TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል #የድንበር ይገባኛል ጉዳይን ጨምሮ የጋራ ድንበር ፀጥታና ንግድን የሚመለከቱ ጉዳዮችን የሚመለከት ስብሰባ በመጪዎቹ ቀናት ይካሄዳል። በጎንደር በሚደረገው በዚህ ስብሰባ የሱዳን ተዋሳኝ ግዛቶች ተወካዮች ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር ይመካከራሉ። የድንበር አካባቢው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበረሰብ ደረጃ በሚፈጠሩ የመሬት ይገባኛል ግጭቶች ሲታወክ ቆይቷል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #KENYA ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገር ኬንያ ጋር በሰላምና የደህንነት ጉዳዮች ለመተባበር ተስማምታለች። ዛሬ የኢፌዲሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኬንያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሮበርት ኪቢቹ ኬንያ፣ ናይሮቢ ውስጥ ተወያይተዋል። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከኬንያ አቻቸው ጄኔራል ሮበርት ኪቢቹ ጋር ባደረጉት ምክክር ሁለቱ አገሮች…
#Ethiopia #SouthSudan

በጄኔራል አበባው ታደሰ የተመራ ልዑክ ቡድን በደቡብ ሱዳን የሥራ ጉብኝት እያካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው የሚመሩት ልዑክ በደቡብ ሱዳን ጁባ የስራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

በዚህ የስራ ጉብኝት ጀነራል አበባው ታደሰ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ሉ/ጄኔራል ቶይ ቻኒይ ሬይት ጋር ውይይት አድርገዋል።

በሎጂስቲክስ እና በአቅም ግንባታ ጉዳዮች ለደቡብ ሱዳን ድጋፍ ለማድረግና ተሞክሮ ለማጋራት እንዲሁም የሁለቱ አገራት #የድንበር_አካባቢ ፀጥታና ደህንነትን ለማረጋገጥ በትብብር ለመሥራት ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል።

ትላንትና የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፤ በናይሮቢ ከኬንያ አቻቸው ከጄኔራል ሮበርት ኪቢቹ ጋር ውይይት ካደረጉ በኃላ ሁለቱ ሀገራት በሰላም እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ ለመተባበር ስምምነት ማድረጋቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#አውሮፓ

የአውሮፓ ፓርላማ የህብረቱን #የስደተኞች እና #የጥገኝነት ደንቦችን የሚያጠናክር ትልቅ ማሻሻያ አጽድቋል።

የአውሮፓ ህብረት የጥገኝነትና ፍልሰት ስምምነት ከ2015 ጀምሮ ሲመከርበት የቆየ ሲሆን በ2 ዓመት ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

አዲሱ ሕግ ምን ይዟል ?

➡️ የጥገኝነት ሂደት ጥያቄ #ያፋጥናል ፤ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ #ያስገድዳል

➡️ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት የጥገኝነት ጠያቂዎችን ኃላፊነት እንዲጋሩ ያደርጋል።

➡️ የአውሮፓ ህብረት 27 አባል አገራት በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ከጣሊያን፣ ግሪክ እና ስፔን ካሉ " #የድንበር " አገራት እንዲወስዱ ወይም በምትኩ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያቀርቡ ያደርጋል።

➡️ ዝቅተኛ ተቀባይነት የማግኘት እድል ያላቸው የጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ አውሮፓ ህብረት ግዛት ሳያስገቡ ጉዳያቸው በፍጥነት መታየት አለበት ይላል።

➡️ የጥገኝነት ጥያቄዎች ቢበዛ በ12 ሳምንታት ውስጥ እንዲያልቁ ይላል።

➡️ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው በ12 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ #በግዳጅ ወደ አገራቸው መመለስ አለባቸው  ይላል።

➡️ ስደተኞች ከመግባታቸው በፊት ባሉ በ7 ቀናት ውስጥ ጠንከር ያለ የማጣራት ሂደት ይደረግላቸዋል። የጤና እና የደህንነት ፍተሻዎችን ይጨምራል።

➡️ ከ6 ዓመት እና ከዛ በላይ ለሆኑ ማናቸውም ስደተኞች የባዮሜትሪክ መረጃ ይሰበሰባል። ስደተኞች ቁጥር በአጋጣሚ ካሻቀበም ምላሽ የሚሰጥበት አሠራር ተዘርግቷል።

ምንም እንኳን አንዳንድ የአውሮፓ ህብረት አገራት የተወሰኑ የስምምነቱን ክፍሎችን ቢቃወሙም በሚያዝያ ወር መጨረሻ በሚደረግ ድምጽ አሰጣጥ የአብዛኛውን ይሁኝታ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፈው አመት 380 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የአውሮፓ ህብረትን ድንበር በህገ ወጥ መንገድ አቋርጠዋል። ይህም እ.አ.አ ከ 2016 ወዲህ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

ስለ ሕጉ ምን ተባለ ?

#ጀርመን፦ የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ “ ታሪካዊና አስፈላጊ እርምጃ ” ብለውታል።

#የአውሮፓ_ፓርላማ፦ የፓርላማው ፕሬዝዳንት ሮቤታ ሜሶላ “ በአብሮነት እና በኃላፊነት መካከል ያለውን ሚዛን ጠብቋል ሁሉንም ነገር በአንድ ጀምበር ባይፈታም ግን 10 ግዙፍ እርምጃ የተጓዘ ነው " ብለዋል።

#ሀንጋሪ ፦ ምንም አይነት የስደት ስምምነት ቢደረስ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞችን አልወስድም ብላለች።

#ፖላንድ ፦ የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ቱስክ የተወሰኑ ጥገኝነት ጠያቂዎችን መውሰድ አልያም ለድንበር አገራት ገንዘብ መክፈል የሚለውን ሃሳብ " ተቀባይነት የሌለው " ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።

#ስሎቫንያ፦ “ ልንሰራበት የምንችለው ስምምነት ነው ” ስትል ደግፋለች።

#ቤልጂየም፦ “ ፍፁም አይደለም (ሕጉን) ግን እንደግፈዋልን ” ስትል አሳውቃለች።

#ፈረንሳይ ፦ ፕ/ት ኢማኑኤል ማክሮን ድጋፍ ሰጥተዋል። የፈረንሣዩ ቀኝ አክራሪ ናሽናል ራሊ አባል ጆርዳን ባርዴላ ስምምነቱ “ #አስፈሪ ” ነው ሲሉ ተቃውመዋል።

#አምነስቲ_ኢንተርናሽናል ፦ ስምምነቱ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ “ከፍተኛ ስቃይ” የሚመራ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

ከመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚነሳው አንዱ ተቃውሞ ዝቅተኛ ተቀባይነት የሚኖራቸው #ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳያቸው በድንበር #መግቢያዎች ላይ ወይም #በማቆያ_ስፍራዎች እንዲስተናገዱ በማድረግ ፍትሃዊ ዕድል የማግኘት ተስፋቸውን ያመነምነዋል የሚል ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ምንጭ ቢቢሲ መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia