TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል በሴኔጋል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የሚሰጠውን "Royal Order of the Lion" የተሰኘውን የክብር ሽልማት ለአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ቴድሮስ_አድሃኖም መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡

©etv
@tikvahethiopia @tsegabwolde
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ቴድሮስ_አድሃኖም ጋር በዓለም አቀፍ የጤና ሽፋንና በመሰረታዊ የጤና አገልግሎት ዙሪያ ተወያይተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ቴድሮስ_አድሃኖም ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። በቆይታቸውም የዓለም የጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ለማስፋፋት እየሰራቸው ባሉ ስራዎች እና በምን መልኩ መደገፍ ይቻላል በሚለው ጉዳይ ላይ መክረዋል።

©Office of the Prime Minister
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሪፖርት📌የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው አዲስ ሪፖርት በዓለማችን በአማካይ ከ20 ሰዎች ውስጥ አንዱ በአልኮል መጠጥ #እንደሚሞቱ ጠቁሟል።

በፈረንጆቹ 2016 ብቻ ከ3 ሚሊየን በላይ ሰዎች መሞታቸውም በሪፖርቱ ተካቷል።
ከዚህ ውስጥ ከ75 በመቶ የሚበልጡት ወንደች መሆናቸው ተገልጿል።

የአልኮል መጠጡ ለጉዳት በመዳረግ የሚሞቱት ሰዎች 28 በመቶ ሲሆኑ፣ ለምግብ መፈጨት ችግር በመጋለጥ የሚሞቱት 21 በመቶ ያህል ናቸው።

19 በመቶ ያህሉ ደግሞ የአልኮል መጠጡ በሚፈጥረው የልብ ችግር ህይወታቸውን እነደሚያጡ ሪፖርቱ ጠቁሟል።

ቀሪዎቹ ለካንሰር፣ ለቁስ ህመሞች፣ ለአዕምሮ ችግርና ሌሎች በአልኮል ምክንያት ለሚመጡ የጤና መታወክ በማጋለጥ ሰዎችን ለሞት መዳረጋቸውም ተነግሯል።

የአልኮል መጠጥን መጠቀም በዓለም ላይ ከሚገኙ በሽታዎች 5 በመቶ ያህሉ እንዲባባሱ ማድረጉም ነው የተገለጸው።

በዓለም ላይ 237 ሚሊየን ወንዶችና 46 ሴቶች በአልኮል መጠጥ ምክንያት ለአዕምሮ ችግር መዳረጋቸውንም ሪፖርቱ አሳይቷል፤ ለዚህ ጉዳት ከተዳረጉት መካከል አውሮፓውያን ቀዳሚ ሲሆኑ አሜሪካውያን ይከተላሉ።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር #ቴድሮስ_አድሃኖም ጤናማ ትውልድ ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ስጋት የደቀነውን የአልኮል መጠጥ አጠቃቀም መዛባት ለመከላከል በትጋት መስራት አለብን ብለዋል።

በዓለም ላይ 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ያህል ሰዎች አልኮል ይጠጣሉ። በርካታ ታዳጊዎችም 15 ዓመት ሳይሞላቸው አልኮል መጠጣት እንደሚጀምሩ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።

ምንጭ፦ሲኤንኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር #ቴድሮስ_አድሃኖም

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ሔፒታይተስን ለመከላከል፣ የምርመራ እና የሕክምና አገልግሎት ለማቅረብ በየአመቱ ተጨማሪ ስድስት ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተናገሩ። በኢትዮጵያ በተለምዶ የጉበት በሽታ ተብሎ የሚታወቀውን ሔፒታይተስ በጎርጎሮሳዊው 2030 ዓ.ም. ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ፖለቲካዊ አመራር እና ተግባራዊ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ዶክተር ቴድሮስ ጥሪ አቅርበዋል።

የዓለም #የሔፒታይተስ ቀን ዛሬ ሲከበር የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልዕክት ሔፒታይተስን ከአስራ አንድ አመታት ገደማ በኋላ ከመላው ዓለም ለማጥፋት በየአመቱ ተጨማሪ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ሲሉ ይገልፃሉ። «በመላው ዓለም 325 ሚሊዮን ሰዎች በተላላፊ ሔፒታይተስ ተጠቅተዋል። ከአስሩ መካከል ስምንቱ ለመከላከል፣ ለምርመራ እና ለሕክምና የሚያስችል አገልግሎት አያገኙም። ሁሉም ሰው የሚፈልገውን ክብካቤ እንዲያገኝ #የሔፒታይተስ የሕክምና አገልግሎትን በአፋጣኝ ማሳደግ ያስፈልጋል። ዛሬ የዓለም የጤና ድርጅት ሁሉም መንግሥታት እና አጋሮች ሔፒታይተስን በ2030 ለማስወገድ የሚያስችል ሥራ እንዲሰጡ ጥሪ ያቀርባል። ከዚያ ግብ ለመድረስ የመከላከያ፣ ምርመራ እና የሕክምና አገልግሎቶችን ለማሳደግ የዓለም የጤና ድርጅት በመላው ዓለም በየአመቱ ተጨማሪ ስድስት ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ይገምታል» የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚጠቁመው በመላው ዓለም 325 ሚሊዮን ሰዎች በሒፒታይተስ ተይዘዋል። በየአመቱ 1.4 ሚሊዮን ሰዎች ይሞታሉ። ከሳንባ ነቀርሳ ቀጥሎ ብዙ ሰዎችን የሚገድለው ይኸው ሔፒታይተስ ነው።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia