TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሙሉ በሙሉ #በሴቶች እየተመራ ወደ #ኦስሎ የተጉዋዘው የበረራ ቡድን በቦታው ሲደርስ በዲፕሎማቶች እና የኢትዮጵያውያን ማሕበረሰብ አባላት #ደማቅ_አቀባበል ተደርጎለታል።

Via የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጀመረ ሀገራችን በድርቤ ወልተጂ የተወከለችበት የ800 ሜትር የሴቶች #ፍፃሜ ውድድር ተጀምሯል። ድል ለሀገራችን 🇪🇹❤️ ! @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ🇪🇹

በ800 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ብቸኛዋ የሀገራችን ተወካይ ድርቤ ወልተጂ አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች። ነሀስ ለማግኘት ከፍተኛ ትግል ነው ያደረገችው 👏

ውድድሩን ፦

1ኛ አሜሪካ 🥇(ወርቅ)
2ኛ እንግሊዝ 🥈(ብር)
3ኛ ኬንያ 🥉(ነሀስ) በመሆን አጠናቀዋል።

ሀገራችን #ኢትዮጵያ በተለይም #በሴቶች ከፍተኛ ድል ያስመዘገበችበት የኦሪገን ዓለም ሻምፒዮና በዚህ አብቅቷል።

@tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ሰለሞን ባረጋ ለኢትዮጵያ የነሃስ ሜዳሊያ አምጥቷል። በግላስኮ ዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በወንዶች 3 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያ በአትሌት ሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የነሃስ ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች። ጌትነት ዋለ 4ኛ ወጥቷል። ኢትዮጵያ በዚህ ርቀት በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ላይ የወርቅ ሜዳሊያ ሳታሸንፍ ስትቀር ከ3 ተከታታይ ውድድሮች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ሰለሞን ባረጋ…
#ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 1ኛ ሆና አጠናቀቀች።

በዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም ደግሞ 5 በመሆን አጠናቃለች።

ከማርች 1-3/2024 በእንግሊዝ ግላስጎ ሲካሄድ የ19ኛው የዓለም የቤት ዉስጥ ሲካሄድ ነበር። በሻምፒዮናው ከ130 በላይ አገሮች የተውጣጡ ከ650 በላይ አትሌቶቸ ተሳትፈዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በ800 ሜትር፣ በ1500 ሜትር እና በ3000 ሜትር በሴትና በወንድ  በአጠቃላይ በ8 ሴቶች እና በ5 ወንዶች በድምሩ በ13 አትሌቶች ተሳትፋለች።

በዚህም #በሴቶች 800 ሜትር ፅጌ ዱጉማ እና በሴቶች 1500 ሜትር ፍሬወይኒ ሀይሉ #የወርቅበሴቶች 3000 ሜትር ጉዳፍ ፀጋይ የብር እንዲሁም #በወንዶች 3000 ሜትር ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝተዋል።

ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያ በሁለት ወርቅ አንድ ነሀስ በአንድ ብር በአጠቃላይ በአራት ሜዳሊያዎች በሜዳልያ ሰንጠረዡ   ከአፍሪካ 1ኛ  ከዓለም 5ኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሳለች።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

@tikvahethiopia