TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጉዞ_ዓድዋ_6🔝

ታላቁን የዓድዋ ድል ለመዘከር በየአመቱ የሚካሔደው የእግር ጉዞ ዘንድሮም ለ6ኛ ግዜ ቀጥሏል። ከሐረርና አዲስ አበባ የተነሱት ተጓዦች በድምሩ ከሺህ በላይ ኪሎሜትሮችን አቋርጠው #መቐለ_ከተማ እንደገቡ ታላቁን ኢትዮጵያዊ ጀግና ራስ አሉላ እንግዳን (አባ ነጋ) ለማስታወስ የሽሬ ልጆች መቐለ ከተማ በመግባት የአዲስ አበባ እና የሐረር ተጓዦችን ተቀላቅለዋል።

ብዛታቸው 5 የሆኑት #የሽሬ_ልጆች ከመቐለ እስከ ዓድዋ እናት ሀገራቸው ኢትዮጵያን እና ታላቁን የዓድዋ ድል ለማግዘፍ እንደ ታላቁ ራስ አሉላ አባ ነጋ ከወንድም እህቶቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
"ታሪካዊ #ጀግኖቻችን የልዩነታችን ምክንያት ሳይሆኑ የአንድነታችን መሰረት ናቸው"

#ፍቅር_ለኢትዮጵያ !!
#የምናቋርጣቸው_የሀገራችንን_መንደሮች_እንጂ_ድንበሮች_አይደለም
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም

Via Yared Shumete
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜጀር ጄኔራል መሀሪ ዘውዴ🔝

ሜጀር ጄኔራል መሀሪ ዘውዴ ገ/ማሪያም የአብዬ #ጊዚያዊ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት #የጦር_ሀይል_አዛዥ ሆነው መሾማቸውን የተባበሩት መንግስታት ሴክሬታሪ ጄኔራል አንቶኒ ጉቴሬዝ አስታወቁ፡፡ ሜጀር ጄኔራል መሀሪ እንደ እ.ኤ.አ በሚያዝያ 23/ 2019 የስራ ጊዚያቸውን የሚያጠናቅቁትን ሜጀር ጄኔራል ገብሬ አድሃና ወልደዝጉን ተክተው ይሰራሉ ተብሏል፡፡

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለተሰናባቹ ሜጀር ጄኔራል ገብሬ አድሃና ደከመኝ ሳይሉ ላደረጉት አገልግሎትና በተመድ ለነበራቸው ውጤታማ የአመራር ጊዜ #ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ጄኔራል ሴክሬቴሪያቱ በንግግራቸው ሜጄር ጄኔራል መሀሪ ዘውዴ ከኢትዮጵያ የታጠቁ ሀይሎች ጋር በመሆን ለ37 ዓመታት ማገልገላቸውን ገልጸው በቅርቡ የኢትዮጵያ የመከላከያ የሰው ሀይል ኃላፊ በመሆንና ለምድር ጦሩ እና ለአጠቃላይ የመከላከያ ሀይሉ የሰው ሀይልና የአስተዳደር ስራ በሀላፊነት መስራታቸውን አክለዋ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የመከላከያ ሚኒስቴር የአማካሪ አባል በመሆን ከ2007 ጀምሮ ሰርተዋል፡፡

ለኢትዮጵያ አየር ሀይል ከ2001-2007 ምክትል ኮማንደር፣ ለምስራቁ የአየር ሀይል ዕዝ በኮማንደርነት በ1989-1997 እና በሌሎች ተሳትፎዎችም ከኢትዮጵያ ታጣቂ ሀይሎች ጋር አገልግለዋል፡፡ሜጀር ጄኔራል መሀሪ ዘውዴ በብሪታንያ ከሚገኘው ግሪን ዊች ዩኒቨርስቲ በሳይንስ የማሰተርስ ድግሪ አግኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ላለፉት 2 ሳምንታት ዝግ ሆኖ የቆየው የጎንደር-መተማ/ሱዳን መንገድ #አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። መንገዱ የተዘጋው በአካባቢው ግጭት መከሰቱን ተከትሎ ታጣቂዎች አሽከርካሪዎችንና መንገደኞችን በማገት የማስለቀቂያ ገንዘብ መጠየቅ በመጀመራቸው ነበር።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው #63ኛ_መደበኛ_ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ #ውሳኔ አሳልፏል፡፡

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጦር መሳሪያን ጨምሮ ግምታዊ ዋጋቸው 5 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በኦሮሚያ ክልል #ጭናቅሰን_ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በቁጥጥር ስር የዋሉት ዕቃዎች 3 ሽጉጥ፣ አንድ ማይክሮስኮፕ፣ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች፣ መድሃኒቶች፣ የሞባይል ቀፎዎች እና ሌሎች የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ናቸው። የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የሰሌዳ ቁጥራቸው ኮድ3-04677 ሱማ፣ 3-A59728 አአ እና 3-04878 ድሬ በሆነ ተሽከርካሪዎች ሲንቀሳቀሱ በኦሮሚያ አድማ ብታኝ ፖሊስ፣ በመከላከያ ሰራዊትና በጉምሩክ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የድሬደዋ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት አስታወቋል። ቅ/ፅ/ቤቱ እንዳለው ተጠርጣሪዎቹ ለጊዜው #ቢሰወሩም ክትትል እየተደረገባቸው ይገኛል።

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታጣቂዎች ሁለት ሰዎችን ገደሉ‼️

በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ዛሬ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሁለት ሰዎች መገደላቸውን የዐይን ዕማኝ እና የወረዳው ባለሥልጣን አስታወቁ። ጥቃቱ የተፈጸመው ወረዳውን ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን በሚያዋስነውና #ጎልቤ በተባለ ሥፍራ ላይ ነው።

ጥቃቱን ተከትሎ በአካባቢው የሚገኘው መከላከያ ሠራዊት ወደ ሥፍራው በመንቀሳቀስ #ከበባ ማድረጉ ታውቋዋል፡፡ በሥፍራው የነበሩ የአይን እማኝ እንዳረጋገጡት ሠራዊቱ በሥፍራው ከመድረሱ አስቀድሞ የታጠቁ ቡድኖች ወደ መንደሩ በመግባት በነዋሪዎች ላይ #ተኩስ ከፍተዋል፡፡

አንድ የመንደሩ ነዋሪ "አማሮ ወረዳ ጎልቤ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ልዩ ስሙ ላፊፋ በተባለ ቦታ ነው ታላቅ ወንድሜ እና የታላቅ ወንድሜ ልጅ ከብት ከሚጠብቁበት ከማሳቸው ገብተው ጨፈጨፏቸው በቀብር ሥርዓት ላይ ነን ያለንው" ሲሉ ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ተናግረዋል።

የአማሮ ልዩ ወረዳ አስተዳደር የባህል ፤ ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ #አማረ_አክሊሉ "ዛሬ አራት ሰዓት ገደማ ላይ ነው የጸረ-ሰላም ኃይሎች ሰዎች የገደሉት። ታጣቂዎቹ ወደ አማሮ ወረዳ ጎልቤ ቀበሌ የመጡት ከገላና ወረዳ በኩል ነው" ሲሉ ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጠዋል። ኃላፊው በሰራዊቱ ክትትል ውስጥ መሆናቸውን የተረዱት ታጣቂዎቹ በገላና ሸለቆ ውስጥ ገብተው #መሰወራቸውንና ሠራዊቱም ወደ ጦር ሰፈሩ መመለሱን ገልጸዋል፡፡ "መከላከያ ሰራዊቱ ሁለት ሰው ከሞተ በኋላ መጥቶ ነበር። መከላከያ ሰራዊቶች መጥተው ክትትል አድርገው አላገኟቸውም። ወደ ኋላ ተመልሰው ወደ ካምፓቸው ተመልሰዋል። ታጣቂዎቹን ሊያገኟቸው አልቻሉም። ጫካ ነው የገቡት" ሲሉ አቶ አማረ ሁኔታውን ለጀርመን ራድዮ ጣቢያ አስረድተዋል።

በአካባቢው በተፈጸመው ጥቃትና በተካሄደው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ እስከአሁን ከአገር መከላከያ ሚኔስቴርም ሆነ ከፌደራሉ መንግሥት የተሰጠ #ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ የለም፡፡

በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ካለፈው የሰኔ ወር ጀምሮ የታጠቁ ሀይሎች በተደጋጋሚ በሚፈጽሙት ጥቃት እስከ አሁን ሰማኒያ አራት ሰዎች ሲሞቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ከወረዳው አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ:- የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በየቤታችን እንወያይ!

የዚህች ሀገር ችግር ተመዞ አያልቅም። ከእናተው ጋር ሆኜ ብዙ እየሰማው እና እያየሁ እንደመዋሌ ላለፉት 3 ዓመታትም በየቀኑ እዚሁ ከናተው ጋር መረጃዎችን ስቀባበል ስውል እንደተረዳሁት ትልቁ ችግራችን ስለሰው ክቡርነት በሀገራችን ብዙ ስራ አልተሰራም። ዛሬ ዝርፊያው፣ ማሳደዱ፣ መግደሉ፤ ማፈናቀሉ...የምንሰማቸው ዘግናኝ ኢ ሰብዓዊ ወንጀሎች ሁሉ ሰው ምን ምንድነው የሚለውን በጥልቀት ካለመረዳት የመጣ ይመስለኛል። አንድን ሰው በሰውነቱ ካከበርነው ብሄሩን፣ ዘሩን፣ ቋንቋን፣ ማንነቱን...ሁሉንም እናከብርለታለን።

#በጥቅም ተደልለንም፤ በግለሰቦች ቅስቀሳም ወገናችንን የምንጎዳውም፤ ሰው የምናፈናቅለውም፤ ሰው የምንጠላውም #ሰውነትን በአግባቡ ስላልተረዳን ነው። መጀመሪያ ሰው እንሁን! ሰው ስንሆን የሌላው ሞት የኛ፤ የሌላው ስቃይ የኛ፤ የሌላው በደል የኛ ...ይሆናል! ሰውን ሁሉ እንደራሳችን ማየት ስንጀምር #ሰላም እንሆናለን።

ስለአንድነት፣ ስለነፃነት ፣ስለዴሞክራሲ ለማውራት በቅድሚያ እውነት እኛ #ሰውነት_ገብቶናል?? ብለን ልንጠይቅ ይገባል። ሁላችንም በሰውነት ጥላ ስር ከተከለልን የስቃይ እና የመከራ ጊዜው ያጥራል።

•እንደመነሻ ሀሳቤን ገልጫለሁ እናተስ ምን ትላላችሁ...?

ሀሳባችሁ ገፁ ላይ እንዲለጠፍ...👇

•በአማርኛ ፅሁፍ አጠር አድርጋችሁ ሀሳባችሁን ማቅረብ ወይም

•በድምፅ ከ4 ደቂቃ ያልበለጠ በጨዋ ቋንቋ የግል ምልከታችሁን ብቻ በ @tsegabwolde መላክ ይቻላል!

🔹ሚቀድመውን እናስቀድም! ከምንም ነገር በፊት ሰውነት ይቀድማል!! እውነት እኛ የሌላውን ስቃይ እንደራሳችን እናያለን?? ወይስ እኛን ሊያስለቅሰን የኛ ዘመድ ወይም የኛ ብሄር ሰው መሆን አለበት??
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቢሾፍቱ...

"የእኔ ሐሳብ ከሐገራችን ትምህርት አሰጣጥ ሁኔታም ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም አብዛኛዎቹ የዚህ ዘመን መምህራን ለቀለም ልጆቻቸው ማርክ እንጂ በሰብእና እና እሴት ላይ ያተኮረ ትምህርት እየሰጡ አይደለም፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በዘመናችን ያሉ ሙዚቃዎች ስለ ዝሙት እና ማንነትን የሚያስረሳ እንጂ ሰለ ሐገር እና ስለ ሰው የሚዘፍን በጣም ውስን ነው፡፡ስለዚህ እነዚህን መልክ ማስያዝ ቢቻል እላለሁ፡፡
ዮናስ ነኝ ከቢሾፍቱ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአምቦ...

