TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ‼️

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በፀጥታ ችግር #የባከነውን የትምህርት ጊዜ #ለማካካስ የእረፍት ቀናት ጨምሮ እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡

በጸጥታ ችግር ምክንያት የባከነ የትምህርት ጊዜን በማካካስ የመጀመሪያውን መንፈቅ ዓመት በስኬት ለማጠናቀቅ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆናቸውን የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን ለኢዜአ ገልጸዋል።

አሁን አንጻራዊ #ሰላም በመስፈኑ ተቋሙ ያመቻቸላቸውን የትምህርት ማራዘሚያ ጊዜ በመጠቀም የባከነውን ጊዜ ለማካካስ ከመምህራን ጋር እየሰሩ እንደሚገኙ ተማሪዎች ገልጸዋል።

የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዘላለም አብዲሳ በበኩላቸው በምዕራቡ ክፍል ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር ለተወሰነ ጊዜ የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ የሁለት ሳምንት ማራዘሚያ ተደርጓል።
በእረፍት ቀናትም ጭምር የማካካሻ ትምህርቱ እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይ ለሴት ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት መዘጋጀቱን የገለፁት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራን ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በ1999 ዓ.ም 851 ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር የጀመረው የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት በመደበኛና ተከታታይ የትምህርት መርሀ ግብር በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ 38 ሺህ ተማሪዎች በማስተማር ላይ መሆኑ ታውቋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia