TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
 #Tigray

በአንድ ቀን ብቻ የ 7 ሰዎች ህይወት በትራፊክ አደጋ ሲቀጠፍ ከ20 በላይ ሰዎች የአከል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ከሟቾቹ ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባል ናቸው።

የትራፊክ አደጋው ያጋጠመው ግንቦት 28/2016 ዓ.ም በአንድ ቀን በሁለት የትግራይ አከባቢዎች ነው።

ከዓድዋ ከተማ ወደ ጥንታዊትዋ የይሓ የቱሪስት ማእከል በየዓመቱ የሚከበረውን የቤተክርስትያን ዝክር ለማክበር በግል መኪና ሲጓዙ የነበሩት የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ በተከሰተው የትራፊክ አደጋ አራቱ ለህልፈት ሲዳረጉ ፤ ከ10 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል።

በዚያው በተመሳሳይ ቀን በሓውዜን ወረዳ ሙሽሮች የጫነ መኪና ከሞተር ሳይክል ጋር በመጋጨቱ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ10 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል።

የአደጋዎቹ መነሻ በማይመች ቦታ ከሚፈቀደው በላይ መፈጥንና መጫን መሆኑ የትራፊክ ባለሙያዎች ገልጸዋል።

አሽከርካሪዎች ለራሳቸውና ለሰው ደህንነት ትኩረት ሰጥተው እንዲያሽከርክሩ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በትግራዩ ጦርነት ምክንያት በየቦታው የተቀበሩ እና የተጣሉ ተተኳሾች፣ ፈንጂዎች አሁንም በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረሳቸው ቀጥሏል። ዛሬ ዓርብ ግንቦት 16 / 2016 በተጣለ ተተኳሽ ባል እና ሚስት ህይወታቸው አልፏል። አደጋው ያጋጠመው በትግራይ ክልል ፣ በማእከላዊ ዞን ቆላ ተምቤን ምረረ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ሲሆን በተተኳሹ ምክንያት የባል ህይወት ወድያው አልፏል። የሟች ሚስት ወደ…
#Tigray🚨

በሓውዜን ወረዳ በተጣለ ተተኳሽ #የ4_ሰዎች ህይወት ጠፋ።
 
በትግራዩ ጦርነት ምክንያት በየቦታው የተቀበሩ እና የተጣሉ ተተኳሾች ፣ ፈንጂዎች አሁንም በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረሳቸው ቀጥሏል።

ሰኔ 1/2016 ዓ.ም በትግራይ ክልል በምሰራቃዊ ዞን ፤ ሓውዜን ወረዳ ማይጎቦ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በፈነዳ ተተኳሽ የ4 ወገኖች ህይወት #ተቀጥፏል

ከአራቱ የአደጋው ሰለባዎች ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባል ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሓውዜን ወረዳ ኮሙኒኬሽን ባገኘው መረጃ  ፥ ሟቾቹ ከ 9 እስከ 14 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ገና ትንንሽ ልጆች ናቸው።

ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የሰኔ 1/2016 ዓ/ም አደጋን ጨምሮ በትግራይ የተለያዩ ወረዳዎች በተጣሉ እና በተቀበሩ  ተተኳሾችና ፈንጂዎች ከ107 ሰዎች ላይ የሞት ፣ የአካል መጉደል አደጋ ደርሷል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray

ህዝቡ በህብረት ስራ ማህበራት ስም ከሚፈፀሙ #የማደናገር እና #የማጭበርበር ተግባራት ራሱ እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ።

ይህን የማስጠንቅያ ጥሪ ያቀረቡት የትግራይ ፍትህ ቢሮና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በጋራ ሆነው ነው።

መንግስታዊ ተቋማቱ  " አቦ " በሚል ስያሜ በቤቶች ግንባታና ልማት " ተሰማርቻለሁ ... ተመዝገቡ የቤት ባለቤት ሁኑ " በሚል እንቅስቃሴ በማካሄድ የሚገኘው የህብረት ስራ ማህበር እውግዘዋል ፤  እግድም ጥለዋል።

መንግስታዊ ተቋማቱ ባወጡት መግለጫ ፥ " አቦ " በሚል ስም የሚታወቀው የህብረት ስራ ማህበር ፥ " ከደደቢት ማይክሮፋይናንስ በጋራ በትግራይ 5 ከተሞች ቤቶች ገንብቼ አስረክባሎህ " ብሎ ከሰነ 3/2016 ዓ.ም ያስጀመረው የምዝገባ እንቅስቃሴ ህጋዊ አይደለም  ብለዋል።

" አቦ " የተባለ የህብረት ስራ ማህበር በ5 የትግራይ ከተሞች ቤት ገንብቶ ለማስረከብ የተሰጠው መሬት የለም ያለው የትግራይ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ድርጅቱ ከድርጊቱ እንዲታቀብ አስጠንቅቋል።

የመኖሪያ የቤቶች ግንባታ በህብረት ስራ ማህበር የማደራጀት ስልጣን የተሰጠው ለፍትህ ቢሮ ነው ያለው የክልሉ ፍትህ ቢሮ ፥ " አቦ የቤቶች ግንባታ ህብረት ስራ ማህበር " በህግ ባልተፈቀደለት የስራ ዘርፍ ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ እግድ እንደጣለበት አስገንዝቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#Tigray
 
ወደ 26 የትግራይ ወረዳዎች ለእርዳታ በመጓጓዝ ላይ ያለ #የተበላሸ የማሽላ እህል ለህዝብ እንዳይከፋፈል ታገደ።

እግዳውን ያስተላለፈው የትግራይ ክልል ምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ነው።

ከማሽላ እህሉ በተወሰደ የናሙና ምርመራ ውጤት መሰረት ፦
- መጥፎ ሽታ ያለው መሆኑ፤
- በነቀዝ የተበላና ወደ ዱቄትነት የመቀየር ደረጃ የደረሰ በመሆኑ ፤
- በአጠቃላይ የበሰበሰና የተበላሸ በመሆኑ፡
ለምግብነት ቢውል የሚያስከትለው የጤና ጠንቅ እጅግ ከባድ ስለሆነ እህሉ በያለበት መጋዘን እንዲታገድ ተወስኗል።

በመጓጓዝ ላይ ያለውም እንዲቋረጥ ሲል መ/ቤቱ ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለወረዳዎቹ በፃፈው የእግድ ደብዳቤ አስታውቀዋል።

እግድ የተጣለበት የማሽላ እህል ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' በሚል በክልሉ የተቋቋመው በድርቅ እና በሰብአዊ ቀውስ ለተጎዱ ወገኖች ለማገዝ ከአገር ውስጥና ከውጭ ለጋሾች ባሰባሰው ብር የተገዛ ነው።

ግብረ ሃይሉ ሰነ 5 ቀን 2016 ዓ/ም ለሚድያዎች በሰጠው መግለጫ  እህሉ በግዢ ጊዜ በናሙና ከቀረበው ውጭ የሆነና የተበላሸ ለጤና ጠንቅ መሆኑ ስለተደረሰበት እንዳይከፋፈል ሲል ገልጿል።

መግለጫው ተከትሎ በማሽላ እህሉ ምርመራ ያካሄደው የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ፤ እህሉ የተበላሸና ለምግብነት ውሎ የሚያስከትለው አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት  በ90 ሚሊዮን ብር በጨረታ የተገዛው የማሽላ እህል #እንዲታገድ ወስኗል።

እግዱን ተከትሎ ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ በሰጠው መግለጫ " እህሉ ከጥቅም ውጭ እንዲሆን ፤ ለመግዣ የተመደበው 90 ሚሊዮን ብር በ26 ወረዳዎች ለሚገኙ ተረጂዎች በጥሬ ገንዘብ እንዲከፋፈል ፤ የጨረታ ሂደቱ ተሰርዞ አህል አቅራቢው ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዘው 9 ሚሊዮን ብር እንዲወረስ ወስኛለሁ " ብሏል። 