"አብዛኛው የሀገራችን አርቲስቶች ምን እየሰሩ እንዳሉ ሊገባኝ አልቻለም። ችግር ሲኖር ለመድረስ እና ለመጮኸ ከሆን ምንም ፋይዳ የለውም። በሞያቸውን እንዴት ህብረተሰቡን ስለሰውነት ስለሰላም አያስተምሩም። ገንዘብ መሰብሰብ ብቻ ምን ዋጋ አለው። ራሳቸውን ሰቅለው ከተቀመጡበት ወርደው በዚህ ፈታኝ ሰዓት ስለሰውነት ስለሰላም መስራት አለባቸው። ቢያስ ባለፉት አመታት አብዛኛዎቹ አርቲስቶች ብዙ ነገር ሀገሪቱ ውስጥ ሲሆን ዝም ብለው ቆይተዋል። አሁን ግን ከነሱ ብዙ ይጠበቃል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የ20 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ #ሳሙኤል_ተፈራ በበርሚንግሐም የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር የዓለም ክብረ-ወሰን አሻሻለ። ሳሙኤል ውድድሩን በ3 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ ከ04 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል። ላለፉት 22 አመታት አይነኬ ሆኖ የቆየው እና በሞሮኳዊው ሒሻም ኤል ጎሩዥ ተይዞ የነበረው ክብረ-ወሰን 3 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ ከ18 ማይክሮሰከንድ ነበር። ባለፈው ሳምንት ክብረ-ወሰኑን ለማሻሻል 0.01 ሰከንድ ብቻ ሲቀረው ውድድሩን ያጠናቀቀው ሌላው ኢትዮጵያዊ ዮሚፍ ቀጀልቻ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ዮሚፍ በዚህ ውድድር የዓለም ክብረ-ወሰንን የማሻሻል ዕቅድ ነበረው። የአውስትራሊያው ስቴዋርት ማክስዌይን ውድድሩን በሶስተኛነት አጠናቋል። ሳሙኤል ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ "ይኸን ማመን አልችልም። በውጤቱ ተደስቻለሁ። የዓለም ክብረ-ወሰን ባለቤት መሆን የተለየ ስሜት ይፈጥራል" ሲል ተናግሯል።

via dw
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በየቤታችን እንወያይ! የዚህች ሀገር ችግር ተመዞ አያልቅም። ከእናተው ጋር ሆኜ ብዙ እየሰማው እና እያየሁ እንደመዋሌ ላለፉት 3 ዓመታትም በየቀኑ እዚሁ ከናተው ጋር መረጃዎችን ስቀባበል ስውል እንደተረዳሁት ትልቁ ችግራችን ስለሰው ክቡርነት በሀገራችን ብዙ ስራ አልተሰራም። ዛሬ ዝርፊያው፣ ማሳደዱ፣ መግደሉ፤ ማፈናቀሉ...የምንሰማቸው ዘግናኝ ኢ ሰብዓዊ ወንጀሎች ሁሉ ሰው ምን ምንድነው የሚለውን በጥልቀት…
ከቡሌ ሆራ...

"እኔ እንደማስበው ሀገራችን ሰላም እንድትሆን ሁሉም ሰው ለአዕምሮው ሰላም የሚሰጠውን ተግባር መለየት አለበት። አዕምሯች ሰላም የሚያገኘው ሌሎች ላይ መጥፎ በማድረግ ነው ብለን ካሰብን አብደናል። በሌሎች ስቃይ ህሊናችን ደስታ የሚያገኝ ከመሠለን ልክ አደለንም። አዕምሯችን ሰላም የሚያገኘው ለሰወች መልካም በማድረግ እንጂ ሰወችን እያናከስንና ህሊናቸው ላይ መርዘኛ አስተሳሰብ በመተው እንዳልሆነ ማወቅ አለብን። ሁሉም ሰው ያለፈውን ጥሩም መጥፎም ተሪክ በበጎ ከመነዘርነው ሰላማችን በእጃችን ናት። ያኔ ኢትዮጵያ ውስጣቸው ሰላም ያላቸው ሰዎች የሚኖሩባት ሀገር ትሆናለች። ሰላም የሚጀምረው ከራስ ነው። ወርቅነህ ነኝ ከቡሌ ሆራ። አመሰግናለሁ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአርባ ምንጭ...

"ወንድሞቼ ከላይ ያነሱት ሀሳብ እዳለ ሁኖ የኔ እይታ #ሀይማኖት ተቋማት ላይ በደንብ መሠራት አለበት፡፡ ወጣቶች ሀይማኖቱን በሁለቱም አለም ስኬታማ የሚሆንበትን ጉዳይ ትቶ ዛሬ ገደል የሚከተውን መጤ መንገድ ተከትለናል። በተለይ ወጣቱን ወደ ሀይማኖቱ የማምጣት ስራ ቢሠራ በየቸርቹ፣ በየመስጅዱ ትምህርቱ ከአንድ ሰሞን የዘለለ ቢሆን ባይ ነኝ! ሙሀመድ ከአርባምንጭ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውድ የTIKVAH-ETH አባላት በተነሳው የውይይት ርዕስ ላይ እያቀረባችሁት ያለው ሀሳብ ይቀጥል?? እየተከታተላችሁ ነው?? ~~ አይቀጥል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከመቀለ...

"የሐገር መሠረት ቤተሰብ ነው፡፡ አያትና ቅድመ አያቶቻችን በአንድነት ና በፍቅር ሆነው የኢትዮጵያን እና የጥቁር ህዝቦችን #ነፃነት ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው አቀዳጁን፤ እኛ ታዲያ ልጆቻችንን እሕት ወንድሞቻችንን ከቤት እስከ ጎረቤት ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ድሮም #አንድ አድርጎ ያስተሳሰረን ውድ ፍቅራችንን ፣ #እሴቶቻችን መንገርና በተግባር ማሳየት ያቅተናል? እኛ የተሳሳተ አስተሳሰብ እንጂ #የሰው_ጠላት_የለንም፤ ሰው በሰውነቱ እኩል ነው ፤ የሃሳብ ልዩነቶቻችንን በሰከነና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍታት እየቻልን ጥላቻንና በቀልን በመዝራት ሞትን፣ ውድመትንና መከራን ስለምን እናጭዳለን?? እኛኮ ውድ የአፍሪካ የቁርጥ ቀን ልጆች ነን፤ እኛኮ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት አርማ ኩራታቸው ነን፤ አባቶቻችን በታላቅ መስዋዕትነት የገነቡትንና ያወረሱንን ድንቅ ታሪካችንን በመገዳደልና በመዘራረፍ ለአለም ሕዝብ #መሳለቂያ መሆን #ያሳፍራል፤ ተው ወገን ይህም ያልፍና ቀጣይ ትውልድ ይታዘበናል...የአገራችን ሰላም በእጃችን ነው አንድም ለማፍረስ አንድም ሰላማችንን ለማስቀጠል፡፡ አሸናፊ ግርማ ከመቖለ ዩኒቨርሲቲ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዳማ...

"እየተጠላላን አንዳችን ለአንዳችን #እየተደማማን መኖር #ይብቃን እባካችሁ ወገኖቼ መጪው ትውልድ ታሪካችንን አንብቦ እንዳይወቅሰን። ወንድም ወንድሙን ገድሎ #መፎከር ይብቃ እስቲ ተያይዘን አብረን እንደግ ሀገራችን በቂያችን ነች ከሀገር የወጡ ወገኖቻችን እኮ ወደው አይደለም ከሰራን ከተለወጥን እነሱም ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ቤታችን ይደምቃል። እህቶቻችን እኮ ወደው አይደለም ከሰው ሀገር የሚንከራተቱት ተባብረን ባለመስራታችን እንጂ አበቃሁ! #አላህ ሀገራችንን ሰላም ያድርግ! መሀመድ ከአዳማ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia