TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#nCoV

- የኮሮና ቫይረስ ምንድነው?

- በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ላይ የሚታዩ ምልክቶች ምንድናቸው?

- የ2019 (አዲሱ) ኖቬል ኮሮናቫይረስ ምልክቶች ምንድናቸው?

- የኮሮና ቫይረስ የሚተላለፍባቸው መንገዶች ምንድናቸው?

- የኮሮና ቫይረስን እንዴት መከላከል ይቻላል? ራስን ከኮሮና ቫይረስ እንዴት መጠበቅ ይቻላል?

- የኮሮና ቫይረስ ህክምናው ምንድነው?

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ለሁሉም ምላሹን ከላይ በሳምባ ሔልዝኬር ኮንሰልታንሲ በተዘጋጀው ምስል ማግኘት ትችላላችሁ። አንብባችሁ ስትጨርሱ ለሌሎች ሼር ማድረግን እንዳትዘነጉ።

[Mitiku Getu Moges - Tikvah Family]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
"የኢትዮጵያ መንግስት እኛን ለመፈለግ ያደረገው ጥረት የለም" - የቲክቫህ ቤተሰቦች በቻይና ጓንዡ የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መንግስት ወደሀገራቸው እንደሚመልሳቸው ጥሪ አቅርበዋል። ከባድ ሁኔታ ውስጥ ላይ ነው የምንገኘው የሚሉት ተማሪዎቹ መንግስት ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። አቅም ያላቸው ጓደኞቻችን ወደሀገር እየገቡ ናቸው እዚህ የቀረነው ተማሪዎች ግን ከፍተኛ…
#nCoV

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የኢትዮጵያ መንግስት ቻይና ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች አስፈላጊውን ሁሉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በማህበራዊ ሚዲያዎችና በሌሎችም ዋና ዋና በሚባሉ መገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ ያሉት ዘገባዎች ያለውን እውነታ የሚያሳዩ አይደሉም ብለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

#nCoV

Confirmed per Country/Region :

• 11,221 Mainland China
• 19 Thailand
• 17 Japan
• 16 Singapore
• 13 Hong Kong
• 11 South Korea
• 10 Taiwan
• 9 Australia
• 8 Malaysia
• 7 Germany
• 7 Macau
• 7 US
• 6 France
• 4 United Arab Emirates
• 3 Canada
• 2 Italy
• 2 Russia
• 2 UK
• 2 Vietnam
• 1 Cambodia
• 1 Finland
• 1 India
• 1 Nepal
• 1 Philippines
• 1 Spain
• 1 Sri Lanka
• 1 Sweden

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 305 ደርሷል። 14,559 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መጠቃታቸው ተሰምቷል። #nCoV

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#nCoV

የቬይትናም አየር መንገድ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደ ቻይና የሚደረጉ በረራዎችን በጊዜያዊነት ሊያቆም እንደሆነ ተሰምቷል። ወደ Beijing, Shanghai, Guangzhou, Shenzhen ከማክሰኞ ጀምሮ በረራዎች ይቋረጣሉ። ወደ Chengdu ከረቡዕ ጀምሮ እንዲሁም ወደ Macau ከሀሙስ ጀምሮ በረራዎች እንደሚቋረጡ ተሰምቷል።

[TNT]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#nCoV

አውስትራሊያ ከቻይና ተመላሽ ዜጎቿን ራቅ ወዳለች ደሴት ማጓጓዝ ጀመረች። ከቻይናዋ ዉሃን ግዛት የተነሱት የአውስትራሊያ ዜጎች የስደተኞች ማቆያ ቦታ ተደርጋ ወደምትታወቀው ክርሲማስ ደሴት እየተጓጓዙ ነው።

ደሴቷ ከአውስትራሊያ በ2700 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ደሴቷ ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞች ለማቆያ ስፍራነት አገልግሎት ስትሰጥ ነበር።

በአሁኑ ወቅት 4 የሴሪላንካ ዜግነት ያላቸው የቤተሰብ አባላት ብቻ ናቸው በደሴቷ ላይ እየኖሩ የሚገኙት። ከቻይና እየተጓጓዙ ያሉት አውስትራሊያውያን ለሁለት ሳምንት በደሴቷ ላይ ይቆያሉ። 89 ታዳጊዎችን ጨምሮ ዛሬ ጠዋት 243 ዜጎች እና የአውስትራሊያ ቋሚ ነዋሪዎች ወደ ደሴቷ ለመጓዝ አውሮፕላን መሳፈራቸውን የአውስትራሊያ መንግሥት አስታውቋል።

ከ600 በላይ የአውስትራሊያ ዜጎች ቫይረሱ በተከሰተበት ሁቤይ ግዛት ውስጥ ይኖራሉ። የተቀሩ ዜጎችን ለማጓጓዝ ተጨማሪ በረራዎች እንደሚዘጋጁ መንግሥት አስታውቋል። የህክምና መስጫ ስፋራዎች ቀደም ብለው በክሪስማስ ደሴት ላይ ተዘጋጅተዋል።

የአውስትራሊያ መንግሥት ስደተኞች ለማቆያ በሚጠቀምበት ደሴት ላይ ዜጎቹን ለይቶ ለማቆየት መወሰኑ ከበርካቶች ትችት ተሰንዝሮበታል። ከዚህ በተጨማሪ መንግሥት በደሴቱ ላይ ያዘጋጀው የህክምና መስጫ ስፍራዎች ደረጃ ዝቅ ያለ ነው የሚሉም በርካቶች ናቸው።

መንግሥት ግን 24 ዶክተሮችን እና ነርሶችን ማስማራቱን እና ከዚህ ቀደም እያንዳንዱ ከቻይና የሚጓጓዝ ዜጋ ወይም ቋሚ ነዋሪ እንዲከፍል ተጠይቆ የነበረው 1ሺህ የአውስትራሊያ ዶላር እንዲቀር ተወስኗል ብሏል። 24 ዶክተሮችን እና ነርሶችን ወደ ደሴቷ መሰማራታቸውን መንግሥት አስታውቋል።

[BBC]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#nCoV #coronavirus

Nagummaa Nyaataa Eeguu Amaleeffadhaa!

- Haaduu fi gabatee irratti kukkuttan kan foon dheedhii fi kan nyaata bilchaatanii adda baasuun ittti fayyadamaa.

- Foon dheedhii yoo tuqxan nyaata bilchaate otoo him tuqiin harka kessan dhiqadhaa.

#SHARE

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#nCoV #coronavirus

ዘውትር የሚመገቡትን ምግብ ደህንነት ይጠብቁ!

- ለጥሬ ስጋና ለሚበስሉ ምግቦች የሚጠቀሙበትን ቢላዋና መክተፊያ ይለዩ።

- በጥሬ እና በበሰለ ምግብ አዘገጃጀት መካከል እጅዎን መታጠብዎን አይዘንጉ።

መልዕክቱን ለሚያውቁት ሁሉ ያጋሩ!
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot