TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ አስመልክቶ ጥር 9/2016 ዓ.ም ያስተላለፈው ውሳኔ ለትግራይ ተፈታኞች አይመለከትም " - የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

የትምህርት ሚኒስቴር ከሰሞኑን ባስተላለፈው ውሳኔና ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች በላከው ደብዳቤ ዘንድሮ የሚሰጡ ፈተናዎችን ማሳወቁ ይታወሳል።

በዚህም ፦

- የተፈጥሮ ሣይንስ ተማሪዎች እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት እንደሚፈተኑ ገልጿል።

- የማኅበራዊ ሣይንስ ተማሪዎች ደግሞ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት እንደሚፈተኑ ገልጿል።

የፈተናው አወጣጥም ፤ ከኢኮኖሚክስ ትምህርት ውጪ ሁሉን የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ፈተናው ይዘጋጃል። 

የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ከ12ኛ ክፍል ብቻ ይዘጋጃል ማለቱ ይታወሳል።

ዛሬ ጥር 15/2016 የትግራይ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ ፤ " ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ  በቅርቡ ያሳተላለፈው ውሳኔ ለትግራይ ተፈታኞች አይመለከትም "ብለዋል።

ሃላፊው አያይዘው " መምህራንና ተማሪዎች ፈተናው በነባሩ ሰርዓተ ትምህርትና መፃሕፍት የሚዘጋጅ መሆኑን እንድታውቁ " ሲሉ ገልጸዋል።

በፈተናው የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችንም  ይፋ አድርገዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ፦
እንግሊዝኛ፣
ሒሳብ፣
ፊዚክስ፣
ኬሚስትሪ፣
ባዮሎጂ
ስነዜጋና ስነምግባር እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት፤

የማኅበራዊ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣
ሒሳብ፣
ታሪክ፣
ጂኦግራፊ፣
ስነዜጋና ስነ-ምግባር እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት መሆናቸውን አስረድተዋል።

" የፈተናው ጥያቄም ከነባሩ መፅሐፍ እንደሚዘጋጅ ለማሳወቅ እንወዳለን " ማለታቸው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።

#TikvahEthFamilyMekelle
                                     
@tikvahethiopia