TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን #ቡራዩ_ከተማ አስተዳደር መልካ ገፈርሳ ቀበሌ ዛሬ በአንድ መዋዕለ ሕጻናት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኝ መጸዳጃ ቤት ተደርምሶ የ4 ሕጻናት ሕይወት አልፏል።

በአደጋው ስምንት ሕጻናት ወደ መጸዳጃ ቤቱ #ጉድጓድ ገብተው እንደነበር የዘገበው ኤፍ ቢ ሲ ከእነዚህ ውስጥም የአራቱ ሕይወት #ወዲያውኑ ማለፉን አመልክቷል።

ቀሪዎቹ አራት ሕጻናት ደግሞ በአደጋው ጉዳት ደርሶባቸው በቤተልና አለርት ሆስፒታሎች የሕክምና #ዕርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የከተማዋ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ በየኑ ረዳ ተናግረዋል።

በአደጋው ሕይወታቸው ላለፉት ሕጻናት ጥልቅ ሐዘን የተሰማቸው መሆኑን በከተማ አስተዳድሩ ስም የገለጹት ወይዘሮ #በየኑ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል። ትምህርት ቤቶች በግቢያቸው ውስጥ የሚገኙ መጸዳጃ ቤቶች ለተማሪዎች ደኅንነት ምቹ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የቡራዩ ከተማ ፖሊስ ምክትል ሳጅን #ሲሳይ_ዓለሙ በበኩላቸው መጸዳጃ ቤቱ የተደረመሰው በነበረበት የጥራት ችግር መሆኑን ተናግረዋል። ጉዳዩን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትም ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን ጠቁመዋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዚህ ወር በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ያጋጠሙ የእሳት አደጋዎች ፦

#ወልቂጤ_ከተማ (ጉራጌ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - በኩር ክ/ከተማ አርሴማ መንደር

• የደረሰው ጉዳት - 14 ቤት ሙሉ በሙሉ 6 ቤት በከፊል ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ነው።

#ቤሮ_ወረዳ (ምዕራብ ኦሞ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ሾላ ቀበሌ

• የደረሰው ጉዳት - 1840 መኖሪያ ቤቶች፣ 547 የንግድ ቤቶች፣ 37 የወርቅ ማህበራት ፣ 109 የወርቅ ማሽን በአጠቃላይ 586 ሚሊዮን 142 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እስካሁን አልታወቀም።

#ሆሳዕና_ከተማ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰው በአንድ የገበያ ማዕከል አዳራሽ

• የደረሰው ጉዳት - ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወድሟል። በርካታ የኤሌክትሮኒክስ እና አልባሳት ንግድ ድርጅቶች ከነ ንብረታቸው ወድመዋል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም። ፖሊስ እያጣራው ነው።

#መካነሠላም_ከተማ (ደቡብ ወሎ ዞን)

• በመካነ ሠላም ከተማ በንግድ ቦታ ላይ ድንገት የተከሰተ አደጋ።

• የደረሰው ጉዳት - በሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች፣ በሴቶች የውበት ሳሎን፣ በልብስ ስፌት ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሳል። ከ100 ሺህ ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ተቃጥሏል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም።

#ወላይታ_ሶዶ_ከተማ (ወላይታ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - መርካቶ ገበያ

• የደረሰው ጉዳት - 1 ቢሊዮን 57 ሚሊዮን 670 ሺህ ብር ወድሟል። 42 ሺህ ገደማ ዜጎች በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ለቀውስ ተጋልጠዋል።

• የአደጋው መንስኤ - አንታወቀም፤ በፖሊስ እየተመረመረ ይገኛል።

#ማሻ_ከተማ (ደቡብ ወሎ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - አዲሱ መናኸሪያ አካባቢ

• የደረሰው ጉዳት - 2 ሼዶች በውስጣቸው ካለ ሙሉ ንብረት ጋር ወድመዋል። ሼዶቹ በውስጣቸው ሱቆች፣ ፖስታ ቤት፣ የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ይገኙበታል። 1 ሚሊዮን 224 ሺህ 936 ብር የሚገመት ሃብት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም፤ እየተጣራ ነው።

#ዌራ_ወረዳ (ሀላባ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ላይኛ በደኔ ቀበሌ በጦሮንቦራ ንዑስ

• የደረሰው ጉዳት - 11 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እህል የተከመረበት ቦታ ላይ በሶላር ባትሪ ቻርጅ የተሰካ የሞባልይ ስልክ ፈንድቶ።

#ምሻ_ወረዳ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ኤራ ጌሜዶ፣ ኩናፋ፣ ጉና ማጋቾ ቀበሌዎች

• የደረሰው ጉዳት - 128 ዶሮዎች፣ 243 ኩንታል የተለያየ እህል፣ 18 የንብ ቀፎ ፣ የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶች በድምሩ 23 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - የተፈጥሮ እሳት

#ሶሮ_ወረዳ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - በጃቾ ከተማ

• የደረሰው ጉዳት - ከ250 ሺህ ብር በላይ ወድሟል።

• የአደጋው ምክንያት - የመብራት ኮንታክት

#ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ

• የአደጋው የደረሰበት ቦታ - ዋናው ግቢ ህንፃ 3

• አደጋው የኤሌክትሪክ መቆጣጣሪያ ላይ የተነሳ ነው።

• የደረሰው ጉዳት - መጠኑ ያልተገለፀ ንብረት ጉዳት ደርሶበታል።

#ቡራዩ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ገፈርሳ ኖኖ ቀበሌ ገብርኤል አካባቢ

• የደረሰው ጉዳት - 16 ሱቆች ፣ 3 መኖሪያ ቤቶች፣ 3 ባርና ሬስቶራንቶች ቃጠሎ ደርሶባቸዋል። በአጠቃላይ ግምንቱ 10 ሚሊዮን ብር የሆነ ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እየተጣራ ይገኛል።

#ባህር_ዳር_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ቀበሌ 3 ጉዶባህር የሚባለው ሰፈር

• የደረሰው ጉዳት - 22 መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። በገንዘብ 300 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ተቃጥሏል።

• የአደጋው መንስኤ - እንጀራ ከሚጋገርበት ወቅት ከተቀጣጣይ ነገሮች የተነሳ ነው።

#ጅግጅጋ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ቀበሌ 2 ልዩ ስሙ ድብኡራሾ ሱቅ

• የደረሰው ጉዳት - 7 የምግድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ንብረት አደጋ ደርሶበታል ይህም 1.2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ነው።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም። ከአንድ ቤት ውስጥ ነው የተነሳው ተብሏል።

#ደብረማርቆስ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ጉልት ገበያ አዳራሽ

• የደረሰው ጉዳት - 48 የንግድ ሱቆች ጉዳት ደርሶባቸዋል። አልባሳት፣ ሸቀጣሸቀጥ፣ ቅመማቅመም፣ አትክልት እና ፍረፍሬ ምርት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። የንብረት ግምት እየተጣራ ነው።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም በፖሊስ እየተጣራ ነው።

በዚህ ወር በደረሱት የእሳት አደጋዎች በርካቶች ጥረው ግረው ያፈሩት ንብረታቸው ፣ ቤታቸው ወድሞባቸው ሜዳ ላይ ወድቀዋል።

በርካቶች ህይወታቸው ተመሰቃቅሏል ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ስራ አጥ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

* የአብዛኛዎቹ የእሳት አደጋዎች ትክክለኛ መንስኤ በግልፅ አይታወቅም።

በቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahFamily

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia