TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የሶማሊላንዱ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ምን አሉ ?

የሶማሊላንዱ ፕሬዝደንት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ከኢትዮጵያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ መፈረሙን ገልጸዋል።

በዚህም ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ ሪፐብሊክ እውቅና እንደምትሰጥ ፤ ሶማሊላንድ በበኩሏ ኢትዮጵያ የባህር ኃይል እና የንግድ ባህር በር መዳረሻ እንዲኖራት ለ50 ዓመታት #በሊዝ እንደምትሰጥ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ጉዳይ በትላንትናው መግለጫ ወቅትም የተናገሩት ሲሆን አሁንም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አረጋግጠዋል።

ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት በኩል እስካሁን በስምምነቱ መሰረት ለሶማሊላንድ የነፃ ሀገርነት እውቅና እንሰጣለን የሚል ቃል አልወጣም።

በሌላ በኩል ስምምነቱ ያስቆጣቸው የሶማሊያ መንግሥት የካቢኔ አባላት ዛሬ ተሰብሰበው ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሏል።

ሶማሊያ ፤ ራዝ ገዟን ሶማሊላንድ እንደ አንድ ሉኣላዊ ግዛቷ ነው የምትቆጥራት።

ለሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ቅርብ የሆኑ ምንጮች ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በይፋ ይቅርታ ካልጠየቁ እና ለሶማሊያ ልዓላዊነት ክብር ካልሰጡ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን እንደምታቋርጥ ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ሶማሊያ ፤ በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል የተደረሰውን ስምምነት በመቃወም እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል እኚሁ ለፅ/ቤቱ ቅርብ የሆኑት ምንጮች አመልክተዋል።

ተጨማሪ . . .

በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል ከተፈረመው ስምምነት ጋር በተያያዘ ዛሬ ማክሰኞ ሁለቱ የፌደራል ፓርላማ ምክር ቤቶች አስቸኳይ የጋራ ስብሰባ እንደሚያደርጉና የሶማሊያው ፕሬዝዳንትም ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ንግግር እንደሚያደርጉ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ በራዝ ገዟ ሶማሊላንድ ይፋዊ መግለጫ ወጥቷል። በዚህም መግለጫ ስምምነቱ ታሪካዊ ነው ተብሏል። ይህ ታሪካዊ ስምምነት ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እውቅና በመስጠት በሊዝ የባህር በር / ለባህርኃይሎቿ የባህር መዳረሻ እንደምታገኝ መግለጫው ይገልጻል። " ስምምነቱ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ነው " ያለው መግለጫው ለኢትዮጵያ የባህር ኃይል ተጠቃሚነት 20 ኪሎሜትር የባህር በር እንደሚሰጥ…
#Ethiopia #Seaport

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከሶማሊለንድ ጋር ስለተፈረመው ስምምነት ምን አሉ ?

- ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቃሚ እንድትሆን በምክክር፣ በሰላማዊ መንገድ ብቻ በሰጥቶ መቀበል መርህ የተለያዩ የዲፕሎማሲ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል።

- ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋር ብዙ ሞክረን ያልተሳካው ከሶማሊላንድ ጋር በተመሳሳይ መንገድ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።

- መንግሥት አቋሙን ይፋ ካደረገ በኃላ ያሉ ሃብቶችን ከመጋራት አንፃር የነበረው ጉዳይ ጥርቶ ከወጣ በኃላ ዝርዝር ውይይት ሲካሄድ ነው የቆየው።

- ጉዳዩ መልክ እስኪይዝ በተወሰነ በጠባብ ቡድን፣ በመሪዎች ደረጃ እና በተወሰኑ አካላት ደረጃ እንዲያዝ እየበሰለ ሲሄድ ደግሞ ሁለቱም አካላት የየራሳቸውን አመራር እያሳተፉ የሚሄዱበት ሁኔታ እንዲፈጠር ተደርጓል።

- የወደብ ስምምነት ተጠቃሚነት በሊዝ አማካኝነት የሚፈፀም ነው።

- ይህ የስምምነት ማዕቀፍ ሶማሌለንድ እና ኢትዮጵያ አንዳቸው ጋር ያለውን ሃብት ለመጋራት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ እድል የሚያሰፋበት፣ በመከላከያና ደህንነት ዘርፍ ኢትዮጵያ ያላትን አቅምና ልምድ ለሶማሊላንድ የምታጋራበት ፤ የጋራ ጥቅማቸውን ማስጠበቅ የሚችሉበት አቅም ይገነባል።

- የስምምነቱ ማዕቀፍ ኢትዮጵያ ሶማሌላንድ ውስጥ Military base እና Commercial maritime ሰፈር እንዲኖራት ይፈቅዳል። ይህ #በሊዝ የሚታሰብ ይሆናል። ለ50 ዓመት እና ከዛ በላይ #በማራዘም የሚካሄድ እንዲሆን ያደርጋል።

- ኢትዮጵያ አማራጭ ወደብን እድል ለማግኘት በርበራ ኮሊደርን የምታሰፋበት ፣ የመከላከያ አቅሟን አዲስ በምትከራየው ቦታ የምታጠናክርበት እድል ይሰጣል።

- ኢትዮጵያ ለሊዝ ተጠቃሚነቷ ቴሌኮም ይሁን፣ አየር መንገድ ይሁን ጥቅም በሚያስገኙ መሰረተ ልማቶች ላይ ድርሻ ትሰጣለች። ምን ያህል ነው ? የሚለው የሚከፈለው ሊዝም ምን ያህል ይሆናል ? የሚለው በዝርዝር ውይይቶች ይወሠናል።

- በጤና፣ በትምህርት ፣ በመከላከያ የሚሰሩት ዝርዝር ስምምነቶች በተናጠል ውይይት ይካሄድባቸዋል። ወደ ፓርላማ ሄደው የሚፀድቁ በርካታ ስምምነቶች ከዚህ ይፈልቃሉ።

- የጋራ የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ አጠቃላይ ማዕቀፍ ሁለቱ አካላት በጋራ ተባብረው የሚያድጉበትን ማዕቀፍ ነው የሚያስቀምጠው። ዋና ዋና አንጓዎች ተቀምጠዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር የምታገኝበትን ዕድል በተጨባጭ ወደመሬት ለማውረድ እድል ይሰጣል።

- ስምምነቱ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ሂደቱ ያልቃል / ወደ ተግባር / ስራ ይገባል።

- ከሌሎች ሀገራት ጋር የጀመርናቸው አሉ #ከኤርትራ ጋር በዝርዝር ውይይት ተጀምሮ የሆነ ቦታ ላይ ነው የቆመው።

- ኢትዮጵያ አንድ ወደብ ፣ ሁለት ወደብ ፣ ሶስት ወደብ ሳይሆን ፤ ኢትዮጵያ አሁን ባለው ሁኔታ እያደገች ከሄደች ሁሉም ቀጠናዎች የሁሉም ጫፎች የኢትዮጵያን ምርቶች የሚያስገቡበት በር ያስፈልጋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በማብራሪያቸው በስምምነቱ ሶማሊያ ልዓላዊ ግዛቴ ናት ለምትለው ራስ ገዟ #ሶማሌላንድ በይፋ የነፃ ሀገርነት እውቅናን ትስጠ እንደሆነ የተናግሩት አንዳች ነገር የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ራስ ገዟ ሶማሊላንድ የሶማሊያ መንግሥትን አስጠነቀቀች። ከኢትዮጵያ ጋር የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ለማደናቀፍም ይሁን ለመቃረን የሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ ይሁን አካል ላይ እርምጃ ወስዳለሁ ብላለች። የራስ ገዟ ሶማሌላንድ" የሚኒስትሮች ምክር ቤት " ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ነበር። ከስብሰባው በኃላ ባወጣው ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ ፦ - ምክር ቤቱ እ.ኤ.አ. ጥር 1/2024…
#ሀርጌሳ

" ሀገራችንን አልሸጥንም " - ሙሴ ባሂ አብዲ

ባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ የነበሩት የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ዛሬ ሐሙስ ዕለት ወደ ሀርጌሳ ተመልሰዋል።

ፕሬዚዳንቱ ሀርጌሳ ሲገቡ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

አደባባይ ወጥቶ ለተቀበላቸው ህዝብ ባሰሙት ንግግር ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑ ገልጸዋል።

ፕሬዜዳንቱ " ሀገራችንን አልሸጥንም " ያሉ ሲሆን " ኢትዮጵያ የባህር ሃይል ጦር ሰፈር #በሊዝ ነው የምትከራየው " ብለዋል።

" ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ እውቅና ለመስጠትም ተስማምታለች " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ መቼ እንደሆነ ቀኑን በግልፅ ባይናገሩም የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት #በቅርቡ ለሶማሌላንድ እውቅና እንደሚሰጥ በድጋሚ ለህዝባቸው ገልጸዋል።

" ይህ የሶማሌላንድ ህዝብ ላለፉት ሶስት አስርት አመታት የደረሰበት ትልቅ ስኬት ነው " ሲሉም ገልጸዋል።

ስምምነቱ በሁለቱም ወገን በኩል ፍላጎትና ጥቅማቸውን መሰረት ያደረገ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል ፤ ሶማሌላንድን እንደ ራሷ አንድ ግዛት የምትቆጥራትና የተፈረመው ስምምነት ሉዓላዊነቴን ጥሷል በሚል የተቃወመችው ሶማሊያ ውስጥ ዛሬ የተቃውሞ የአደባባይ ሰልፎች ሲደረጉ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል።

ፎቶ / ቪድዮ ፦ ሶማሌላንድ፣ ሀርጌሳ (ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 206 ዓ/ም)

@tikvahethiopia