TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአዲስ አበባ ሰኔ 16 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ላስመዘገቧቸው ለውጦች በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመስቀል አደባባይ በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል ተብለው በሚል ምርምራ እየተካሄደባቸው የነበረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ #ዋስትና ተፈቀደላቸው።

አቃቤ ህግ ምክትል ኮሚሽነሩን ጨምሮ ሌሎች 11 የፖሊስ አመራሮችም በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም ትናንት ማስታወቁ ይታወሳል።

የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎትም ዛሬ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፈቅዷል።

ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም፣ ኮማንደር ገብረስላሴ ታፈረ፣ ኮማንደር ግርማይ በርሄና ኮማንደር አንተነህ ዘላለምን ጨምሮ ሌሎች የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል ተብለው የነበሩ ግለሰቦች ከ6 ሺህ ብር እስከ 9 ሺህ ብር በሚደርስ ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ፈቅዷል።

በዚህም የዋስትና ጉዳይን የሚመለከተው መዝገብ መዘጋቱን ነው ፍርድ ቤቱ ያስታወቀው።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ‼️

አሶሳ ዩኒቨርሲቲን ወደ ቀድሞ ሰላሙ #ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ካለፈው እሑድ ጀምሮ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሰላማዊ መማር ማስተማሩ ተስተጓጉሏል፡፡ ተማሪዎች እና ተወካይ ፕሬዝዳንቱ እንደነገሩን የግጭቱ መነሻ የሁለት ተማሪዎች አለመግባባት ነው፡፡ ይህም እየተስፋፋ ሄዶ ወደ ቡድን ፀብ ተቀይሮ ነበር፡፡

ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ዶክተር #ሃይማኖት_ዲሳሳ ችግሩን ለመፍታት ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ከተማሪዎች ጋር ምክክር ተደርጎ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በውይይቱም መግባባት ላይ መደረሱ ተማሪዎች አረጋግጠዋል፡፡

ይሁን እንጂ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት ትናንት ጠዋት ላይ ተማሪዎች ወደ መመገቢያ አዳራሽ ሲገቡ እንደገና #ረብሻ ተጀምሮ ነበር፡፡

እንደ ተማሪዎቹ መረጃ የግጭቱ ዋነኛ ምክንያት የተማሪዎች መማክርት በወቅቱ አለመመረጥ ኢ-ፍትሐዊ አሠራር ፈጥሯል የሚል ነው፡፡

ተማሪዎቹ ምርጫው ‹‹ባለፈው ዓመት ሰኔ ላይ መካሄድ ነበረበት፤ በወቅታዊ ጉዳዮች ምክንያት አልተካሄደም፤ እስካሁን ግን መቆየት አልነበረበትም›› የሚል አቋም አላቸው፡፡

አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ችግሮችን ተወካዮቻቸው በወቅቱ አለመፍታታቸውም ለችግሩ መከሰት ምክንያት መሆኑን ነው ተማሪዎቹ የተናገሩት፡፡

ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ግን ‹‹በውይይቱ ለከፋ ግጭት የሚዳርግ ችግር አላገኘንም›› ነው ያሉት፡፡

በረብሻው ምክንያት ‹‹34 ተማሪዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸውም ይገኛል ብለዋል
ዶክተር ሃይማኖት፡፡

በተከሰተው ግጭት የሶስት ተማሪዎች ህይወት አልፏል፡፡ የጸጥታ ኃይሎች ግቢውን ወደ ቀድሞ ሰላሙ ለመመለስ እየሠሩ መሆናቸውን ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎችም ይህን መመልከታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ይሁን እንጂ ተረጋግተው ለመኖር እና ለመንቀሳቀስም ስጋት ውስጥ መሆናቸውንና ለሰላማቸው #ዋስትና እንደሚፈልጉ ነው የተናገሩት፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢንሳ የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ ዋስትና ታገደ!

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ሐምሌ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በ30,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ለይግባኝ ሰሚው ችሎት ይግባኝ አቅርቦ እንዲታገድ አድርጓል፡፡

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው #በእስር ላይ የሚገኙት ቀድሞ የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዳይሬክተር ሌተና ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ፣ በተመሠረተባቸው ክስ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶባቸው ነበር፡፡ የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007፣ አዋጅ ቁጥር 780/2005፣ አዋጅ ቁጥር 591/2007 የወንጀል ሕግ 808 ተላልፈዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ በማስረዳቱ በአምስት ክሶች  እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶ ነበር፡፡

የተጠቀሱባቸው #የሕግ ድንጋጌዎች #ዋስትና እንደማይከለክሉ በማስረዳት ሌተና ኮሎኔል ቢኒያም በጠበቃቸው አማካይነት ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን እንዲጠብቅላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የተጠቀሱት ሕጎች ከ15 ዓመታት በላይ ሊያስቀጧቸው እንደሚችሉ በመግለጽ፣ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲደረግ ተከራክሮ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄው የሕግ ክልከላ ያለበት ነው ወይስ አይደለም የሚለውን መርምሮ፣ የዓቃቤ ሕግን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በ30,000 ብር ዋስትና እንዲለቀቁና ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ የሚል ከሆነ በማለት አሥር ቀናት ለመጠባበቂያ ሰጥቶ ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕግም ይግባኙን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቦ ‹‹ያስቀርባል›› በመባሉ፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ዋስትናው መታገዱ ታውቋል፡፡

Via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiop
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቅናሽ

" ቅናሽ " የኦንላይን መገበያያ መድረክ ሲሆን የተለያዩ ሕይወቶን የሚያቀሉ ዕቃዎችን ያቀርባል፤ እቃዎችን ለመመልከት  👉 t.me/qnashcom ይቀላቀሉ።

አድራሻ  ፦ ጀሞ 1 ከለላ ህንፃ ግራውንድ ለይ G07

ማሳሰብያ : ሱቃችን ሲመጡ ትክክለኛ የኛ ሱቅ መሆኑ ያረጋግጡ  የራሳችን ሎጎ መኖሩን እና 329 / G07 መሆኑ ያረጋግጡ !
ስልክ: 0946966440 ፣ 0905464599 ፣ +251118639952

t.me/qnashcom

#ጥራት #ዋስትና #ቅናሽ