TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦምሃጀር⬆️

የሰቲት #ሑመራ የልኡካን ብዱን ከ20 አመታት በኋላ ዛሬ ወደ #ኤርትራ ኦምሃጀር ከተማ አቅንተዋል።

የልኡካን ብዱኑ ኣባላት ከሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ወጣቶችና ሴቶች የተውጣጡ ሲሆን፥ ቁጥራቸው ከ50 በላይ መሆኑን ተገልጿል።

ነዋሪዎቹ የተከዜ ድልድይ በመሻገር በኦምሃጀር ከተማ ከሚገኘው ከኤርትራ ህዝብና ከሀገሪቱ የሰራዊት ሃይል ጋር ዛሬ ጠዋት ተገናኝተዋል።

📌ጉዞው ከኤርትራ ህዝብ ጋር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ተነገሯል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ⬇️

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በ73ኛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ለአካባቢው ሰላም እና ዘላቂ ልማት ተግታ የምትሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ እንደ ተመድ መስራች አባል ሀገር ለባለብዙ ወገን መድረክ ትኩረት በመስጠት የተ.መ.ድ መርህ እንዲከበር እንዲሁም ተግዳሮቶች እና ስጋቶች እንዲወገዱ በጋራ ትሰራለች ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተካሄደው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ለሀገሪቱ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ክስተት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እንዲሁም ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ተሰፋው እንዲፈነጥቅ ያደረገ መሆኑንም ዶ/ር ወርቅነህ አውስተዋል፡፡

የህግ የበላይነት እንዲከበር፣ ፍትህ እንዲሰፍን፣ የአገር ኢኮኖሚ በአግባቡ ለማስተዳደር እንዲቻል፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ የብዙሃኑ ተሳትፎ እንዲረጋገጥ እንዲሁም ዴሞክራሲ እንዲያብብ ለማድረግ መንግስት በስፋት እና በጥልቀት እየሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ
ተናግረዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመራው መንግስት በሁሉም አቅጣጫ የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት እና እንደ ሙስና፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ መልካም አስተዳደር ያሉትን የእድግት ማነቆዎች ለመቅረፍ በርካታ ተግባራት እየከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በቀጠናው የሰላም አየር እንዲነፍስ ያበረከተቸውን አስተዋጽኦም አብራርተዋል።

ለ20 አመታት ያክል በግጭት ላይ የነበሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ መክፈታቸው፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ እንዲሁም #ጅቡቲ እና #ኤርትራ ችግሮቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ የተደረገው ጥረት ከቀጠናው አልፎ ለአፍሪካ ሰላም ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ
መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ጁሴፔ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር #ጁሴፔ_ኮንቴ መኪና በመገጣጠም የሚታወቀውን የአምቼ ኩባንያን ጎብኝተዋል።

ኩባንያው 70 በመቶ በጣሊያን መንግስት 30 በመቶ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግስት ድርሻነት የተቋቋመ ነው፡፡

የጣሊያኑ ጠ/ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ #ኤርትራ አቅንተዋል፡፡

ጠ/ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየው በቦሌ አየር ማረፊያ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ፎቶ፦ ጠቅላይሚንስትር ፅ/ቤት
ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና #ኤርትራ!

#ለኤርትራ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከተቀመጡ 16 ሺሕ ተማሪዎች 40.8% ማለፋቸውን የአገሪቱ የማስታወቂያ ምኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር አስታውቀዋል። ፈተናውን ያለፉ የዲግሪ፣ ዲፕሎማና የሰርተፍኬት ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ ተብሏል።

Via Yemane G.Mekel,እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
4 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ነው!

አራት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ገለጸ። ኮርፖሬሽኑ በፓርኮች ግንባታና ምርት ዙሪያ ከምሁራን፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የሙያ ማህበራት ጋር ተወያይቷል። ውይይቱ በኢትዮጵያ በመስኩ እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ፣ እየተገኙ ያሉ ውጤቶችና ችግሮች ላይ ያተኮረ ነው።

የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ሺፈራው ሰለሞን እንደተናገሩት፤ አሁን ካሉት ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተጨማሪ አራት ፓርኮችን ለመገንት የሚያስችል ጥናት እየተከናወነ ነው። አሶሳ፣ አረርቲ፣ አይሻና ሰመራ ከተሞች ላይ ለመገንባት እንደታቀደ ጠቁመው፤ በተለይ #ሰመራ ላይ #የኢትዮጵያና #ኤርትራ ግንኙነት መሻሻልን ተከትሎ የወደብ አማራጭ በመኖሩ የተሻለ እንቅስቃሴ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።

አሶሳ ላይ ደግሞ የቀርከሃ ምርት በስፋት በመኖሩ ለቢሮ፣ ለቤት እቃዎችና መርከብ ግንባታ የሚሆን ግብዓት ለማምረት የሚያስችል የኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት እየተጠና መሆኑን ጠቁመዋል። በቀርከሃ ምርት ለመሰማራት ቻይናዊያን ባለሃብቶች ከፍ ያለ ፍላጎት ማሳየታቸውን ገልጸዋል። ”የጥናት ሂደቱ እንደተጠናቀቀ በውጤቱ መሰረት ወደ ግንባታ ይገባል” ብለዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TiffanyHaddish

የ41 ዓመቷ አሜሪካዊት ተዋናይትና ኮሜዲያን ቲፋኒ ሀዲሽ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ስላለው ግጭት በሰጠቻቸው አስተያየቶች/በምታጋራው መልዕክቶ ምክንያት ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበባት ነው።

የምታጋራው መልዕክቶች በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን አስቆጥቷል።

ቲፍኒ ሀዲሽ ፥ "በትግራይ ላይ የሚፈፀውን የንፁሃን ግድያ ፣ የሴቶች መደፈር፣ የህፃናት ሞት ክዳለች ፣ በትግራይ ጉዳይ ጦሯን ላሰማራቸው #ኤርትራ በተለይም አምባገነን ለሆነው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ድጋፍ ትሰጣለች" በሚል ነው ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገደች የምትገኘው።

ቲፍኒ ሀዲሽ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይ ስላለው ሁኔታ በትዊተር ገጿ የተለያዩ መልዕክቶችን እያስተላለፈች ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ የሚሰራጩ #ሀሰተኛ መረጃዎች የሚመለከት ነው።

በተጨማሪ፥ በአንድ ሪትዊት ላይ የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን "ጦርነቱ የህዝብ መሆኑን ህፃናትም የዚህ አካል ስለመሆናቸው" ተናግረውበታል የተባለውን የእሳቸውን ንግግር አጋርታለች።

ከተቃዋሚዎቹ በተቃራኒው ደግሞ የምታጋራቸውን መልዕክቶች ትክክል እንደሆኑ የሚገልፁ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ታይተዋል።

ቲፍኒ ሀዲሽ በ1979 እ.አ.አ. በሎስ አንጀለስ የተወለደች ሲሆን አባቷ ፀሃዬ ረዳ ሀድሽ በወቅቱ የኢትዮጵያ አካል የነበረችውን ኤርትራን ጥለው የተሰደዱ ስደተኛ ነበሩ።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ቲፋኒ ሀዲሽ ከኤርትራና ከመሪዋ ኢሳያስ አፍወርቂ ጋር ጥሩ የሚባል ወዳጅነትንና ቅርርብ ስለመፍጠራቸው ይነገራል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ኤርትራን የጎበኘችው እ.ኤ.አ. በ2018 ሲሆን በወቅቱ የአባቷን ህልፈት ተከትሎ በእሳቸውን የቀብር ስነስርዓት ላይ ለመገኘት ነበር።

@tikvahethiopia
የሶማሊያ ወታደሮች ጉዳይ ?

ወደ #ኤርትራ ለሥልጠና ተልከው የነበሩ በሺዎች ሚቆጠሩ የሶማልያ ወታደሮች በትግራይ ውስጥ በተደረገው ውጊያ ተካፋይ ሆነዋል በሚል፣ በዚህ ሳምንት በወጣው ሪፖርት የተነሳ በሶማልያ መንግሥት ላይ የሚደረገው ግፊት እያየለ መምጣቱ ተነግሯል፡፡

የልጆቻቸው አድራሻ የጠፋባቸው የወታደሮቹ ቤተሰቦች የሱማሊያ ፕሬዚዳንት የሆኑትን መሀመድ አብዱላሂ መሀመድን (ፈርማጆን) ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን እሳቸው ግን ሪፖርቱን አስተባብለዋል፡፡

ቪኦኤ እንደዘገበው የተወካዮቹ ምክር ቤት ኮሚቴ የወታደሮችን አድራሻ በሚመለከት ምርመራ እንዲደረግ ጥያቄ ማቅረባቸው ተነግሯል፡፡

በተባበሩት መንግስታት (UN) የሰአብአዊ መብት ጉባኤ በዚህ ሳምንት የወጣው ዘገባ እንዳመለከተው “ለሥልጠና ወደ ኤርትራ ተልከው የነበሩ ወታደሮች በኢትዮጵያው የትግራይ ውጊያ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡”

የሶማልያ መንግሥት ግን ወታደሮቹ ትግራይ ውስጥ የነበሩ መሆናቸውን አስተባብሏል፡፡

የሱማሊያ ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ኦስማን ዱቤ ትላንት ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ከሱማሊያ ወታደሮች ጋር የሚወጡት መረጃዎች ሀሰተኛ፣ መሰረተቢስ አሉባልታ፣ እና ፖለቲካዊ ፕሮፖጋንዳ ነው ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/SOMALIA-06-11

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ🇪🇹 #ኤርትራ🇪🇷

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ቡድን ከኤርትራ አቻቸው ጋር ዛሬ ከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን የሚያካሂስ ይሆናል።

ከጨዋታው አስቀድሞ ልዩ የመክፈቻ ስነ- ስርዓት እንደሚኖር የተገለፀ ሲሆን፤ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንደሚታደሙበት ይጠበቃል።

More : @tikvahethsport
#ኢትዮጵያ🇪🇹 #ኤርትራ🇪🇷

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከአዛም ቲቪ ጋር በመተባበር የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ውድድር የመክፈቻ ጨዋታ ከ8:30 ጀምሮ በአማራ ቴሌቪዥን በቀጥታ እንደሚተለላፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።

More : @tikvahethsport
#China

ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ እና ሱዳን ስለ ቻይና-ታይዋን ጉዳይ ምን አሉ ?

#ኢትዮጵያ

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰሞኑን የቻይና-ታይዋን ጉዳይ የተከሰተውን ውጥረት በትኩረት እየተከታተለች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ለኢዜአ ተናግረዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ስታራምድ የቆየችውን የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋሟን እንዳጸናች መሆኑን ተናግረዋል።

" የኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋም ዛሬ የተጀመረ አይደለም ያሉት " አምባሳደር መለስ፤ " ከቻይና ጋር በነበረን ግንኙነት ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስታት አፅንተው የያዙት አቋም ነው " ብለዋል።

አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያ ለ #አንድ_ቻይና ፖሊሲ ፅኑ አቋም አላት ያሉ ሲሆን ፖሊሲውን ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው የተመድና የአፍሪካ ህብረት የሚያራምዱት አቋም መሆኑን ገልፀዋል።

#ሱዳን

ሱዳን ለአንድ ቻይና መርህ ድጋፏን እንደምትሰጥ አሳውቃለች። ታይዋንም የቻይና ግዛት አካል መሆኗን ገልጻለች።

ሱዳን ፤ ቻይና ሉዓላዊነቷን እና የግዛት አንድነትዋን በመጠበቅ ረገድ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደምትደግፍም አስታውቃለች።

#ኤርትራ

ኤርትራ የአሜሪካ አፈጉባዔ ወደ ታይዋን ያደረጉት ጉዞ ከዓለም አቀፍ ህግና መርህ ያፈነገጠ ነው ብላለች።

የአፈጉባኤዋ ድርጊት የቻይና መንግስት ሉዓላዊነት ደንቦችን እና ድንጋጌዎች እንዲሁም " የአንድ-ቻይና " ፖሊሲ የሚጻረር እና የቻይናውያን ውህደት ሂደትን የሚያደናቅፍ ነው ስትል ገልፃለች።

ኤርትራ፤ አሜሪካ ቻይናን ለመቆጣጠርና ለመያዝ ጥረት እያደረገች ነው ብላ ድርጊቱ አጸያፊ ነው ብላለች።

#CGTN #ENA #AlAIN #Shabait

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ኤርትራ ያሉ የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር አባላት ዛሬ በፎቶ ታይተዋል። አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሃሙድ ላለፉት 2 ዓመታት በኤርትራ ስልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙትን የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር አባላትን ጎብኝተዋል። ፕሬዜዳንቱ ኤርትራ ያሉ የሶማሊያ ጦር አባላትን ከኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመሆን ነው የጎበኙት ተብሏል። የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ከትላንት ጀምሮ በኤርትራ የስራ…
#ሶማሊያ #ኤርትራ

የ5 ሺህ የሶማሊያ ወታደሮች ጉዳይ ከምን ደረሰ ?

የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ፤ የሶማሊያ ወታደሮች ከኤርትራ ያልተመለሱበት ምክንያት ፤ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገሪቱ ውስጥ (በሶማሊያ) ባለው የፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ሊመልሷቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መሆኑን ገልፀዋል።

ኤርትራ የሶማሊያን ኃይል በማሰልጠን ረገድ ጥሩ ሀሳብ እንዳላትም ፕሬዜዳንቱ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ፤ ኤርትራ 5000 የሶማሊያ ወታደሮችን ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን እያስታጠቀችም ነው ብለዋል።

የሶማሊያ መንግስት በኤርትራ የሰለጠኑ ወታደሮቹን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ለዚህም የአሜሪካን ድጋፍ መጠየቁን (ወታደሮቹን ለመመለስ) አሳውቀዋል።

ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በቅርቡ ወታደሮቹ እንደሚመለሱና ከአልሸባብ ጋር በሚደረገው ጦርነት የራሳቸውን አስተዋፆ እንደሚያበረክቱ " አረጋግጣለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

በነገራችን ላይ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት በአሁን ሰዓት አሜሪካ የሚገኙ ሲሆን ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ጨምሮ ከሌሎች የአሜሪካ ባለስልጣናት እና የዓለም አቀት ተቋማት ኃላፊዎች ጋር በሀገራቸው ጉዳይ መክረዋል።

ከአንቶኒ ብሊንከን ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ በሶማሊያ ሽብርተኝነትን መዋጋት፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈን እና ለድርቅ ምላሽ መስጠት ላይ መስማማታቸውን ገልፀዋል። አሜሪካ በሶማሊያ የዘላቂ ልማት እና እድገት ስትራቴጂክ አጋር መሆኗንም ገልጸዋል።

መረጃ ምንጭ፦ የቪኦኤ ሶማሊኛ ክፍል ጋዜጠኛ ሀሩን ማሩፍ ፣ ቪላ ሶማሊያ እና የፕሬዜዳንቱ (ሀሰን ሼክ ሞሀመድ) ትዊተር ገፅ።

@tikvahethiopia