TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወላይታ ሶዶ⬆️

ከወላይታ ዩኒቨርሲቲ አንዳንድ ግለሰቦች በተማሪዎች ላይ በፈጠሩት የደህንነት ስጋት ገጥሞአቸው የወጡ የሲዳማ ብሔር ተማሪዎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተደረገው ውይይት #ችግሩ በመፈታቱ ዛሬ ከሲዳማ ዞን አስተዳደርና ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በተወከሉ አመራር አካላት በመመራት ወደ ወላይታ ሶዶ ያቀኑ ሲሆን ሲደርሱም የወላይታ ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የአመራር አካላት እና የዩኒቨርሲቲ ማህበረ ሰብ፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም ከተለያዬ ኀብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ በተገኙበት #ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ለተማሪዎቹ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል የሲዳማ ዞን አስተዳደር ታላቅ ምስጋና አቅርቧል።

ምንጭ:- የሲዳማ ዞን ባህል፣ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ

@tsegawolde @tikvahethiopia