔራል #አሳምነውን ቀድቻቸዋለሁ" ጋዜጠኛ ፋሲካ ታደሰ ከBBC አማርኛ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ከታች ያንብቡት👇
https://telegra.ph/ብጄኔራል-አሳምነውን-ቀድቻቸዋለሁ-ጋዜጠኛ-ፋሲካ-ታደሰ-07-04
#update የኦሮሚያ ክልል የሰላምና የልማት ኮንፍረንስ ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገለፀ። የሰላምና የልማት ኮንፍረንስ ከነገ ጀምሮ በሁሉም የኦሮሚያ ክልል ዞኖች፣ የከተማ አስተዳድሮች እና ወረዳዎች የሚካሄድ መሆኑም ተገልጿል።

በኮንፍረንሱም በኦሮሚያ ክልል ሰላምን ስለማስፈን እና በክልሉ የህግ የበላይነትን ማስከበር የሚሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚመከር የኦዲፒ ማእከላዊ ጽህፈት ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል።

እንዲሁም የክልሉን ህዝብ ከልማት ተጠቃሚ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመከርም ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል፣ ያጋጠሙ ችግሮችን በመቅረፍ በአንድነት በመሆን የጋራ አቋም መያዝ ላይ ውይይት እንደሚደረግም አስገንዝበዋል።

Via #fbc
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል #የተሻለ እና #አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ሕጋዊ ትጥቅን ‹‹የማስፈታት ሥራ እንደተጀመረ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ከእዉነት የራቀ ነዉ›› ተብሏል፡፡ ተጨማሪውን ያንብቡ👇

https://telegra.ph/አማራ-ክልል-ETHIOPIA-07-04
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ፦
https://telegra.ph/ከአማራ-ብሔራዊ-ክልላዊ-መንግስት-በወቅታዊ-ጉዳይ-ላይ-የተሰጠ-መግለጫ-07-04
በሩሲያ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር በመሆን የተሾሙት አምባሳደር #አለማየሁ_ተገኑ ሰኔ 26 ቀን 2011 ዓ.ም የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አቅርበዋል።

Via #EPA
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የትግራይ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት ማካሄድ ጀምሯል። #ትግራይ #ኢትዮጵያ

🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ነገ ከሲቪል ማህበራት መሪዎች ጋር ውይይት እንደሚያካሂዱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት  ጉባዔ አዳራሽ ነገ በሚካሄደው ውይይት የሲቪል ማህበራት መሪዎች ጋር ለዲሞክራሲ ግንባታ ውስጥ ስለሚጫወቱት ሚና እና እየተወሰዱ ስላሉ የህግ ማሻሻል ተግባራት ዙሪያ እንደሚወያዩ ታውቋል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው ሦስት ሺ የሚጠጉ በፌዴራል ደረጃ የተመዘገቡ ማህበራት ይገኛሉ፡፡

🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"መንግሥት አይወክለኝም ለሚሉ ወገኖች ምርጫ ምላሽ ይሰጣል" ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና #ተጨማሪውን_ያንብቡ👇

https://telegra.ph/መንግሥት-አይወክለኝም-ለሚሉ-ወገኖች-ምርጫ-ምላሽ-ይሰጣል-ፕሮፌሰር-መረራ-ጉዲና-07-04
#FakeNewsAlert

አቶ ንጉሱ ጥላሁን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ በሚል የተሰራጨው መረጃ #ሀሰት መሆኑ ተገለጸ፡፡ በዛሬው እለት አቶ ንጉሱ ጥላሁን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሁነው እንደተሾሙ በማህበራዊ የትስስር ገጾች በስፋት የተሰራጨው መረጃ #ስህተት መሆኑን አሐዱ ራድዮ እና ቴሌቪዥን ከአቅርብ ምንጮቼ አረጋግጫለሁ ብሏል። አቶ ንግሱ ጥላሁን የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ባለመሆናቸው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የመሆን እድላቸው ጠባብ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ አሀዱ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ልዩ ኃይል” የደህንነት ዋስትና ወይስ ፈተና

ይህን ተጭነው ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ልዩ-ኃይል-የደህንነት-ዋስትና-ወይስ-ፈተና-07-04

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት የፖለቲካ እስረኞችን #ለመፍታት ተስማማ፡፡ በወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱና በተቃዋሚ መሪዎች መካከል እንደገና በተጀመረው ድርድር ነው የፖለቲካ እስረኞችን ለመፍታት ስምምነት ላይ እንደተደረሰ የተገለጸው፡፡ ሽግግሩን በሚመራው የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ውስጥ እንማን ይካተቱ በሚለው ጉዳይ ሁለቱ ወገኖች ባለመስማማታቸው ድርድራቸው ተቋርጦ ነበር፡፡ ልዩነቱ እንዲቀረፍም #ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኅብረት ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ የፖለቲካ እስረኞችን ለመፍታት ስምምነት የተደረሰበት ውይይትም የጥረቱ ውጤት ማሳያ ነው ተብሏል፡፡ በስምምነቱ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንደሚፈቱ እንጂ መቼ እንደሚፈቱ አልተገለጸም፡፡

