TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SFP

የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዚያዊ የምዝገባ ፈቃድ ማግኘቱን አመልክቷል።

አስተባባሪ ኮሚቴው በላከው መግለጫ ክልሉ በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ ፣በባህላዊና በፍትህ ዘርፎች ትክክለኛ መስመር አለመያዙን ተገንዝቢያለሁኝ ያለ ሲሆን በተለይ ምክንያታዊ ያልሆኑ የስራ አጥነት ቀውስ፣ ፍትህ እጦት፣ ሙስና፣ ጎሰኝነት፣ አድሎአዊ አሰራር፣ ጥሎ የማለፍ ፖለቲካ ስርዓታዊ (systemic) እየሆነ መጥቷል ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በክልሉ ውስጥ ህዝቡን አደራጅቶ የሚታገል ጠንካራ ተፎካካሪ ፖርቲ እንደሌለ መገንዘቡን ገልጾ ፦
- ሁሉን የህብረተሰብ ክፍል ያቀፈ ፣
- የሲዳማ እሴቶችን መርህ ያደረገ፣
- በዴሞክራሲያዊና የህዝብ ስልጣን ባለቤትነትን ተግባራዊ እንዲሆን የሚታገል፣
- በሀሳብ ብዙሃነትና በመነጋገር የሚያምን፣
- እውነተኛ የሆነ ህብረብሔራዊ ፌደራሊዝም የሚከተልና እውን ለማድረግ ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ሀገራዊ ፖርቲዎች ጋር የሚሰራ ክልላዊ የፖለቲካ ፖርቲ ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ጊዜያዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጊዜያዊ ፈቃድ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አግኝቶ የማቋቋሙን ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በአሁኑ ጊዜ ኮሚቴው ሙሉ ፈቃድ ለማግኘት የሚያስፈልጉ ስራዎች እያጠናቀቀ እንደግሚገኝና የአባላት ምዝገባ እያካሄደ መሆኑን አመልክቷል።

በዚህ ሂደት ሚመዘግቡ ወጣቶችና አስተባባሪዎች ላይ የማስፈራሪያ ዘመቻ እየተካሄደ ነው ያለው ሲፌፓ ለድርጊቱን የክልሉን መንግስት አመራሮችን ወቅሷል፤ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም አሳስቧል።

@tikvahethiopia