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
#መቐለ

@tikvahethiopia            
#Mekelle

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመቐለ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ዛሬ ነው።

በዚህም በጊዜያዊነት የጀመራቸው አገልግሎቶች ፦
☑️ ፓስፖርት ማደስ፣
☑️ የጠፋ ፓስፖርት መተካት፣
የተበላሸ ወይ እርማት የመስጠት አገልግሎቶች እንደሆነም ተገልጿል።

የመቐለ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፅህፈት ቤት ተወካይ ክንፈሚካኤል ረዳሀኝ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ከጦርነቱ በፊት በፅህፈት ቤቱ በርካታ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር አመልክተዋል።

በጦርነቱ ሁሉም አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት በኃላ ቢዘገይም የፓስፓርት እድሳት አገልግሎት አሁም መሰጠት እንደተጀመረ ገልጸው ፤ " በመላ ትግራይ የሚገኙ የፓስፓርት እድሳት ፈላጊዎች በአካል መምጣት ሳይስፈልጋቸው ባሉበት ሆኖው በኦንላይን መገለግል ይችላሉ " ብለዋል።

ተገልጋዮች ወደ (መቐለ) ፅ/ቤቱ መምጣት ያለባቸው ሁሉም ነገር ጨርሰው ማህተም ለማስመታት ብቻ እንደሆነ ጠቁመዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
            
#Tigray

" ከዚህ (ከሰላማዊ) ውጭ ያለው መንገድ አዋጭ አይደለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

36ኛው ዓመት " የትግራይ የሰማእታት ቀን " ዛሬ ሰነ 15 ቀን 2016 ዓ/ም በመቐለ የሰማእታት ሀውልት ተከብሯል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ንግግር አድርገው ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " ልጆቻችን በአጋቾች ለሞት እየተጋለጡ ፣ ተፈናቃዮች በመቆያ መጠለያዎች በፀሀይና በብርድ እየተሰቃዩ ባሉበት ወቅት የሰማእታት ቃልና አደራ በተሟላ መልኩ እያከበርን ነው በማለት ማምለጥ አይቻለንም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የሰማእታት ቃል አክበረናል የምንለው በንግግር ሳይሆን በተግባር መሆን ይገባዋል " ብለዋል።

" የሰማእታት ቃል ማክበር ማለት በትግራይ የሃሳብ ብዙህነት እንዲከበር መስራት ለስልጣን ሳይሆን ለህዝብ ጥቅም መዋደቅ ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " አንዳንዶቻችን ይህንን በመዘንጋት ለስልጣንና ለሃብት ስንባላ መታየት አሳፋሪ ነውና ከዚሁ መውጣት ይህንን መቀየር አለብን " ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው " ተፈናቃዮችን በጀመርነው ሰላማዊ መንገድ ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ በአንድነት መንፈስ የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ ተፈፃሚ እንዲሆን መስራት አለብን " ያሉ ሲሆን " ከዚህ ውጭ ያለው መንገድ አዋጭ አይደለም " ሲሉ አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት እና ምክትል ፕሬዜዳንት በጋራ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ። ስራ መልቀቂያውን ያስገቡት ፤ " በፍትህ እና የዳኝነት ሰርዓቱ ለውጥ ለማምጣት ያሰብናቸው ፣ ያቀድናቸው የጀመርናቸው ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች ለማሳካት የሚያስችል ሁኔታ ማግኘት ስላልቻልን ነው " ብለዋል። ሰኞ ሰኔ 17/2016 ዓ.ም የተፃፈው የስራ መልቀቅያ ደብዳቤ በበርካታ የማህበራዊ…
#Update

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ ጥያቄያችን ለመመለስ ቃል ስለገባ የስራ መልቅቅያ ጥያቄያችን ትተነዋል " - የትግራይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንትና ምክትል ፕሬዜዳንት

የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንትና ምክትል ፕሬዜዳንት ያስገቡትን የመልቀቂያ ደብዳቤ እንደተውት አሳወቁ።

ፕሬዜዳንቱና ምክትል ፕሬዜዳንቱ ይፋ ባደረጉት መግለጫ ፤ ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ያቀረቡት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ተከትሎ ሰኔ 18 /2016 ዓ.ም ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ውይይት ማደረጋቸውን ገልጸዋል።

በዚ ውይይት ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች ለመመለስ ቃል በመገባቱ ስራ የመልቀቅ ጥያቄያቸውን እንደተውት አሳውቀዋል።

ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች ምን እንደሆኑ በግልፅ ያላብራሩ ሲሆን ከላይ እስከ ታች የሚገኘው የፍርድ ቤት አካል ስራውን ተረጋግቶ እንዲሰራ መልእክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዜዳንቱና  ምክትል ፕሬዜዳንቱ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ተከትሎ የወረዳና የዞን ፍርድ ቤቶች ስራ የማቆም አድማ መምታት ጀምረው ነበር

ከክልሉ ፕሬዜዳንት ከተደረገው ውይይት በኃላ ችሎቶች ተከፍተው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል በአካል ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

ከመቐለ ውጪ በመላው ክልል ያሉ ፍርድ ቤቶች መደበኛ አገልግሎት መስጠት መቀጠላቸው የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የፕሮቶኮል ሹም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#Tigray #Mekelle

ባለፉት 11 ወራት ብቻ በመቐለ 12 ሴቶች ሲገደሉ 80 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል።

የመቐለ ፓሊስ ከሀምሌ 2015 ዓ/ም እስከ ሰኔ 2016 ዓ/ም ባሉት 11 ወራት ግድያ ጨምሮ 4,340 ከባድና ቀላል የወንጀል ተግባራት በከተማዋ እንደተፈጸሙ አሳውቋል።

የተፈፀሙት ከባድና ቀላል ወንጀሎች በቁጥር ፦
 
➡️ የሴቶች ግድያ 12 

➡️ አስገድዶ መድፈር 80

➡️ ስርቆት 1,953

➡️ ድብደባ  583

➡️ ዝርፍያ 349

➡️ የመገደል ሙከራ 178

➡️ እገታ 10 

ፖሊድ ወንጀል ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዙ 170 የፓሊስ ኮሚኒቲዎች መቋቋማቸውን ገልጿል።

እየተፈፀሙ ያሉ የወንጀል ተግባራት ያልተለመዱ ናቸው ያለው ፖሊስ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች ለመቆጣጠር ከወትሮው በተለየ የህብረተሰብ ተሳትፎ እጅግ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray

" በ9 ወር 270 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 261 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፤ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት ወድሟል " - የትራንስፖርትና መገናኛ ቢሮ

የትግራይ የትራንስፓርትና የመገናኛ ቢሮ ከሰሞኑን አንድ ሪፖርት ይፋ አድርጎ ነበር።

በዚህም በክልሉ ባለፉት 9 ወራት (ከመስከረም እስከ ግንቦት 2016 ዓ.ም) በትራፊክ አደጋ ምክንያት ብቻ 270 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

261 ሰዎች ደግሞ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በንብረት ላይ የደረሰ ውድመት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ተነግሯል።

በጥናት የተለየው የትራፊክ አደጋ መነሻ ምንድን ነው ?
- ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ መንዳት
- ለእግረኞች ቅድሚያ አለመስጠት
- ከተፈቀደ መስመር ውጪ ማሽከርከር
- ርቀት ጠብቆ አለማሽከርከር
- የአሽከርካሪዎች አቅም ማነስ ናቸው።

እግረኞች ዜብራ ተጠቀመው መንገድ አለማቋረጥ እና ቀኝ መስመር ይዘው መጓዝ በተጨማሪነት የአደጋ መነሻዎች ሆነው ተጠቅሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia