TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 58ኛ መደበኛ ስብሰባ በሶስት ረቂቅ ደንቦችና በስድስት የስምምነት ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ እንደሚከተለዉ ውሳኔ አሳልፏል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዱል በቁጥጥር ስር ዋለ‼️

ባለፉት ወራት በቤኒሻንጉል ክልል እየተንቀሳቀሰ ማሕበራዊ ሰላም #ሲያደፈርስ የነበረውና ከጸረ ሰላም ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ በርካታ ወንጀሎችን በመፈጸም የተጠረጠረው ግለሰብ ከትላንት በስቲያ #በፌደራል_ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ጉለሌ ፖስት ከምጮቼ ሠማሁ ብሎ ዘግቧል።

#አብዱል_ወሃብ የተባለውና የቤኒሻንጉል ነፃ አውጪ ግንባር ሊቀ መንበር የነበረው ይህ ግለሰብ ቀደም ሲል በኤርትራ ይንቀሳቀስ የነበረውን ግንባር ሲመራ ቢቆይም፤ በአገሪቱ በተፈጠረው ለውጥ ወደክልሉ ከተመለሰ በኋላ ለውጡን ለመቀልበስ ከሚፈልጉ ሃይሎች ጋር
በመቀናጀት በበርካታ ወንጀሎች ሲፈለግ መቆየቱን የጉለሌ ፖስት ምንጮች ጠቁመዋል።

አብዱል ወሃብ በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ከመዋሉ በፊት በፌደራልፖሊስ አባላቱ ላይ ተኩስ ከፍቶ ለማምለጥ ጥረት ያደረገ ሲሆን በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ተመቶ በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል።

እንደጉለሌ ፖስት ምንጮች ገለጻ ተጠርጣሪው #ለማምለጥ ባደረገው ጥረት የክልሉ ልዩ ሃይል የተወሰኑ አባላት ስልታዊ ድጋፍ ሲያደርጉለት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ...

በያዝነው ዓመት መጀመርያ ላይ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን እንግልት ለመከላከል ቄሮዎችን አደራጅታችኋል በሚል በቤኒሻንጉል ክልል እስር ቤት የሚገኙት ዘጠኝ አዛውንቶች እስካሁን ፍርድ ቤት ያለመቅረባቸውን የመረጃ ምንጮቼ ገልጸዋል ሲል ጉለሌ ፖስት ዘግቧል። በተለይ ኦቦ #ተስፋዬ_አመኑ እና ኦቦ #መላኩ_ቀጄላ የተባሉት አዛውንቶች በሕመም ላይ የሚገኙ መሆኑ በጣም አሳሳቢ እንደሆነባቸውና መንግስት አስቸኳይ እልባት እንዲሰጣቸው እኒሁ ወገኖች ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ጉለሌ ፖስት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለድሬዳዋ ነዋሪዎች፦

"የተከበራችሁ የድሬዳዋ ነዋሪዎች ታህሳስ
7-2011 ዓም ክቡር ጠ/ሚ #አቢይ_አህመድ በተገኙበት ታቅዶ የነበረው የኢንዱስትሪ ፓርክ ምርቃት ላልተወሰነ ጊዜ #የተራዘመ መሆኑን እንገልፃለን!"

©የከተማው ከንቲባ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በእጃችን ላይ ስላለው #ሰላም ዘላቂነት በአንድነት ተጠንክረን ልንሰራ ይገባል ሲሉ የሰላም አምባሳደር እናቶች ገለጹ። የሰላም አምባሳደሮቹ የልኡካን ቡድን አባላት ዛሬ #ጋምቤላ ሲገቡ በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

ወንጀሉ የተፈጸመው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ክልል ልዩ ቦታው ጉርድ ሾላ አካባቢ ሚያዚያ 9 ቀን 2007 ዓ.ም ሲሆን ተከሳሽ በ1996 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 669/2/መ/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ነው ክስ የተመሰረተበት፡፡

የክሱ ዝርዝር ሁኔታ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ በቀለ በራሶ ኩኑሬ በ1ኛ ክስ ለጊዜው ካልተያዙ ግበረ-አበሮች ጋር በመሆን በላዮን ሴኩሪቲ ሰርቪስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አማካኝነት ከህዳር 2007 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 9/2007 ዓ.ም በጥበቃ ሰራተኛነት #የጁፒተር_የንግድ_ስራ_ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ በሚሰራበት ወቅት የድርጅቱን የዕቃ ማስቀመጫ መጋዘን በተለያየ ጊዜ በተመሳሳይ ቁልፍ እየከፈቱ የተለያየ ሞደል ያላቸው ብዛታቸው 211 የሆኑ ኮር አይ3 ቶሸባ ላፕቶፖችን ጠቅላላ የዋጋ ግምታቸው 2,838,400 (ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰላሳ ስምንት ሺህ አራት መቶ) ብር የሚገመት ንብረት ከተወሰደው ውስጥ 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር) የተከፈለው ስለሆነ በፈጸመው ከባድ የስርቆት ወንጀል በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የልደታ የወንጀል ዘርፍና የፍታብሄር ፍትህ አስተዳደር የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡

በሁለተኛ ክስ ደግሞ በ2005 ዓ.ም የወጣውን በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 780/05 አንቀጽ 29/1/ሀ/ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ከላይ በተገለጸው ቦታና ጊዜ ለጊዜው ካልተያዙ ግብረ-አበሮቹ ጋር በመሆን የጥበቃ ሰራተኛ ሆኖ ሲሰራ በተለያየ ጊዜ በተመሳሳይ ቁልፍ የድርጅቱን የንብረት ማስቀመጫ ክፍል ከፍተው ከሰረቁት ንብረት ውስጥ ከደረሰው 60,000 ብር ውስጥ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ጨምሮበት ሰኔ በ19 ቀን 2007 ዓ.ም የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1-ደ/ህ 07963 የሆነ ትራይ ሳይክል ባጃጅ በ70,000 /በሰባ ሺህ/ ብር ከአቶ ታረቀኝ ናኡሻ በ23/10/2007 ዓ.ም ገዝቶ ውሉን ሲጽፍ በአርባ ሺህ ብር እንደተገዛ አድረጎ በገዥው ስም ሊብሬ እንዲያሰሩ፣ ሊብሬ
በሰነድ ፈርመው እንዲቀበሉ፣ ውል እንዲዋዋሉ ስሙን ወደ ስማቸው እንዲያዛውሩ የሚልና ስለንብረቱ አጠቃላይ ውክልና የወሰደ ስለሆነ
በፈጸመው በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል፡፡

የፌደራል ዐቃቤ ህግም በጉዳዩ ላይ ተከሳሽ ለመርማሪ ፖሊስ የሰጠውን 7 ገጽ የቃል ማስረጃ፣ የሽያጭ የውል ስምምነት ሰነዶችን እንዲሁም የሰው ማስረጃን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ችሎትም ህዳር በ18 ቀን 2011ዓ.ም በዋለው ችሎት በ14 ዓመት ጽኑ እስራትና እና በ10,000 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ሀዋሳ‼️

በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር በሞያሌና ቱርካና ተደጋግመው የሚከሰቱ ግጭቶች "የአካባቢው ምጣኔ ኃብት #እንዲቀጭጭና በቀጣናው ውጥረት እንዲሰፍን አድርጓል" ሲል የምሥራቅ አፍሪካ በየነ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት(ኢጋድ) አስታውቋል። በጉዳዩ ላይ እየተነጋገረ ያለው የኢትዮጵያና የኬንያ ድንበር ተሻጋሪ የዘላቂ ሰላም የምክክር መድረክ የሁለቱ አገሮች የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት ትላንት ሃዋሳ ከተማ ውስጥ ተከፍቷል፡፡

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ወጣቶች የመልካም ተግባር አርአያ መሆን እንጂ በስሜት በመነሳሳት #አንድነትን በሚሸረሽሩ ተግባራት ላይ መሰማራትየለባቸውም!››

የትግራይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ...

እኔ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ!

#የዚችን_ሀገር_ችግር_የምቀርፈው_በመማር_ነው!

#መብቴን_የማስከብረው_በማወቅ_ነው

#ከምማርበት_ጊዜ_ቀንሼ_ለወንድሜ_ድንጋይ_አላነሳም!

#ይልቅስ_ጊዜ_ተርፎንም_ከሆነ_በጎ_ፈቃደኞች_ነን!

ትዝታዎቼን ከጥላቻ ጋር ማስተሳሰር አልሻም።ሰዎችን በመደገፍ ግን የተሻለ አለም ለወገኖቼ መፍጠር እሻለሁ! ጓደኞቼም እንደዛው!

ቀኖቻችንን ፍቅር በመስጠት ውስጥ እያሳለፍን ነው! ብዙ ፍቅራችንን የሚፈልጉ ወገኖች አሉ!

በመገፋፋት በታሪካችን ላይ የምናሰፍረው አንዳች መልካም አሻራ የለም!

እኛ ጋር ብትመጡ የምናወራችሁ እና የምናሳያችሁ መልካም ነገር እንጂ የተሰበረ መስታወት ፥የተጠቃ ተማሪ ፥ አይደለም እኛ በጎ ፍቃደኞች ነን!

#ጣሊታ_ራይዝ_አፕ #ሀምሊን_የፌስቱላ_ማዕከል
#ሀዋሳ_ዩኒቨርስቲ #አዋዳ_ካሞፓስ
#ቅን_ዲል_ክበብ

©ሀና ሀይሉ(አዋዳ TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አ.ሳ.ቴ.ዩ🔝

"ዛሬ እሁድ ከቀኑ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ብቻ በየትምህርት ክፍላችሁ በመገኘት ያልተመዘገባዥሁ እንድትመዘገቡ እና ሰኞ ትምህርት እንድትጀምሩ..."

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድጋሚ...

ለድሬዳዋ ነዋሪዎች፦

"የተከበራችሁ የድሬዳዋ ነዋሪዎች ታህሳስ
7-2011 ዓም ክቡር ጠ/ሚ #አቢይ_አህመድ በተገኙበት ታቅዶ የነበረው የኢንዱስትሪ ፓርክ ምርቃት ላልተወሰነ ጊዜ #የተራዘመ መሆኑን እንገልፃለን!"

©የከተማው ከንቲባ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥቆማ መስጫ ስልክ መስመሮች፦

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት በከተማው የሚታዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታዎች፣ በህገወጥ መንገድ ታጥሮ የተቀመጡ መሬቶች ፣ ህገወጥ የቀበሌ ቤቶች እና የኮንደሚኒየሞች እንዲሁም በአገልግሎት መስጫ ተቋማት እና የመንግስት መስሪያ ቤት ኃላፊዎች ወይም ሰራተኞች በአጠቃላይ በከተማው ውስጥ የሚከናወኑ ማንኛውንም ህግን ያልተከተሉ ሥራዎች ላይ ህብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲያደርግ ይፈልጋል፡፡

ወ/ሪት ፌቨን ተሾመ(የከንቲባ ፅ/ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪ) በዚህ ሳምንት በሰጡት መግለጫ ህብረተሰቡ በከተማው የሚስተዋለውን ደካማ አሰራር እና በብልሹ አሰራር የተዘፈቁ አመራሮችን እና ባለሙያዎችን እንዲጠቁሙ እና ለውጡን በመደገፍ የድርሻቸውን እንዲወጡ ለከተማዋ ነዋሪ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በጥቆማው ላይ ሊካተቱ ከሚገባቸው መረጃዎች ውስጥ ፦

1፦የድርጊቱ አይነት፣
2፦የኃላፊው ሙሉ ስም
3፦የሰራተኛው ሙሉ ስም
4፦የአገልግሎት ዘርፍ

የጥቆማ መስጫ የስልክ መስመሮች

የካ (+251 118548252 )
ንፋስስልክ (+251 118548067 )
ልደታ (+251 118547907 )
ኮልፌ (+251 118547896 )
ጨርቆስ (+251 118548753)
አዲስከተማ (+251 118548423 )
አራዳ (+251 118548397 )
አቃቂ (+251 118548257 )
ቦሌ (+251 118548415 )
ጉለሌ (+251 118548638 )
በመጠቀም ጥቆማ በማድረስ ለውጡን እንዲደግፉ የከንቲባ ፅ/ቤት ጥሪውን አቅርቧል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
''ወንጀለኞቹ ማንም ይሁኑ ማን . . . አድነን ለሕግ ማቅረባችን አይቀሬ ነው'' ጠ/ሚ ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ በወቅታዊ የሰላም እንቅስቃሴ ዙሪያ ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ ወይይቱ በሶረቃ ከተማ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡ ሕዝባዊ ውይይቱ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ተስተውሎ የነበረው ግጭት ወደ አካባቢው እንዳይዛመት አስቀድሞ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቐለ🔝የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በመቐለ ከተማ መካሄድ ጀመረ። በጉባዔ መክፈቻ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበርና የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረፂሆን ገብረሚካኤል ተገኝተዋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወ/ሮ ፀዳለ ማሞ ከእስር ተፈቱ‼️

የመንግሥትን ሥራ በማያመች አኳኃን በመምራት በመንግሥት ላይ ከ11.9 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ፣ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ከአንድ ዓመት በፊት ተመሥርቶባቸው የነበሩት፣ የቀድሞ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ #ፀዳለ_ማሞን ጨምሮ የአራት ኃላፊዎች ክስ ተቋርጦ ከእስር ተፈቱ፡፡

ተከሳሾቹ ወ/ሮ ፀዳለ ማሞ፣ የጽሕፈት ቤቱ የሎጂስቲክስ አስተዳደርና ፋይናንስ መምርያ ኃላፊ የነበሩት አቶ የማነ ፀጋዬ፣ የመሬት ዝግጅት መሠረተ ልማትና ዲዛይን መምርያ ረዳት መምርያ ኃላፊ የነበሩት ወ/ሮ ሳባ መኮንንና የፕላንና ዶክመንቴሽን አገልግሎት ኃላፊ የነበሩት አቶ ሽመልስ ዓለማየሁ ናቸው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የጽሕፈት ቤቱ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል ሆነው ሲሠሩ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዕቃና አገልግሎት ግዥ መመርያ ቁጥር 4/1991 አንቀጽ 6(2) እና አንቀጽ 25 በመተላለፍ ከተፈቀዱ የግዥ ዘዴዎች ውጪ እንዲፈጸም ጨረታ ማውጣታቸወን ዓቃቤ ሕግ በፍርድ ቤት የመሠረተባቸው ክስ ያስረዳል፡፡ በመሆኑም የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ከየማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ጋር በመመሳጠር፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ያወጣውን ጨረታ እንዲያሸንፍና ግዥው እንዲፈጸም በማድረግ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውንም ክሱ ያብራራል፡፡ ለአፈር ቆርጦ መጣል፣ ለገረጋንቲ ማጓጓዣና ለገረጋንቲ መሙላት 33,384,526 ብር ግዥ መፈጸሙንም ጠቁሟል፡፡ ይኼ ዋጋ የተከፈለው ሌሎች ተጫራቾች ካቀረቡት ዋጋ በላይ እጅግ በተጋነነና ከ80 እስከ 120 በመቶ ጭማሪ በማድረግ መሆኑንም አክሏል፡፡

በአጠቃላይ ተከሳሾቹ የ11,979,848 ብር ጉዳት በመንግሥት ላይ አድርሰዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶባቸውና ዋስትና ተከልክለው ሲከራከሩ የከረሙ ቢሆንም፣ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ክሳቸውን ኅዳር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዳቋረጠላቸው ታውቋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ ክሱን ያቋረጠላቸው ተከሳሾቹ በመንግሥት ላይ ያደረሱትን 11,979,848 ብር በመክፈላቸው መሆኑን ገልጿል፡፡ ዓቃቤ ሕግ ክሱን ማቋረጡን ያስታወቀው በሌሉበት ክስ ተመሥርቶባቸው ጥፋተኛ በተባሉት አቶ የማነ አብርሃ፣ አቶ ወንድወሰን ደምረውና አቶ ሲሳይ በቀለን ጨምሮ ቢሆንም፣ የሦስቱን ተከሳሾች ክስ መቋረጥ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም፡፡ ዓቃቤ ሕግ ክስ የማቋረጥ ሥልጣን ቢኖረውም ከፍርድ በፊት መሆኑን ጠቁሞ፣ በሦስቱ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ በመሰጠቱ እንደማይችል በመጠቆም ቅጣት ጥሎባቸዋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዳቸው በስድስት ዓመታት ጽኑ እስራትና 20,000 ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ የፌዴራል ፖሊስም ፍርደኞቹን አፈላልጎ በመያዝ ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምቦ ዩኒቨርሲቲ...

በአምቦ ዩኒቨርስቲ የወሊሶ ካምፓስ የተማሪዎች ዉይይት መጨረሻ ለይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶር #ታደሰ_ቀነኣ የተጠቀሙት አስደናቂ
ስልት።

አሥር የኦሮሞ ተማሪዎች፣ አሥር የአማራ ተማሪዎች እንዲሁም አሥር ተማሪዎች ከሌሎች ብሔረሰቦች ወደፊት እንድወጡ ጠየቋቸው።

ተማሪዎቹም በተጠየቁት መልኩ ወጡ። ተቀላቅለው እንዲሰለፉ ተጠየቁ። እንደተጠየቁም አደረጉት። አንድ ጥያቄ ለተዳሚዎች አቀረቡ ከተሰለፉት ታማሪዎች ማን ኦሮሞ፣ ማን አማራ፣ ማን ትግሬ ፣ ማን ጉራጌ ወዘተ እንደሆነ ለይቶ የሚነግረን ብሎ ጠየቁ። ሁሉም ዝም ዝም አሉ። አንድ ናይጄሪያዊ ወይም ቻይና ብቀላቀል መለያት የቅተናል ወይ ብሎ ጠየቁ። ሁሉም በአንድ ድምፅ አያቅተንም ብሎ መለሱ። ስለዚህ ካለብን ልዩነቶች በጭንቅላታችን የሚንፈጥራቸዉ ልዩነቶች ስለሚበልጡ አንድነታችንን እናጉለ አሉ። ተማሪዎቹም ተቃቅፈው በአንድነት ወደ መመገቢያ ቦታ ሄዶ ምሳቸዉን በሉ።

Via~Mekonnen Bersisa
@tsegabwolde @tikvahethiopia