TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የደህንነት ካሜራዎቹ ስራ ጀመሩ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ ከቦሌ እስከ መስቀል አደባባይ ባለው ጎዳና ላይ የተተከሉ #የደህንነት_ካሜራዎች ስራ መጀመራቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ካሜራዎቹ የተተከሉት ከቦሌ ውስጠኛው አደባባይ እስከ መስቀል አደባባይ ባለው መንገድ ግራና ቀኝ በኩል የተተከሉ መሆናቸውን በኮሚሽኑ የአይሲቲ ኢንፍራስትራክቸር ዲቪዥን ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር #አንድነት_ሲሳይ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም በመዲናዋ የተለያዩ ጎዳናዎች ካሜራዎችን የመትከል እቅድ መኖሩን የጠቀሱት ሃላፊው ከቦሌ እስከ መስቀል አደባባይ ያሉት ካሜራዎች ከሶስት ቀናት በፊት ስራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።

የካሜራዎቹ ቀረፃና የቁጥጥር ስራውም ያለምንም መቆራረጥ ሌት ከቀን እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ የቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ዳይሬክተር ተወካይ ኮማንደር ሁነኛው አየነው ከዚህ በፊት በመዲናዋ ውስን አካባቢዎች የነበሩ ካሜራዎች ከመንገድ ስራ ጋር ተያይዞ መነሳታቸውን አስታውሰዋል።

ሆኖም አገልግሎቱ ዳግም መጀመሩ አዲስ አበባ የበርካታ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መቀመጫ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የተጠናከረ ጥበቃ ለማድረግ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

የደህንነት ካሜራ አገልግሎት የብዙ ተቋማትን ቅንጅትና በርካታ መዋለንዋይ የሚፈልግ በመሆኑ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በአንድ ጊዜ ማዳረስ አዳጋች ቢሆንም በቀጣይ ግን በተለይ የኢንዱስትሪ መንደሮች ባሉባቸው ከተሞች ማስፋፋት ያስፈልጋል ብለዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእርቀ ሰላም ውይይት ተጀመረ!

በምዕራብ ጎንደር ዞን ነጋዴ ባሕርና አካባቢው የሚኖሩ #የአማራና #የቅማንት ህዝቦች ተወካዮች የእርቀ ሰላም ውይይት ጀምረዋል፡፡ ውይይቱ ነጋዴ ባሕር ከተማ ላይ ነው እየተካሄደ ያለው፡፡ የእርቀ ሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ያደረጉት ከሁለቱም ወገኖች የኃማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ናቸው፡፡ የውይይቱም ዓላማ አሁን ላይ ያለው #አለመግባባት እንዲያበቃና ወደቀደመው መከባበርና አንድነት ለመመለስ ነው፡፡ የሰዎች ሞትና የንብረት ውድመት እንደማይጠቅምና ተጎጅዎችም ራሳቸው መሆናቸውን ተወያዮቹ ተናግረዋል፡፡

#ከግጭት ይልቅ የቀደመውን #አንድነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት፡፡ ‹‹የጥፋቱ መንስኤ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ከሆነ ህግን ተከትሎ መንግስት ሊፈታው ይገባል፤ እኛ ሰላማዊ ነዋሪዎች ነን፤ ሰላማችንን ልንጠብቅ ይገባናል›› ነው ያሉት፡፡ በጥፋቱ የሚጠየቁ ግለሰቦች ካሉም በጋራ ሆነን ተጠርጣሪዎችን ለህግ እንዲቀርቡ እናደርጋለን ብለዋል ተወያዮቹ፡፡

‹‹መንግስት የሚደርሰው ጥፋት ከተከሰተ በኋላ ነው፤ ስለዚህ ለጥፋቱ የድርሻውን ይውሰድ፤ እኛም ችግሩን ወደ ሌላ ሳንገፋ የድርሻችንን ልንወስድ ይገባል›› ብለዋል፡፡ ለዘራፊዎች በራቸውን መክፈት ሳይሆን ሰላማቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡

የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል #አማረ_ገብሩ በውይይቱ ላይ ተገኝተው የሀገር መከላከያ ሰራዊት #ህይዎትን_ለማትረፍ ቅድሚያ እንደሚሰጥ አረጋግጠውላቸዋል፡፡ ‹‹ሕዝብ ከሌለ ሀገር የለም፤የህግ የበላይነትን ለማስከበር የሚችል መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው አለ፤ ከሕዝብ የምንጠብቀው ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠትና ለችግሮች መፍትሔ መስጠት ነው›› ብለዋል፡፡ ሰራዊቱን ሕዝቡ እንዲደግፈውም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

#በእርቀ_ሰላም ውይይቱ እንዲሳተፉ ከአካባቢው 16 ቀበሌዎች ጥሪ ቀርቦላቸው እንደነበር ተገልጧል፡፡ አብዛኛዎቹ ተሳትፈዋል፤በተለያዩ ምክንያቶች ከሁለቱም ወገኖች ለውይይት ያልተገኙ የቀበሌ ተወካዮችም አሉ፡፡ ሁሉን አቀፍ የጋራ መግባባት እንዲኖር ለማድረግም ለየካቲት 15/2011 ዓ.ም ሕዝባዊ ውይይት ለማካሄድ ቀጠሮ ተይዞ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጉዞ ሉሲ~ለሰላምና ለፍቅር!

‹‹ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር መርሀ-ግብር›› ትላንት ምሽት በሚሊኒዬም ተጀምሯል፡፡ በዝግጅቱ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር #ሂሩት_ካሰው ‹‹ዘረኝነት፣ መለያዬት፣ ማግለልና ንፉግነት የኛ የኢትዮጵያዊነት ባሕል አይደለም፡፡ ከዛሬ ጀምሮ የነበረንን መተዛዘን፣ #ፍቅርና #አንድነት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ለውጥ የሚጀምረው ከራስ ነውና ለለውጥ እዘጋጃለሁ፤ ለለውጥ እንዘጋጅ›› በሚል #የአንድነት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

በመርሀ-ግብሩ ከአፋር ክልል ጀምሮ በተለያዩ ክልሎች ሉሲ የአምስት ቀናት ቆይታ እያደረገች ሕዝቡ #በአንድነቱ ዙሪያ እንደሚወያይ የገለጹት ሚኒስትሯ ‹‹ሉሲንና ሌሎች አንድ የሚያደርጉን በዩኔስኮ የተመዘገቡ ቅርሶችን በታላቅ ክብር ከብሔራዊ ሙዚዬም ወደ ፓርላማ አጓጉዘን ወደ አፋር በመሸኘት ይጀመራል›› ነው ያሉት፡፡

ሉሲ የእገሌ የሚባል ሃይማኖት፣ ብሔር፣ አስተሳሰብ ወይም ሌላ #ወካይ_ያልሆነች የሁሉም የሰው ዘር ግንድ መሆኗን የጠቀሱት ሚንስትሯ ‹‹ደግነትና አብሮነት ስላልተለየን በጎ ትሩፋት ሳይሠራ የሚውል #ኢትዮጵያዊ የለም፡፡ የትኛውም ኢትዮጵያዊ የተራበ ሳያበላ፣ የተጠማ ሳያጠጣ፣ የወደቀ ሳያነሳ፣ የሞተ ሳይቀብር አይውልም፤ ኢትዮጵያዊነትም ይህ ነው›› ብለዋል፡፡ እንኳን እርስ በእርስ ከሌላውም ዓለም ጋርም ኢትዮጵያዊ በሉሲ የተዛመደ መሆኑንና #ዘረኝነት የኢትዮጵያዊነት ባሕል አለመሆኑን ነው ዶክተር ሂሩት ያስገነዘቡት፡፡

በመርሀ-ግብሩ መክፈቻ ዝግጅት በአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አዳራሽ አንጋፋና ወጣት ድምጻውያን የሙዚቃ ዝግጅቶቻቸውን አቅርበዋል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአንድነት ጥሪ ለመላው ኢትዮጵያዊያን!

‹‹ዘረኝነት፣ መለያየት፣ ማግለልና ንፉግነት የኛ የኢትዮጵያዊነት ባሕል አይደለም፡፡ ከዛሬ ጀምሮ የነበረንን #መተዛዘን#ፍቅርና #አንድነት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ለውጥ የሚጀምረው ከራስ ነውና ለለውጥ እዘጋጃለሁ፤ ለለውጥ እንዘጋጅ›› ዶክትር #ሂሩት_ካሳው

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እኛስ

የጥንት አባቶቻችን ያለብሄር፣ ያለዘር፣ ያለቋንቋ፣ ያለሀይማኖት ልዩነት ወራሪውን የጣልያን ጦር አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው፤ በደም በአጥንታቸው ይህቺን ሀገር #አስከብረው ለኛ #አስረክበውናል

የዛሬዎቹ ትውልዶች እኛስለቀጣዩ ትውልድ ምን ይሆን የምናወርሰው? የትኛዋን ሀገር ነው የምናወርሰው?

ወገኖቼ ለመጪው ትውልድ ክፍፍል እናውርስ? አንድ የሚያደርገንን ሰውነትን ረስተን በብሄር መቧደንን ለልጆቻችን እናውርስ? ንገሩኝ...በዘር መከፋፈልን እናውርስ? አለመከባበርን እናውርስ?? መሰዳደብን እናውርስ? ቁጭ ብሎ ማውራትን እናውርስ? አለመደማመጥን እናውርስ?

ቆይ ምን ሰርተን አለፍን እንበል

አድዋ የነፃነት ምልክት ብቻ አይደልም፤ አድዋ የኢትዮጵያዊያን #አንድነት እና ጠንካራ #ትስስር መገለጫም ጭምር ነው።

አድዋን ስናከብር...እኛስ ለቀጣዩ ትውልድ ምን እናውርስ? እኛስ ለኢትዮጵያ ምን ሰርተን እንለፍ? የሚሉትን ጥያቄዎች እራሳችንን #እየጠየቅን መሆን አለበት።

በTIKVAH-ETH ስም ሁላችሁንም እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ!

ሰላም፤ ፍቅር፤ አንድነት!
#Adwa123 #አድዋ123
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እኛ ኢትዮጵያዊያን በየትኛውም መንግሥት፣ በየትኛውም መሪዎች ዘመን ከልዩነት ይልቅ #አንድነት፣ ከግል ጥቅም ይልቅ የሃገርን የምናስቀድም፣ #ከከፋፋይ አሉባልታ ይልቅ ስለ አንድነትና የጋራ እሴቶቻችን የምንገዛ ታላቅ እና ኩሩ ሕዝቦች ነን። ለዚህም አንዱ ምስክር የአባቶቻችን፣ የአያቶቻች ገደል ነው።" ኢ/ር ታከለ ኡማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech-ኩልፎ ካምፓስ👆

#በኩልፎ_ካምፓስ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ከTIKVAH-EHT ጋር በመተባበር ያዘጋጀው #የStopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። የStopHateSpeech አስተባባሪዎችን #ቴዎድሮስ_ዮሴፍ የተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለው ተቀብለዋል። በዝግጅቱ ላይ ዶ/ር #ይስሀቅ_ከቸሮ የኮሌጅ ዲን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ የተቋማቸው ተማሪዎች የሀገሪቱን #አንድነት ከሚሸረሽሩ ግለሰቦች ጋር #መታገል እንዳለባቸዉ እና በቀጣይም የሀገሪቱ እጣ ፈንታ #በወጣቶች ላይ መሆኑን አውቀው የሚዲያ አጠቃቀማቸውን እንዲያስተላካክሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ማስታወሻ🗓በነገው ዕለት #ተመሳሳይ መድረክ #በአባያ_ካምፓስ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል!! #አርባምንጭ_ዩንቨርስቲ

የአርባምንጭ ተማሪዎች ተቀላቀሉ👇 @tikvahethamu @tikvahethamu

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህብረ ብሄራዊቷን ኢትዮጵያ አትፈልጓት እኛ ውስጥ ናት ይሏችኃል የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች! #ሰላም #ፍቅር #አንድነት

ከፈጣሪ ቀጥሎ ኢትዮጵያን የሚታደጓት እኚህ👆ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል #የተሰባሰቡ የፍቅር እና የሰላም አምባሳደር ወጣቶች ናቸው።

የሀገሬ ሠዎች አትስጉ፤ ተስፋም አትቁረጡ በፍቅር አትዮጵያን ትልቅ እናደርጋታለን!! አርማችን ነጩ የሰላም ምልክት!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአንድ እናት ልጆች ነን መስመር አይለየን...
የአንድ ቤት ልጆች ነን መስመር አይለየን...

#መቐለ_ዩኒቨርሲቲ የሰላም አምባሳደር!
#ፍቅር #ተስፋ #አንድነት #መቐለ_ዩኒቨርሲቲ
#አዲስ_አበባ: "መልካም ወጣት ለኢትዮጵያ #አንድነት 2011" የተሰኘ በአገልጋይ #ዮናታን_አክሊሉ የሚዘጋጅ የወጣቶች መርሃ ግብር #በትላንትናው ዕለት በሚሊኒየም አዳራሽ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በተገኙበት መከፈቱ ተሰምቷል። በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የገቢዎች ሚንስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተገኝተው ነበር።

🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የድጋፍና የልማት ማህበር አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እገዛችንን ከፈለገ ከጎኑ እንቆማን አለ፡፡
.
“የደርግ ሰራዊት” የሚለው የበፊት መጠሪያው “የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት” በሚል ተቀይሮ ከመንግስት እውቅና እንደተሰጣቸውም የማህበሩ መሪዎች ተናግረዋል፡፡ “አሁንም የኢትዮጵያን #አንድነት ለማስጠበቅ ከቆመ መንግስት ጋር አብረን ለመስራት ዝግጁ ነን” ብለዋል፡፡

በመላው አገሪቱ 53 ቅርንጫፎች እንዳሉት ተነግሯል፡፡ የማህበሩ ሀላፊዎች በአጠቃላይ ከ1 ሚሊዮን በላይ አባላት አሉት ማለታቸውን ከጋዜጣዊ መግለጫው ሰምተናል፡፡ ማህበሩ ከቀድሞዎቹ ሚሊሺያዎች እስከ ከፍተኛ የጦር መኮንንነት የደረሱ አባላት እንዳሉት ተነግሯል፡፡

ምንጭ - ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕለቱ መልዕክት፦

ከጭፍን ጥላቻ መላቀቅ ይቻላል!

አብዛኞቹ ሰዎች ጭፍን ጥላቻን በመሠረተ ሐሳብ ደረጃ የሚያወግዙ ቢሆኑም ከጭፍን ጥላቻ መዳፍ የሚላቀቁ ግን ጥቂቶች ናቸው። እንዲያውም ሥር የሰደደ ጭፍን ጥላቻ ያላቸው ብዙ ሰዎች ጥላቻ እንደሌላቸው ሊናገሩ ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ ሰዎች ጭፍን ጥላቻቸውን ይፋ እስካላወጡ ድረስ ምንም ጉዳት የለውም ይላሉ።

ይሁን እንጂ ጭፍን ጥላቻ ሰዎችን የሚጎዳና የሚከፋፍል መጥፎ ነገር ነው። ጭፍን ጥላቻ የድንቁርና ልጅ ነው ቢባል የልጅ ልጁ ደግሞ ጠላትነት ነው። ቻርልስ ካለብ ኮልተን የተባሉት ደራሲ (1780-1832) “አንዳንድ ሰዎችን ስለማናውቃቸው #እንጠላቸዋለን። ስለምንጠላቸውም #ልናውቃቸው አንችልም” ብለዋል። ጭፍን ጥላቻን ሰዎች መማር እንደሚችሉ ሁሉ ማስወገድም ይችላሉ።

Via #JW

#ፍቅር #ሰላም #አንድነት #ተስፋ #ኢትዮጵያ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA💪ክብር ይገባችኃል!

ስንተባባር በአንድነት ስንቆም ምንም ነገር አያቅተንም!! 6710 የልብ ህሙማን ህፃናትን አለንላችሁ እንበላቸው!!

#TIKVAH_ETHIOPIA_FAMILY

Screenshot ወደዚህ ግሩፕ👇

https://publielectoral.lat/joinchat/FCD9AhWFZJX_rX95-4rWNQ

#አንድነት #ተስፋ #መተሳሰብ #ፍቅር #ቲክቫህ
❤️ከ3000 በላይ አባል❤️

6710 ላይ የህፃናት የልብ ህክምናን ለማገዝ በተከፈተው ግሩፕ ላይ እስካሁን ከ3 ሺህ የሚበልጡ የቤተሰባችን አባላት ተቀላቅለውናል!! በሺዎች የሚቆጠር ገንዘበ እንደ አቅማችን አስተዋፆ እያደረግን እንገኛለን!! ሀገር ወዳድነት መገለጫው ይህ ነው!!

Screenshot ወደዚህ ግሩፕ👇

https://publielectoral.lat/joinchat/FCD9AhWFZJX_rX95-4rWNQ

እኔ ካለኝ ላይ አካፍያለሁ?? እናተስ??

ለአንድ መልዕክት የሚቆርጠው 1 ብር ብቻ ነው!!


በትንሹ 3 መልዕክት ይላኩ!

#አንድነት #ተስፋ #መተሳሰብ #ፍቅር #ቲክቫህ
#UnityPark

መደበኛ የክፍያ ጉብኝት ከነገ ሰኞ ይጀምራል!

ከነገ ሰኞ ማለትም ከጥቅምት 3 2012 ጅምሮ ማንኛውም ዜጋ 200 ብር እንዲሁም በቪአይፒ (VIP) 1 ሺህ ብር በመክፈል ቤተ መንግስቱን መጎብኘት ይችላል።

የአንድነት ፓርክን ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ይዞ መገኘት ሲኖርበት በተጨማሪም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመሁኔታዎች ካላሟሉ ፓርኩን መጎብኘት አይችሉም።

ጎብኚዎች ይዘው መምጣት የሌለባቸው ነገሮች፦

- ስለት
- ተቀጣጣይ ቁሶች
- የጦር መሳሪያዎች
- ምግብ መጠጦች እና ጣፋጭ ነገሮች
- ማስቲካ
- የመዋቢያ ቁሶች
- የግል ካሜራዎች
- ስልኮች ታብሌቶች እና ማንቸውንም የምስልና ድምጽ መቅረጫ መሳሪያዎችን
- ሲጋራ እና አደንዛዥ ዕጾች

በፓርኩ ውስጥ ማድረግ የተከለከሉ ተግባራትና ባህሪያት፦

- መጮህና መረበሽ
- ከአስጎብኚ ውጪና ከተመደቡበት የጉብኝት ቡድን ውጪ መንቀሳቀስ
- በታሪካዊ ህንጻዎቹ ላይ መደገፍ
- ቅርሶችንና እንስሳትን መነካካት
- እንስሳትን ከተፈቀደው ቦታ ውጪ መቅረብ
- እንስሳትን መመገብ
- እንስሳትን ማስቆጣት (ጠጠር መወርወር፣ በአካላዊ እንቅስቃሴ ማስፈራራት፣ አላስፈላጊ ድምጽ ማውጣት)
- ከተቀመጡ የቆሻሻ ማስወገጃ እቃ ውጪ ቆሻሻ መጣል
- ሲጋራና ሌሎች አደንዛዥ እጾችን መጠቀም
- የቤት እንስሳትን ይዞ መምጣት
- መንገድ ከተበጀለት ዉጪ መራመድ እና አጥሮችን ከልክ በላይ መጠጋትም ሆነ መደገፍ
- ማንኛዉንም በፓርኩ የሚገኝ የኤሌትሮኒክስ ቁስ ያለፍቃድ መንካት

#አንድነት_ፓርክ
#UnityPark

@tsegabwolde @tikvahethiopia