TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Assosa

ከሰሞኑን በአሶሳ ከተማ ውስጥ በግለሰቦች ቤት በተደረገ ፍተሻ የተከማቸ 50 በርሜል ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የአሶሳ ከተማ ፖሊስ ለኢዜአ በሰጠው ቃል ፤ በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸው 50 በርሜል ነዳጅ (ቤንዚን እና ናፍጣ) ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር በህብረተሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድቷል።

በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በከተማው #ቤንዚን እና #ናፍጣ በጥቁር ገበያ በሊትር እስከ 200 ብር እየተሸጠ መሆኑን ፖሊስ የጠቆመ ሲሆን የዚህ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ምንጭ በህጋዊ መንገድ ከነዳጅ ማደያዎች ተቀድቶ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ጥቂት ግለሰቦች እጅ መግባት መሆኑን አስረድቷል።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ #Update

ወደ ትግራይ ክልል #ነዳጅ መግባት መጀመሩን የክልሉ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ፤ ወደ መቐለ 10 ቦቴ ነዳጅ መግባቱን ያመለከተ ሲሆን ወደ ኩዊኃ እና ዓጉላም ነዳጅ መግባት መጀመሩን ጠቁሟል።

ከፌዴራል መንግስት ጋር ጥሩ ትብብር እየተደረገ ነው ያለው ቢሮ " እናተ ጋር ካለው ችግር አንፃር ቅድሚያ እንሰጣለን " ተብለናል ሲል ገልጿል።

ጦርነት ለመፈጠሩ በፊት በወር 12 ሚሊዮን ሊትር ናፍጣ ይገባ እንደነበር የገለፀው ቢሮው አሁን እየገባ ያለው ነዳጅ ከሚፈለገው አንፃር እጅግ በጣም ትንሽ ነው ብሏል።

መቐለ ውስጥ ካሉት 15 ማደያዎች ነዳጅ የገባው በ4ቱ ላይ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

ነዳጅ ለማግኘት እነማን ቅድሚያ አላቸው ?

አሁን እየገባ ያለው ነዳጅ በተወሰነ መልኩ ስለሆነ ፦

- አምቡላንስ
- እሳት አደጋ
- ውሃ አቅራቢ ቦቴዎች
- የመንግስት ተሽከርካሪዎች
- የእርዳታ አከፋፋይ አካላት
- ባንክ፣ ቴሌ፣ መብራት ኃይል
- በትራንስፖርት ቢሮ ታሪፍ የወጣላቸው ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ቅድሚያ እንደሚያገኙ ተመላክቷል።

የፋይናንስ እጥረት በበቂ ሁኔታ ነዳጅ እንዳይገባ እንቅፋት መሆኑን ያሳወቀው ቢሮው ችግሩን ለማፍታት ከባንክ ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ቤንዚን እና ናፍጣ ስንት እየተሸጠ ነው ?

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከፌዴራል መንግስት ለክልሉ እንደተላከ ለመረዳት ተችሏል።

በመቐለ #ቤንዚን በሊትር 60 ብር ከ57 ሳንቲም እየተሸጠ ሲሆን #ናፍጣ 66 ብር ከ58 ሳንቲም እየተሸጠ መሆኑን ከክልሉ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Photo Credit : Tigrai Television

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቤንዚን ? በአዲስ አበባ ቤንዚን ረጅም ሰዓት ሰልፍ ሳይሰለፉ ማግኘት ዘበት ከሆነ ሰነባብቷል። ባለፉት ሳምንታት በትንሽ በትንሹ የጀመረው የቤንዚን ሰልፍ ከሰሞኑን እጅግ ብሶበታል። በአንዳንድ ማደያዎች " ቤንዚን የለም " እየተባለ ሲለጠፍ ቤንዚን ያለባቸው ማደያዎች እጅግ በጣም ረጅም ሰልፍ ነው ያለው። በዚህም ምክንያት የመኪና አሽከርካሪዎች ቀናቸውን በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ይገኛሉ።…
#ቤንዚን

° " ቤንዚን ማግኘት ፈተና ሆኖብልናል " - አሽከርካሪዎች

° " የቤንዚን አቅርቦት ችግር የለም " - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን

አሁን ላይ በአዲስ አበባ ቤንዚን ማግኘት አስቸጋሪ እንደሆነባቸው አሽከርካሪዎች እየገለጹ ናቸው።

የተለያዩ ማደያዎች ላይ " ቤንዚን የለም " የሚል የተለጠፈ ሲሆን ቤንዚን አለባቸው የሚባሉና የሚቀዳባቸው ማደያዎች ላይ እጅግ በጣም ረጅም ሰልፎች ነው ያሉት።

አሽከርካሪዎች ቤንዚን ለመቅዳት ሰዓታትን ለመሰለፍ እየተገደዱ ነው። በዚህም ቀናቸውን በሰልፍ እያሳለፉ በመሆኑ ስራቸው እየተበደለ ነው።

ምንም እንኳን ከሰሞኑን ችግሩ ብሶ ቢታይም ባለፉት ሣምንታት አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሰልፎች ይታዩ ነበር።

ለመሆን ምንድነው የተፈጠረው ?

በዚህ ጉዳይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን መ/ቤትን ማብራሪያ ጠይቋል።

የተፈጠረው ነገር ምንድን ነው ? ስንል ጥያቄ ያቀረብንላቸው የባለስልጣኑ አንድ አካል በሰጡን አጭር ማብራሪያ፣ " የቤንዚን እጥረቱ የለም " ብለዋል፡፡

በከተማዋ ያለውን ችግር በተመለከተ ፤ " የእኛ ልጆች ኢስፔክሽን ሲወጡ ያዩት ነገር አሁን የቴሌ ብር አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ ነው፡፡ ምክንያቱም በካሽ ግብይት መፈጸም አይቻልም ፤ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ስለሆነ አብዛኛው ሰው ያንን ሲስተም ሳይጠቀም ቆይቶ በካሽ ትራንሰፈር እያደረገ ነበር፡፡ በዚያ ምክንያት አንዱ ከማደያ ላይ ነዳጅ ቀድቶ ለመውጣት ረጅም ሰዓት ይወስዳል " ብለዋል፡፡

" እናም ረጃጅም ሰልፍ የሚፈጠረው በዛ ነው እንጅ በእጥረት አይደለም " ብለው ለተጨማሪ መረጃ ወደ ሌላ የሚመለከተውን የተቋሙ አካልን የመሩን ሲሆን ሌላኛው አካል ማብራሪያ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ቢሰጡም በቀጠሮ ሰዓት በተደጋጋሚ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

በሌላ በኩል ፥ ባለስልጣን መ/ቤቱ ለካፒታል ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፥ በአዲስ አበባ ከተማ በአማካይ እስከ 1.4 ሚሊየን ሊትር ቤንዚን እያቀረበ መሆኑን አመልክቷል።

" በአዲስ አበባ ከሰሞኑ በነዳጅ ማደያዎች ላይ የተስተዋለው ያልተለመደ ሰልፎች ባለፈው ሣምንት በነበሩት ሁለት ቀናት ከበዓላት ጋር በተያያዘ የአቅርቦት መቀነስ በመኖሩ ነዉ " ብሏል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ፥ " በከተማዋ በቀን በአማካይ እስከ 1.4 ሚሊየን ሊትር ቤንዚን የሚቀርብ ቢሆንም የማደያዎቹ አገልግሎት አሰጣጥ ዝግታ መኖሩ እና የቤኒዚን ምርት ላይ ከፍተኛ የጥቁር ገበያ ፍላጎት መኖር ሠልፎችን ምክኒያት በማድረግ የአቅርቦት ዕጥረት ያለ በማስመሰል አጋጣሚውን ለትይዩ ገበያዉ ለመጠቀም መሞከር ይታያል " ሲል አስረድቷል።

" ከነዳጅ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ያለው ሁኔታ በአፋጣኝ እንዲስተካከል የተደረገበት እርምጃ እንዲወሰድ ተደርጓል " ያለዉ መ/ቤቱ " በዚህም በመዲናዋ ከመደበኛ ኮታ ተጨማሪ ቤንዚን እንዲቀርብ ሆኗል " ሲል አስታዉቋል።

" የየቤኒዚን ተጠቃሚ አሽከርካሪዎች አቅርቦት በበቂ ሁኔታ መኖሩን ተረድተው በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ ማደያዎችን በመጠቀም መገልገል ይችላሉ " ሲል አሳስቧል።

#AddisAbaba #Benzine

@tikvahethiopia