TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የተዘጋው መንገድ ሙሉ በሙሉ አልተከፈተም‼️

በተቃውሞ ሳቢያ የተዘጋው የአዲስ አበባ፤ አዋሽ ጅቡቲ መንገድ ዛሬም ሙሉ በሙሉ #አልተከፈተም። ወደ #ጅቡቲ የሚያመራው እና የኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ ንግድ የደም ሥር እንደሆነ የሚነገርለት የመኪና መንገድ አዋሽ ሰባት ከተማ ላይ ዛሬም ለተሽከርካሪዎች ዝግ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪ ለDW አረጋግጠዋል።

ተቃዋሚዎች ከትናንት ጀምሮ ዋናው መንገድ ከሚያልፍባት የአዋሽ ከተማ መውጪ እና መግቢያዎች እንደዘጉ መሆናቸውን የዐይን እማኙ ተናግረዋል።

በንግድ ሥራ የሚተዳደሩት የአዋሽ ነዋሪ "መንገዱ አልተከፈተም፤ ምንም የሚንቀሳቀስ ነገር የለም" ብለዋል።

በሎጊያ አካባቢ የሚገኘው የመንገዱ ክፍል ግን በዛሬው ዕለት ተከፍቶ እንቅስቃሴ መጀመሩን አንድ የከባድ መኪና አሽከርካሪ ተናግረዋል። ትናንት መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት መንገድ ላይ ማደራቸውን ለDW የገለጹት አሽከርካሪ ዛሬ ወደ ሎጊያ ከተማ ለመግባት መቻላቸውን ገልጸዋል። ተቃዋሚዎች ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር ላይ ስለመሆኑ መረጃ እንደደረሳቸው የገለጹት የከባድ መኪና አሽከርካሪ "ሕዝቡ ለሰባት ቀን ጊዜ ሰጥቶ አሁን መኪና መንቀሳቀስ ጀምሯል። በሰባት ቀናት ውስጥ ጥያቄያችን ካልተመለሰ #አሁንም_እንዘጋለን ብለዋል" ሲሉ ኹኔታውን አስረድተዋል።

በአዋሽ ሰባት የሚኖሩት ነጋዴ ግን የአካባቢውን የንግድ እንቅስቃሴ ክፍኛ ያስተጓጎለው የመንገድ መዘጋት "እስከ ነገው ዕለት ይቀጥላል" የሚል መረጃ ደርሷቸዋል። "ሶስት ቀን እያሉ ነው። ነገንም ይጨምራል መሰለኝ" ያሉት የአዋሽ ሰባት ነዋሪ ከመንግሥት መፍትሔ ካልተገኘ ሊከፈት እንደማችል በተቃውሞው የተካፈሉ ሲዝቱ መስማታቸውን ለDW አረጋግጠዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia