TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EthiopianAirlines🇪🇹

" የችግሩን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

መነሻውን አዲስ አበባ ያደረገ የበረራ ቁጥሩ " ኢቲ106 " የሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቐለ " አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ " ችግር እንዳጋጠመው ይታወቃል።

ይህ በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን አለ ?

- የአውሮፕላኑ በረራ ቁጥር ET106/18 ነው።

- ከአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት የተነሳው ቀን 6:30 ላይ ነው።

- ክስተቱ ያጋጠመው በአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ከቀኑ 8 ስአት አካባቢ ነው። በሚያርፍበት ወቅት ከመንደርደሪያው መንገድ ተንሸራቶ ወጥቷል።

- ሁሉም ተሳፋሪዎችና የበረራ ቡድን አባላት ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም ወጥተዋል።

- ችግሩ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ / የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል።

በተፈጠረው ችግር መጉላላት ለደረሰባቸው መንገደኞችም #ይቅርታ ጠይቋል።

Video Credit - Tigrai Television

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል።

የከተራና የጥምቀት በዓልን ተከትሎ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር ለትራፊክ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

በጥምቀት በዓል በርካታ ህዝብ ታቦታትን አጅቦ ከተለያዩ ቤተ-ክርስቲያናት ወደ ጥምቀተ ባህር የሚንቀሳቀስ በመሆኑ በትራፊክ ፍሰቱ ላይ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ታቦታቱ በሚጓዙባቸው መንገዶች ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት አቁሞ መሄድ የተከለከለ ሲሆን በተለይም በርካታ ህዝብ በሚታደምበት በጃን ሜዳ ከጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ታቦታት ወደ መንበረ ክብራቸው እስኪመለሱ መንገዶቹ ለተሸከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ፡-

- ከ6ኪሎ አደባባይ እስከ 3ተኛ ሻለቃ ፈረንሳይ ለጋሲዬን መንገድ

- ከ3ኛ ሻለቃ አደባባይ በምንሊክ ሆስፒታል እስከ ቀበና አደባባይ

- ከምንሊክ ሆስፒታል እስከ 6 ኪሎ ታክሲ ተራ

- ከቅድስተ ማርያም ቤ/ክርስቲያን እስከ 6 ኪሎ፣

- ከ6ኪሎ እስከ መነን፣

- ከሀምሌ 19 እስከ ግብፅ ኢምባሲ፣

- ከቅድስተ ማሪያም መነጸር ተራ እስከ ጃንሜዳ፣

- ከግንፍሌ ድልድይ ምንሊክ ሆስፒታል ውስጥ ለውስጥ፣

- ከግንፍሌ መገንጠያ ምንሊክ ሆስፒታል ፊት ለፊት፣

- ከምንሊክ ሆስፒታል የኋላ በር እስከ ቤላ መገንጠያ ድረስ፣ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በጃን ሜዳና በዙሪያው ተሽከርካሪ አቆሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ እየገለፀ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላትን ትእዛዝ በመቀበል የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IGAD ዛሬ በኡጋንዳ፣ ኢንቴቤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ይደረጋል። ስብሰባው ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው። ሌላው የሱዳን ጦርነት ነው። ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እስካሁን ድረስ በታወቀው ፦ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጅቡቲው ፕሬዜደንት ኢሳሜል ኦማር ጌሌህ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት…
#IGAD

" ... ማንኛውም #ስምምነት ወይም #ዝግጅት በሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት #ፈቃድ መሆን አለበት " - ኢጋድ

የምሥራቅ አፍሪካ ልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) ዛሬ ኡጋንዳ ኢንቴቤ ውስጥ አስቸኳይ የመሪዎች ስብሰባውን አድርጎ ነበር።

ይህ አስቸኳይ ስብሰባ የኢጋድ መስራቿ ኢትዮጵያን ጨምሮ የኤርትራ እና የሱዳን መንግሥት ተወካዮች / መሪዎች ባልተገኙበት የተካሄደ ነው።

ስብሰባው ትኩረት ያደረገው ስለ ወቅታዊው የኢትዮጵያ እና ሱማሊያ ግንኙነት ጉዳይ እንዲሁም ስለ ሱዳን ጦርነት ነው።

ከኢጋድ አባል ሀገራት የትኞቹ መሪዎች ተገኙ ?

🇩🇯 የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢማኤል ኦማር ጌሌህ (ስብሰባውን የመሩት እሳቸው ናቸው/ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ናቸው)
🇰🇪 የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ
🇸🇴 የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ
🇸🇸 የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫኪየር ማያርዲት
🇺🇬 የኡጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ተገኝተው ነበር።

ሌሎችስ እነማን ተገኙ ?

- የኢጋድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፤
- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ የሱዳን የግል መልዕክተኛ ራምታኔ ላምራ፣
- የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሌድ አልኩራጂ
- የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች / #UAE የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ካሊፋ ሻሂን አል ማራርት
- የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔታ ዌበር፤
- #የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር፤
- የአረብ ሀገራት ሊግ ረዳት ዋና ፀሀፊ ሆሳም ዛኪ
- የኢጋድ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ መሐመድ አብዲ ዋሬ
- የደቡብ ሱዳን የኢጋድ ልዩ መልዕክተኛ እና የሱዳን የሰላም ሂደት የኢጋድ ተወካይ አምባሳደር እስማኤል ዋይስ
- የኢጋድ የቀይ ባህር፣ የኤደን ባህረ ሰላጤ እና የሶማሊያ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር መሀመድ አሊ ጉዮ
- #በቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቱትኩ ኢናም
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ቺክ ኮንዴ ተገኝተው ነበር።

ኢጋድ ከስብሰባው በኃላ ባወጣው መግለጫ ምን አለ ?

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግኙነት መካከል የተፈጠረው ሁኔታ በእጅጉ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

በዋነኛ መርህነት የሶማሊያ ሉዓላዊነት ፣ አድነት እና የግዛት አንድነት ሊከበር ይገባል ሲል አረጋግጧል። ማንኛውም ተሳትፎ ይህንን መርህ ባከበረ መልኩ ሊሆን ይገባል ብሏል። ማንኛውም #ስምምነት ወይም #ዝግጅት በሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት #ፈቃድ መሆን አለበት ብሏል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው ያለውን ውጥረት በማርገብ በምትኩ ገንቢ የሆነ ውይይት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

ኢትዮጵያ ስብሰባው ላይ ለምን አልተገኘችም ?

ኢትዮጵያ ከዛሬው የአስቸኳይ ስብሰባ ቀደም ብላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል " በተደራራቢ መርሃ ግብር " ምክንያት በዚህ ስብሰባ ላይ መገኘት እንዳማትችል ለጂቡቲ የውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ትብብር እና ኢጋድ በድብዳቤ አሳውቃለች።

ኢጋድ ከጠራው ጉባኤ ቀደም በሎ ከተያዘ መርሃ ግብር ጋር የሚጋጭ በመሆኑ እና የተቀመጠውም ጊዜ አጭር በመሆኑ በስብሰባው ላይ መገኘት እንደሚያስቸግራት በዚሁ ደብዳቤ አሳውቃ ነበር።

ነገር ግን " ኢጋድ በሚመራበት ደንብ መሰረት " በተለዋጭ ቀን ለመወያየት ዝግጁ መሆኗን አሳውቃቸዋለች።

(ሙሉ የኢጋድ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
Forwarded from telebirr
በህብረ ቀለማት አሸብርቆ፣ ከሁሉም ማዕዘን በአብሮነት አሰባስቦ በአንድነት በሚንቆጠቆጠው የጥምቀት በዓል ተጨማሪ ድምቀት የሆኑትን ልዩ የሞባይል ጥቅሎች እስከ 25% በሚደርስ ቅናሽ አሰናድተን እነሆ በሰፊው ገበታችን አቅርበናል!

የጥምቀት ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል፣ አርዲ ቻትቦት እንዲሁም *999# ለራስዎ እየገዙ ለሚወዷቸውም በስጦታ እያበረከቱ የበዓል መልካም ምኞትዎን ያድርሱ!

መልካም አውደዓመት!
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
25 ዓመታት በሕብረት

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

ቴሌግራም- https://publielectoral.lat/HibretBanket
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank
እንኳን ለጥምቀት ከተራ በዓል አደረሳችሁ !

መልካም በዓል !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ " ስለ ስምምነቱ ቀድሞውኑ የሚመለከታቸው ሀገራት እና ተቋማት እውቅናው ነበራቸው ፤ ግን አላዋቂ ለመምሰል ጥረት እያደረጉ ነው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን ስለ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ምን አሉ ? " ኢትዮጵያ ከባህር በር ጋር በተያያዘ ዕድል ያላት የሚመስለው ከሰሜን በኩል ነበር። ሁሉም ሰው ስለ ባህር…
" የባሕር በር ጉዳይ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው " - ኢትዮጵያ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ?

" ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው።

ከሶማሌላንድ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ከዓላማው ውጪ የሆኑ የተሳሳቱ መረጃዎች ተሰራጭተዋል።

የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው።

ኢትዮጵያ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ በጅቡቲ ወደብ በኩል የገቢ ወጪ ንግዷን እያከናወነች ነው። አሁን ካለው አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታ አኳያ አማራጮችን መፈለግ ግድ ይላል።

ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላም እና ፀጥታ የሕይወት መስዕዋትነት ከፍላለች። ከሶማሊያም ሆነ ከሌሎች ጎረቤት አገራት #በጋር_ጥቅም ላይ የተመሰረተ ትብብር ታደርጋለች።

ከሶማሊ ላንድ ጋር የተደረገው የመግባቢያ ስምምነት እያደገ የመጣውን የሕዝብ ቁጥር እና ኢኮኖሚ ምላሽ መስጠትን ዓላማ ያደረገ እንጂ ማንንም ለመጉዳት አይደለም። "

አምባደር ሬድዋን ሁሴን ይህን ያሉት በአዲስ አበባ ተቀማጭነታቸውን ላደረጉ የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

Via ENA

@tikvahethiopia
" የኢትዮጵያ እግር ውሃ መርገጥ አለበት "

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ምን አሉ ?

" ግብፅን ጨምሮ ሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች እዚህ አፍንጫችን ስር የባህር መዳረሻ እና ወደብ ሲከፍቱ ኢትዮጵያ ስታደርገው ነውር የሚሆነንበት አመክንዮ ምንድነው ?

ሶማሌላንድ ውስጥ ሌሎች ሀገሮች አላቸው። ኢትዮጵያ እንዲውም ወደብ የላትም። አለመታደል ሆኖ የዚህ ወጣት የሆነው ትውልድ ዕጣፈንታ የተወሰነበት መንገድ መለወጥ ስላለበት ጉዳዩ የፍትህም፣ የርትህም ፣ የልማትም ፣ የሰላምም ጉዳይ ስለሆነ ኢትዮጵያ የባህር መዳረሻ ያስፈልጋታል።

የኢትዮጵያ እግር ውሃ መርገጥ አለበት። "

@tikvahethiopia