TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SouthWollo : የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ከሰሞኑን በደቡብ ወሎ ዞን አንዳንድ አካባቢዎች በአዲስ በተቀሰቀሰው ጦርነት ብቻ ከ250 ሺህ በላይ ወገኖች መፈናቀላቸውን አመልክቷል።

የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መሳይ ማሩ ዛሬ ለጀርመን ድምፅ በሰጡት ቃል ፥ ካለፈው ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮ እንደአዲስ በተቀሰቀሰ ጦርነት በደቡብ ወሎ ዞን በርካቶች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው ብለዋል።

የተፈናቃይ ቁጥር ከቀን ወደቀን እየጨመረ ነው ያሉት አቶ መሳይ ፤ እየተፈናቀሉ ያሉት አረጋውያን፣ ሴቶች እና ህፃናት ፤ ከዛሬ ነገ ችግሩ ይፈታል ብለው ጫካ ለጫካ የቆዩ ወገኖች ናቸው ብለዋል።

ከዚህ በፊት በደሴ ከተማ 450 ሺህ ተፈናቃዮች የነበሩ ሲሆን አሁን ግን የተፈናቃዮች ቁጥር 700 ሺ መድረሱን አመልክተዋል።

ኃላፊው ፥ ተፈናቃዎችን ለማስተናገድ መጠለያ ከፍተኛ ችግር መሆኑን አንስተዋል፤ ከዚህ ቀደም 24 ትምህርት ቤቶች ተፈናቃዮችን ይዘው የነበረ ሲሆን አሁን ላይ 45 ት/ቤት ደርሷል።

ከት/ቤት በተጨማሪ የመንግስት ሼድ ፣ የግል ሼድ ፣ የተጀመሩ የመንግስት የቢሮ ግንባታዎች ጭምር ለተፈናቃይ መጠለያ እንዲሆን እየተደረጉ መሆኑንም አክለዋል።

በተለይ መርሳ፣ ድሬ ሩቃ ከሚባሉ አካባቢዎች አጠቃላይ ሊባል በሚችል ደረጃ ህዝቡ አካባቢውን ጥሎ መምጣቱን ገልፀው ፤ ከባቲ እስከ ሀርቡ የመንግስት ት/ቤቶች በተፈናቃዮች ተይዘዋል ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

Photo : File (Dessie Commu.)

@tikvahethiopia
#VisitAmhara

ግሸን ደብረ ከርቤ !

ግሸን ደብረ ከርቤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በአንጋፋነታቸው ከሚታወቁት ቅዱሳን ሥፍራዎች አንዷ ናት፡፡

የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ሌሎች የገዳሟን ታሪክ ማወቅ የሚፈልጉ ሰዎች በየጊዜው ወደ ግሸን ይጓዛሉ፡፡

በተለይ ከመስቀል በዓል እስከ መስከረም 21፣ ጥር 21 እንዲሁም መጋቢት 10 ወደ ግሸን የሚጓዘው ሕዝብ በመቶ ሽዎች ይቆጠራል፡፡

በረከት ለማግኘት፣ ታሪክ ለማወቅ እና ለመፈወስ ግሸን ለእምነቱ ተከታዮች ቀዳሚ መዳረሻ ናት፡፡

በኢትዮጵያ የሀይማኖት ቱሪዝም ታሪክ ብዙ እንግዶችን በማስተናገድ ግሸን ከቀዳሚዎች መካከል ትገኛለች፡፡

ነገ መስከረም 21 ታላቁ የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ክብረ በዓል ይከበራል፡፡

እንኳን አደረሳችሁ !

(Vist Amhara)

#TourismAndPeace  #GishenDebreKerbe #SouthWollo #ReligiousFestival #Ethiopia #LandOfOrigins

@tikvahethiopia