TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ " ስለ ስምምነቱ ቀድሞውኑ የሚመለከታቸው ሀገራት እና ተቋማት እውቅናው ነበራቸው ፤ ግን አላዋቂ ለመምሰል ጥረት እያደረጉ ነው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን ስለ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ምን አሉ ? " ኢትዮጵያ ከባህር በር ጋር በተያያዘ ዕድል ያላት የሚመስለው ከሰሜን በኩል ነበር። ሁሉም ሰው ስለ ባህር…
" የባሕር በር ጉዳይ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው " - ኢትዮጵያ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ?

" ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው።

ከሶማሌላንድ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ከዓላማው ውጪ የሆኑ የተሳሳቱ መረጃዎች ተሰራጭተዋል።

የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው።

ኢትዮጵያ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ በጅቡቲ ወደብ በኩል የገቢ ወጪ ንግዷን እያከናወነች ነው። አሁን ካለው አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታ አኳያ አማራጮችን መፈለግ ግድ ይላል።

ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላም እና ፀጥታ የሕይወት መስዕዋትነት ከፍላለች። ከሶማሊያም ሆነ ከሌሎች ጎረቤት አገራት #በጋር_ጥቅም ላይ የተመሰረተ ትብብር ታደርጋለች።

ከሶማሊ ላንድ ጋር የተደረገው የመግባቢያ ስምምነት እያደገ የመጣውን የሕዝብ ቁጥር እና ኢኮኖሚ ምላሽ መስጠትን ዓላማ ያደረገ እንጂ ማንንም ለመጉዳት አይደለም። "

አምባደር ሬድዋን ሁሴን ይህን ያሉት በአዲስ አበባ ተቀማጭነታቸውን ላደረጉ የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

Via ENA

@tikvahethiopia