TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#PressRelease

በአማራ ክልል ከ 2014 የጥምቀት በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ በእስልምና ተቋማት ላይ የተፈፀሙ ሃይማኖታዊ ትንኮሳዎችን በተመለከተ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት መግለጫ አውጥቷል።

በ2014 በተከበረው የጥምቀት በዓል በበርካታ ቦታዎች ህዝብን ለግጭት የሀገርንም ሰላም የሚያናጋ ትንኮሳ ተካሂዷል ብሏል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው ላይ ፦

- ጥር 10 ከቀኑ 8 ሰዓት በባህር ዳር ከተማ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ግንብ አጥር በከፊል መፍረሱን ፣ በተጨማሪ በወቅቱ በነበሩት የምክር ቤቱ ሰራተኞችና የመላውን ሙስሊም ህብረተሰብ ክብረነክ ስድብ በመስደብ ግጭት ለማስነሳት ሙከራ መደረጉን ፣

- በመሸንቲ ከተማ የሙስሊሞች የበዓል ማክበሪያ ቦታ ላይ መስቀል መትከል

- በተመሳሳይ ቀን በባህር ዳር ከተማ አባይ ማዶ በሚኖሩት ትልቅ የሙስሊም አባት ሼኽ አደም ሼኹ የመኖሪያ ቤት በድንጋይ መደብደብ

- በተመሳሳይ ቀን በጎንደር ቀበሌ 18 በሚገኘው ነስረላህ መስጂድ አጥሩ እና ጣሪያው በጥይት መመታት፣

- በተመሳሳይ ጥር 10 በሰ/ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ ከበርካታ እንግልት በኃላ የተፈቀደውን መሥጂድ ቦታ ድንኳንና መስቀል ካላስቀመጥን በማለት ከፀጥታ አካላት ጋር ግጭት መፍጠር ፣

- ጥር 11 ከቀኑ 10 ሰዓት በደሴ ከተማ በሚገኘው አረብ ገንዳ መስጂድ ሙስሊሞች በሶላት ላይ ባሉበት ሰዓት መስጂድ በጥይት መደብደብ ፣

- በተመሳሳይ ቀን በቡሬ ከተማ በሙስሊሞች የመካነ መቃብር ላይ መስቀል መትከል፣ በደ/ሜጫ ወረዳ መራዊ ከተማ የመቃብር ቦታ ላይ መስቀል መትከል ትንኮሳዎች ተፈፅመዋል ብሏል።

ምክር ቤቱ የሁላችንም ወኪል ነው ብለን እምነት የጣልንበት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሰሞኑ ከጥምቀት በዓል ጋር በተያያዘ ስለተፈጠረው ችግር አዲስ አበባ ላይ በመታጠር የሰጠው መግለጫ ጉባኤውን የአንድ ወገን ብቻ ጉዳይ አስፈፃሚ ሆኖ እንደተመለከተው ገልጿል።

የምክር ቤቱ ስራ አስፈፃሚ በቀን 16/5 /2014 ባካሄደው ስብሰባው በተፈፀመው ሃይማኖታዊ ትንኮሳ ዙሪያ የተለያዩ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን አሳውቋል።

ይኸውም ፦

- የተፈፀሙት ድርጊቶች በእምነቱ እና አማኞች ሰብዓዊ መብት ላይ ያነጣጠሩ ፣ በሰላም የሚኖረውን ህዝብም ለግጭት የሚዳርግ በመሆኑ በጥብቅ አውግዞ አጥፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ጠይቋል።

- በባህር ዳር ከተማ የክልሉ ምክር ቤት ግንብ አጥር ሲፈርስ በእለቱ የነበሩ ለአካባቢው ጥበቃ ስምሪት የተሰጣቸው የፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት በዝምታ የተመለከቱ በመሆናቸው በስምሪታቸው መርሃግብር መሰረት እንዲጠየቁ።

- የአማራ ክልል መንግስት እና በየደረጃው ያለው አስተዳደር በእስልምና ተቋማት እና አማኞች ላይ በተደጋጋሚ የሚፈፀሙትን ሃይማኖታዊ ትንኮሳዎች አደጋውን አርቆ በማሰብ ህግ የማስከበር እና ወንጀለኞችን በህግ አግባብ እንዲታረሙ በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ሲል ጠይቋል።

@tikvahethiopia
#PressRelease

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ጠቅላይ ምክር ቤት መጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ.ም. 48ተኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

በዚህ ስብሰባ ማጠናቀቂያ ም/ቤቱ ባለአስር ነጥብ የአቋም መግለጫ ያወጣ ሲሆን ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia