#update የጦር መሳሪያን ጨምሮ ግምታዊ ዋጋቸው 5 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በኦሮሚያ ክልል #ጭናቅሰን_ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በቁጥጥር ስር የዋሉት ዕቃዎች 3 ሽጉጥ፣ አንድ ማይክሮስኮፕ፣ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች፣ መድሃኒቶች፣ የሞባይል ቀፎዎች እና ሌሎች የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ናቸው። የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የሰሌዳ ቁጥራቸው ኮድ3-04677 ሱማ፣ 3-A59728 አአ እና 3-04878 ድሬ በሆነ ተሽከርካሪዎች ሲንቀሳቀሱ በኦሮሚያ አድማ ብታኝ ፖሊስ፣ በመከላከያ ሰራዊትና በጉምሩክ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የድሬደዋ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት አስታወቋል። ቅ/ፅ/ቤቱ እንዳለው ተጠርጣሪዎቹ ለጊዜው #ቢሰወሩም ክትትል እየተደረገባቸው ይገኛል።

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia