TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፖሊስ‼️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በህገ-ወጥ መንገድ ግለሰቦችን በመመልመል በጫካ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ የነበሩ 10 አሰልጣኞች #መያዛቸውን ፖሊስ ገለጸ፡፡

በክልሉ ህዝብ ላይ #ጥፋት ለመፈጸም በአሶሳ ወረዳ ገንገን ቀበሌ በጫካ ውስጥ ህገ-ወጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 51 #ተጠርጣሪዎች በቅርቡ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ነጋ ጃራ ዛሬ ለኢዜአ እንዳስታወቁት በሕገ ወጥ መንገድ ስልጠና ሲሰጡ የነበሩት አሠልጣኞች ሰሞኑን በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጄነራሎቹ⁉️

የቀድሞው የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ ዋና ሃላፊ ሜጀር ጀነራል #ክንፈ_ዳኘው መያዛቸው ተነገረ። ሃላፊው ከትግራይ የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው ጀነራሉ የተያዙት ትናንት ማምሻ ሁመራ ከተማ ውስጥ ነው።

#የትግራይ ልዩ ፖሊስ ጀነራሉን ከያዘ በኋላ ለፌደራል መንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች #ማስረከቡን ምንጮች አስታውቀዋል። ከጀነራል ክንፈ ዳኘው በተጨማሪ የቀድሞ ኢንሳ በሚል ምህጻረ ቃል የሚጠራው የመረጃ ቴክኖሎጂ መስሪያ ቤት የቀድሞ ሃላፊ ሜጀር ጀነራል #ተክለብርሃን_ወልደአረጋይም ከሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ጋር #መያዛቸውን የተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዘግበው ነበር።

ይሁን እና ጀነራል ተክለብርሃን የፍርድ ቤት #የማሰሪያ ትዕዛዝ አልተሰጠባቸውም በሚል እንዳልተያዙ ምንጮቼ ገልጸዋል ብሏል የጀርመን ድምፅ ራድዮ የአማርኛው አገልግሎት ክፍል።

ጉዳዩን #ለማጣራት የተለያዩ መሥሪያ ቤቶችን እያነጋገረን ነው እንደደረሰን መረጃውን እናቀርባለን ብሏል የጀርመን ድምፅ።

ሁለቱን ጀነራሎች ጨምሮ በርካታ የቀድሞ ከፍተኛ የጦርና የመረጃ (ስለላ) ባለሥልጣናት እሥረኞችን በማሰቃየት እና በሙስና ወንጀል እንደሚጠረጠሩ የኢትዮጵያ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ትንንት አስታውቆ ነበር።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በአዲስ አበባ በሞተር ብስክሌት በመታገዝ የቅሚያ ወንጀል ከፈፀሙ ግለሰቦች መካከል ግማሽ ያህሉ #መያዛቸውን የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የኢንዶክትሬሽንና ህዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር #ፋሲካ_ፈንታ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ 61 በሞተር ሳይክል የተደገፈ ቅሚያ በከተማዋ ተፈፅሟል።

ወንጀሉ የተፈፀመው በከተማዋ በሚገኙ 8 ክፍለ ከተሞች መሆኑንም ተናግረዋል።
ከፍተኛ የቅሚያ ወንጀል የተፈፀመበት የቦሌ ክፍለ ከተማ 21 በሞተር ሳይክል የተደገፉ ወንጀሎች የተፈፀመበት ሲሆን ዝቅተኛ የቅሚያ ወንጀል በተፈፀመበት ልደታ ክፍለ ከተማ አንድ ወንጀል ተፈጽሟል።

በአቃቂ ቃሊቲና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች ምንም አይነት በሞተር ብስክሌት የተደገፈ ቅሚያ አለመፈጸሙን ገልጸዋል።
ወንጀል ፈፃሚዎቹ በራሳቸውና በተከራዩት የሞተር ብስክሌት የቅሚያ ወንጀሉን እየፈፀሙ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር ፋሲካ ወንጀሉን ፈጽመው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች በፍርድ ቤት ጉዳያቸው እንደተያዘና ቀሪ የወንጀል ፈጻሚዎች ለመያዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

ፖሊስ የሚያከናውነውን ወንጀል የመከላከል ተግባር ኅብረተሰቡ ወንጀል ፈፃሚዎችን #የማጋለጥና ወንጀል የመከላከል ስራው እንዲደግፍ ጥሪ አቅርቧል።

”ወንጀልን መከላከል በፖሊስ ጥረት ብቻ የሚከወን አይደለም” ያሉት ኮማንደር ፋሲካ የኅብረተሰቡ ድጋፍ ከተጠናከረ ወንጀል ፈፃሚዎች ሊያመልጡ እንደማይችሉም ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ከቅሚያ ወንጀሉ በተጨማሪ ሌሎች የትራፊክ ደንብ ጥሰቶችን የፈፀሙ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ላይም እርምጃ መወሰዱን ኮማንደሩ ተናግረዋል።

#ሀሰተኛ_መንጃ_ፈቃድ ይዘውና ያለመንጃ ፍቃድ ሞተር ብስክሌት ሲያሽከረክሩ የነበሩ እንዲሁም ሲያሽከረክሩ ማሟላት የሚገባቸውን እንደሄልሜት ያሉና ሌሎች የትራፊክ ደንብ ጥሰት የፈፀሙ ከ7ሺህ በላይ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia