TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ኤርትራ ያሉ የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር አባላት ዛሬ በፎቶ ታይተዋል። አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሃሙድ ላለፉት 2 ዓመታት በኤርትራ ስልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙትን የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር አባላትን ጎብኝተዋል። ፕሬዜዳንቱ ኤርትራ ያሉ የሶማሊያ ጦር አባላትን ከኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመሆን ነው የጎበኙት ተብሏል። የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ከትላንት ጀምሮ በኤርትራ የስራ…
#ሶማሊያ #ኤርትራ

የ5 ሺህ የሶማሊያ ወታደሮች ጉዳይ ከምን ደረሰ ?

የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ፤ የሶማሊያ ወታደሮች ከኤርትራ ያልተመለሱበት ምክንያት ፤ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገሪቱ ውስጥ (በሶማሊያ) ባለው የፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ሊመልሷቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መሆኑን ገልፀዋል።

ኤርትራ የሶማሊያን ኃይል በማሰልጠን ረገድ ጥሩ ሀሳብ እንዳላትም ፕሬዜዳንቱ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ፤ ኤርትራ 5000 የሶማሊያ ወታደሮችን ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን እያስታጠቀችም ነው ብለዋል።

የሶማሊያ መንግስት በኤርትራ የሰለጠኑ ወታደሮቹን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ለዚህም የአሜሪካን ድጋፍ መጠየቁን (ወታደሮቹን ለመመለስ) አሳውቀዋል።

ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በቅርቡ ወታደሮቹ እንደሚመለሱና ከአልሸባብ ጋር በሚደረገው ጦርነት የራሳቸውን አስተዋፆ እንደሚያበረክቱ " አረጋግጣለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

በነገራችን ላይ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት በአሁን ሰዓት አሜሪካ የሚገኙ ሲሆን ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ጨምሮ ከሌሎች የአሜሪካ ባለስልጣናት እና የዓለም አቀት ተቋማት ኃላፊዎች ጋር በሀገራቸው ጉዳይ መክረዋል።

ከአንቶኒ ብሊንከን ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ በሶማሊያ ሽብርተኝነትን መዋጋት፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈን እና ለድርቅ ምላሽ መስጠት ላይ መስማማታቸውን ገልፀዋል። አሜሪካ በሶማሊያ የዘላቂ ልማት እና እድገት ስትራቴጂክ አጋር መሆኗንም ገልጸዋል።

መረጃ ምንጭ፦ የቪኦኤ ሶማሊኛ ክፍል ጋዜጠኛ ሀሩን ማሩፍ ፣ ቪላ ሶማሊያ እና የፕሬዜዳንቱ (ሀሰን ሼክ ሞሀመድ) ትዊተር ገፅ።

@tikvahethiopia