Via #ቢቢሲ
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሶማሊያ ከምዕራብ አፍሪቃዊቱ ጊኒ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች። መንስኤው ጊኒ የሶማሌላንድ ፕሬዝደንትን ቀይ ምንጣፍ ዘርግታ መቀበሏ ነው። ድርጊቱ የሶማሊያን ሉዓላዊነት የጣሰ፤ አንድነቷንም የሚፈታተን ነው ስትል ከሳለች።

Via #DW
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰኔ 15 ጦር ሀይሎች አካባቢ ምን ተከሰተ?
/ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/

ሰኔ 15 ቀን አመሻሽ ላይ በአማራ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ውስጥ ቦሌ አካባቢ የተከሰተው ግርግር እና ግድያ ብዙ ትኩረት ቢስብም #ጦር_ሀይሎች በተለምዶ ሲግናል (በድሮ አጠራሩ #መኮ) የተከሰተው ሁነት ግን እስካሁን ይፋ አልሆነም።

ጋዜጠኛ ኤልያስ ቢያንስ ሶስት ምንጮች አረጋገጡልኝ እንዳለው ጦር ሀይሎች አካባቢ በነበረው ግጭት ሁለት ወይም ሶስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። እስከ ለሊቱ ስድስት ሰአት ገደማም የጥይት ተኩስ ይሰማ ነበር። ይህ ክስተት በእለቱ ከነበሩት ሌሎች ግድያዎች ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ግልፅ አይደለም።

በቅርቡ ስለ ጉዳዩ በAPው ጋዜጠኛ የተጠየቁ አንድ የመንግስት የስራ ሀላፊ "ስለ ጉዳዩ መረጃ የለኝም። አጣርቼ መልስ ልሰጥህ እሞክራለሁ" የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።

በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ አለኝ ያለ አንድ ግለሰብ ለጋዜጠኛው ተከታዩን መረጃ አቀብሎ ነበር፦

"ስለ ሰኔ 15ቱ (የጦር ሀይሎች አካባቢ ጉዳይ) የተወሰነ መረጃ አለኝ። መረጃውን ላገኝ የቻልኩት ደግሞ በዛ ምሽት ከሞቱት ሶስት የፌዴራል ኮማንዶዎች አንዱ የአክስቴ ልጅ ስለነበር ሬሳ ለመቀበል ከቤተሰብ ጋር በሄድንበት ጊዜ የአሟሟቱ ጉዳይ ስለተነገር ነው። እናም ጉዳዩ ከጀነራሎቹ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠረ አንድ ኮሎኔል ለመያዝ በሄዱበት ጊዜ በተፈጠረው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ነው። ግን እስካሁን አንድ የመንግሥት አካል ስለ ጉዳዩ ምንም ነገር አለማለታቸው እጅግ በጣም አሳዝኖኛል።"

Via #EliasMeseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአርባ ምንጭ ከተማ በወንጀል የተጠረጠሩ ከ100 በላይ ግለሰቦች ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ከ160 በላይ የባለሦስትና ባለሁለት እግር ባጃጆችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ #ተጨማሪ👇
https://telegra.ph/በአርባ-ምንጭ-በወንጀል-የተጠረጠሩ-ከ100-በላይ-ግለሰቦች-ምርመራ-እየተደረገባቸው-ነው-07-04
#update የፊታችን ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓም የሲዳማ ሕዝብ ደቡብ ከሚባል ድሪቶ ውስጥ ለማደር የማይገደድበት እና በራሱ ዕጣ ፈንታ ላይ በራሱ ምክር ቤት ራሱ ብቻ የወሰነበትን ውሳኔ የሚያጸናበት ቀን ነው ሲል ኤጄቶ የተባለው የሲዳማ የመብት አቀንቃኝ ቡድን አስታወቀ።

ቡድኑ ዛሬ በሐዋሳ ከተማ ከአባላቱ እና ከደጋፊዎቹ ጋር መወያየቱን በመግለፅ የሲዳማ ሕዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ዙሪያ ያለውን አቋም በማኅበራዊ ድረ ገጹ ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መግለጫው አንዳመለከተው የሲዳማ ኤጄቶች የሲዳማ ጥያቄ እና ጥያቄው የሚፈታበት ዴሞክራሲያዊ መንገድ ሀገራዊ ለውጡን በማይናድ መሠረት ላይ የሚገነባና ኅብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝሙን የሚያጠናክር ኩነት መሆኑን እናምናለን ብሏል።

የሲዳማ ክልል ጥያቄን አስመልክቶ ከየትኛውም አካል የሚሰጥ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ፡ ምላሽ ምንም አይነት ተቀባይነት አይኖረውም ያለው መግለጫው ጥያቄያችንን እና ውሳኔያችንን ለመቀልበስ የሚነዙ #ማስፈራሪያዎች እና #ዛቻዎች የሲዳማን ሕዝብ ጥንታዊ የጀግንነት ስነልቦና በጉልህ ካለመገንዘብ የሚመነጩ ተራ ፉከራዎች እንደሆኑ እንገነዘባለን ሲልም አትቷል።

የሲዳማን ሕዝብ የነጻነት ቀን ለማጨለም እና ሃሳቡንም በተንሸዋረረ መልኩ የተረዱ አካላት ይህን ቀን የዓለም ፍጸሜ በማስመሰል የሚያሰሙትን ተራ ፕሮፓጋንዳ አምርረን እንቃወማለን ሲል ገልጿል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ ውስጥ በየክልሉ የሚታዩ ሽኩቻዎች የሀገሪቱን አለመረጋጋት #እንዳያባብሱት ዓለም አቀፉ የቀውስ አጥኚ ቡድን አሳሰበ። ደቡብ ኢትዮጵያ ላይ የሲዳማ ሕዝብ መሪዎች ለጥያቄያቸው የፌደራል መንግሥትን #አዎንታዊ ምላሽ ካላገኙ ከፊል ራስገዝ አስተዳደርነትን በመጪው ሐምሌ አጋማሽ ለማወጅ መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል። ለተባለው ወሳኝ ቀን የሁለት ሳምንታት ዕድሜ ቢቀርም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ሕዝበ ውሳኔ እንዲሰጥበት ቀን እንዳልቆረጡ እና ዝግጅትም እንዳላደረጉ ቡድኑ ይፋ ባደረገው ዝርዝር ዘገባ ጠቅሷል። ጉዳዩ በአግባቡ ካልተያዘ የሀገሪቱ ጥምር መሪ ፓርቲ የገጠመውን ቀውስ ሊያባብስ እንደሚችል ክራይስስ ግሩፕ አመልክቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የግንባሩ መሪዎች ከሲዳማ ሕዝብ መሪዎች ጋር የሚግባቡበትን መንገድ እንዲፈልጉ እና ቆየት ብለውም ለሕዝበ ውሳኔው ቀን መቁረጥ እንደሚያስፈልግ አመልክቷል።

https://www.crisisgroup.org/africa/horn-africa/ethiopia/b146-time-ethiopia-bargain-sidama-over-statehood

Via #DW
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጋምቤላ ክልል ለሚገኙ ስደተኞች የተላከውን ከ400 ኩንታል በላይ በቆሎና አልሚ ምግብ ወደ ባህር ዳር ሲጓዝ በጊዳ አያና ወረዳ በፖሊስ ተያዘ።

የምስራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ቡድን ተወካይ ኮማንደር አስመራ ቀነዓ እንዳስታወቁት ለደቡብ ሱዳን ስደተኞች የተባለው የምግብ ዕርዳታ የጫነው ተሽከርካሪ አቅጣጫ ቀይሮ ሲጓዝ በቁጥጥር ሥር ውሏል።

የሰሌዳ ቁጥር ኢት 3-81572ና ኢት-24720 ተሳቢ ተሽከርካሪ ሰሞኑን በቁጥጥር ሥር የዋለው  በጊዳ አያና ወረዳ ላሊስቱ አንገር ቀበሌ ውስጥ መሆኑን ገልጸዋል።

ከአደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን መረጃ በመነሳት በተደረገው ምርመራ ተሽከርካሪው ለስደተኞቹ የተላከውን 300 ኩንታል በቆሎና 101 ኩንታል አልሚ ምግብ ወዳልታሰበ ሥፍራ ሲያጓጉዝ እንደነበር ተረጋግጧል ብለዋል።

አሽከርካሪው ለጊዜው የተሰወረ ቢሆንም፤በፖሊስና በኅብረተሰቡ ተሳትፎ ክትትል ለሕግ ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ኮማንደር አስመራ ተናግረዋል።

በአሁኑ ጊዜ በቁጥጥር ሥር የዋለው ተሽከርካሪና ዕርዳታው በሌላ አሽከርካሪ ወደ ጋምቤላ በመውሰድ ለስደተኞቹ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

Via #ENA
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢንዱስትሪ ፓርኮች ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደሞዝ ዝቅተኛ በመሆኑ ከስራ የሚለቁት ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱ ተገለጸ። በበጀት ዓመቱ በመንግስት ከሚለሙ ሰባት ኢንዱስትሪ ፓርኮች 110 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ መገኘቱም ተገልጾል።

https://telegra.ph/በኢንዱስትሪ-ፓርኮች-የሰራተኞች-ፍልሰት-እየተባባሰ-መጥቷል-07-04
#update በቢጂአይ ኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉት አቶ ኢሳያስ ሃደራ ከኩባንያው መልቀቃቸው ተሰምቷል።

https://telegra.ph/በቢጂአይ-ኢትዮጵያ-ለረዥም-ጊዜ-ያገለገሉት-አቶ-ኢሳያስ-ከኩባንያው-መልቀቃቸው-ተሰማ-07-04