TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GAMBELA

ከጋምቤላ ከተማ 38 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር ዛሬ በቁጥጥር ሥር ዋሉ። የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አቶው አኮት እንደገለጹት መሣሪያዎቹ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በክልሉ ጸጥታ ኃይል፣ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ሠራዊት ለሦስት ቀናት ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት ነው።

የጦር መሣሪያዎቹና ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት  ከአንድ ግለሰብ ቤት ኮድ 3 ሠሌዳ ቁጥር ቁጥር አዲስ አበባ 55966 በሆነ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር ነው። በክልሉ እየተስፋፋ ያለውን ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች ዝውውር ለመግታት የክልሉና የፌዴራል ጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው በመሥራት ላይ  መሆናቸውን ገልጸዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ኡቲያንግ ኡቻን እንተናገሩት ክልሉ ድንበር ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች ዝውውር መበራከቱን ተናግረዋል። ችግርን ለመካለካል በሚደረገው ጥረት ሕዝቡና  ጸጥታ አካላት ለሚያደርጉት ጥረት አመስግነው፣ በቀጣይም ቁጥጥሩ ይጠናከራል ብለዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GAMBELA | በትላንትናው ዕለት በባሮ ኮላ ኬላ ከቀኑ 9:00 አካባቢ ከሁለት ሃይሩፍ እየተባሉ ከሚጠሩ መኪኖች 3 ኪሎ እና 10 ኪሎ ካናቢስ አደንዛዥ ዕዥ በቁጥጥር ስር ውሏል። አደንዛዥ ዕፁ ከአዲስ አበባ ወደ ጋምቤላ ሲጓዝ ነው በፌደራል ፖሊስ እና በጉሙሩክ ሰራተኞች አማካኝነት በቁጥጥር ስር የዋለው።

Via HAMI/TIKVAH ETH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GAMBELA

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶከተር አብይ አህመድ ለኖቬል የሰላም ሽልማት በመብቃታቸው እና የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ኩራትና ድል በመሆኑ በጋምቤላ ከተማ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የከተማው ኑዋሪዎች ደስታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገልፀዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GAMBELA

በጋምቤላ ያለ ሰሌዳ ቁጥር ሲንቀሳቀሱና መንጃ ፈቃድ በሌላቸው ግለሰቦች ሲነዱ የነበሩ 101 ሞተር ሳይክሎች መያዙን የከተማዋ ፖሊስ ገለፀ።

በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ ቁጥጥር ስታቲስቲክስ ኦፊሰር ምክትል ኢንስፔክተር ታደለ አየለ ንደገለፁት ሞተር ሳይክሎቹ የተያዙት አንዳንዶቹ ያለ መንጃ ፈቃድ ሲያሽከረክሩ ቀሪዎቹ ደግሞ የሰሌዳ ቁጥር ስለሌላቸው ነው ብለዋል።

በተደረገው ድንገተኛ ቁጥጥር  101 ሞተር ሳይክሎች የተያዙ ሲሆን ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል። ከተያዙት ሞተር ሳይክሎች መካከል 27ቱ የሰሌዳ  ቁጥር የሌላቸው ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ የመንጃ ፈቃድ በሌላቸው ግለሰቦች ሲሽከረከሩ የነበሩ ናቸው።

በተለይም በከተማዋ የሰሌዳ ቁጥር የሌላቸው ሞተር ሳይክሎች አደጋ አድርሰው የሚጠፉበት ሁኔታ መኖሩን ምክትል ኢንስፔክተሩ ጠቁመው ችግሩን ለመፍታት የትራፊክ ፖሊስ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GAMBELA

በጋምቤላ ክልል በኑዌር ብሄረሰብ ዞን በቀበሌ ሊቀመንበር መገደል ምክንያት የተቀሰቀሰ ግጭት ለ12 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ተነገረ።

ቀስ በቀስ ወደ ጎሳ ግጭት የቀየረው በዚህ ሁከት 21 ሰዎች ሲቆስሉ፣ 400 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከ300 በላይ የቤት እንስሳቶችም ተዘርፈዋል። በተጨማሪ የግጭቱ ሰለባ የሆኑ የ5 ቀበሌ ነዋሪዎች [7 ሺህ ሰዎች] ተፈናቅለዋል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GAMBELA

በጋምቤላ ክልል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመቆጣጠርና ሊያደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ ለ81 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል።

ይቅርታ የተደረገላቸው በቀላል ወንጀል እስከ ሶስት ዓመት ተፈርዶባቸው ያሉና በማረሚያ ቤት ቆይታቸው በአመክሮ እስከ አንድ ዓመት የቀራቸው መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአስሩ ክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ወቅታዊ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ስርጭት ቁጥራዊ መረጃ ፦

#Afar

በቫይረሱ የተያዙ - 1,408
ያገገሙ - 231

#Amhara

በቫይረሱ የተያዙ - 3,388
ህይወታቸው ያለፈ - 34
ያገገሙ - 2,224

#BenishangulGumuz

በቫይረሱ የተያዙ - 1138
ያገገሙ - 382

#Harari

በቫይረሱ የተያዙ - 1,505
ህይወታቸው ያለፈ - 27
ያገገሙ - 693

#Oromia

በቫይረሱ የተያዙ - 9,415
ህይወታቸው ያለፈ - 63
ያገገሙ - 4,415

#SNNPRS

በቫይረሱ የተያዙ - 2,211
ህይወታቸው ያለፈ - 16
ያገገሙ - 1,656

#AddisAbaba

በቫይረሱ የተያዙ - 36,939
ህይወታቸው ያለፈ ድምር - አልተገለፀም
ያገገሙ ሰዎች ድምር - አልተገለፀም

#Tigray

በቫይረሱ የተያዙ - 5,403
ህይወታቸው ያለፈ - 27
ያገገሙ - 4,275

#Somali

በቫይረሱ የተያዙ - 1,375
ህይወታቸው ያለፈ - 26
ያገገሙ - 1,076

#Sidama

በቫይረሱ የተያዙ - 1,897
ህይወታቸው ያለፈ - 22
ያገገሙ - 1,449

#DireDawa

በቫይረሱ የተያዙ - 1,246
ህይወታቸው ያለፈ - 21
ያገገሙ - 1,041

#Gambela

በቫይረሱ የተያዙ - 954
ያገገሙ - 506
ህይወታቸው ያለፈ - አራት በኮሮና ተቋም፣ አምስት ከአስክሬን፣ አስራ አንድ ላብራቶሪ ውጤት በመጠበቅ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የአስሩ ክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ወቅታዊ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ስርጭት ቁጥራዊ መረጃ ፦

#Afar

በቫይረሱ የተያዙ - 1,447
ያገገሙ - 231

#Amhara

በቫይረሱ የተያዙ - 3,427
ህይወታቸው ያለፈ - 35
ያገገሙ - 2,273

#BenishangulGumuz

በቫይረሱ የተያዙ - 1138
ያገገሙ - 382

#Harari

በቫይረሱ የተያዙ - 1,514
ህይወታቸው ያለፈ - 27
ያገገሙ - 748

#Oromia

በቫይረሱ የተያዙ - 9,602
ህይወታቸው ያለፈ - 67
ያገገሙ - 4,801

#SNNPRS

በቫይረሱ የተያዙ - 2,242
ህይወታቸው ያለፈ - 16
ያገገሙ - 1,717

#AddisAbaba

በቫይረሱ የተያዙ - 37,278
ህይወታቸው ያለፈ ድምር - አልተገለፀም
ያገገሙ ሰዎች ድምር - አልተገለፀም

#Tigray

በቫይረሱ የተያዙ - 5,433
ህይወታቸው ያለፈ - 27
ያገገሙ - 4,333

#Somali

በቫይረሱ የተያዙ - 1,376
ህይወታቸው ያለፈ - 26
ያገገሙ - 1,084

#Sidama

በቫይረሱ የተያዙ - 1,926
ህይወታቸው ያለፈ - 22
ያገገሙ - 1,576

#DireDawa

በቫይረሱ የተያዙ - 1,260
ህይወታቸው ያለፈ - 21
ያገገሙ - 1,086

#Gambela

በቫይረሱ የተያዙ - 954
ያገገሙ - 506
ህይወታቸው ያለፈ - አራት በኮሮና ተቋም፣ አምስት ከአስክሬን፣ አስራ አንድ ላብራቶሪ ውጤት በመጠበቅ

መስከረም 9/2013 ዓ/ም
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia