TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአዲስ ተማሪዎች ምደባ #በቀናት ውስጥ ይፋ የሚደረግ ይሆናል። ይህን ተከትሎ ዩኒቨርስቲዎች በሚያወጡት ፕሮግራም መሰረት አዲስ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲገቡ ይደረጋል። ዩኒቨርስቲዎችም ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ አስፈላጊውን #ዝግጅት አጠናቀዋል።

©ዶ/ር ሳሙኤል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በመቀለ ከተማ ከ77 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የ11 ኪሎ ሜትር የድንጋይ ንጣፍ መንገድ ግንባታ ሥራ ለማከናወን #ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሩን የ2019 አፍሪካ ዋንጫን በሀገራ የማስተናገድ መብት መነጠቋን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡ ካሜሩን በመጪው #ሰኔ ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለትን የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ መብት የተነጠቀችው የዋንጫ ውድድሩን ለማሳናዳት በቂ እና አሳማኝ #ዝግጅት ባለማድረጓ ነው ተብሏል፡፡ በመሆኑም የአዘጋጅነቱ መብት ለአዲስ ሀገር በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚሰጥ ትናንት ጋና አክራ ላይ በተደረገው የካፍ ስራ አስፈጻሜ ኮሚቴ ረዥም ስብሰባ መወሰኑን ነው የተነገረው፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ
ህዳር 22/03/2011 ዓ.ም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech-----አባያ ካምፓስ👆

#በአባያ_ካምፓስ----አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ከTIKVAH-EHT ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 2ኛው #የStopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ #ዝግጅት በዛሬው ዕለት በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።

እናመሰግናለን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MoSHE

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተከታዩን ብለዋል ፦

- በዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች በየደረጃው ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ የሚያስችል ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው።

- በቅርቡ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በየተራ ተማሪዎቻቸውን ይቀበላሉ።

- በሀገሪቱ ሁሉም ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ወደዩኒቨርሲቲ ለማምራት #ዝግጅት ማድረግ አለባቸው።

- በ44 ዩኒቨርሲቲዎች በተደረገ ግምገማ አብዛኛዎቹ ኮሮና ቫይረስን በመከላከል የመማር ማስተማሩን ሂደት ማከናወን በሚችሉበት ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

- የቀሩ ጥቂት ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣይ ሳምንት ዝግጅታቸውን እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

- የጤና ፕሮቶኮል እና የሰላም ሁኔታውን የሚያስጠብቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል።

- በተጨማሪም በአመቱ ከክህሎት እና እውቀት በተጨማሪ የስብእና ግንባታ ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን በስርአተ ትምህርቱ ይካተታል። (ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ዝግጅት_ጥቆማ

ልባም ህይወት !

በኒውሮ ሊንጉስቲክ ፕሮግራሚንግ ፕሪክቲሼኔር የሚሰጥ - "መጥፎ እና ጥሩ ሀሳብ ወደ አእምሮአችን እንዴት ይመጣል?"

ፕሮግራሙ ሀምሌ 30/2013 ዓ/ም ከምሽት 12 እስከ 1:45 የሚካሄድ ሲሆን ፕሮግራሙ በነፃ የሚሰጥ ነው።

በስልክ ቁጥር 0911624348 ወይም 0911280510 ስም በቴክስት በመላክ ቦታ መያዝ እንደሚቻል አዘጋጆቹ ለቲክቫህ አሳውቀዋል።

22 ወደ መገናኛ በሚወስደው መንግድ ብሉ በርድ ሆቴል አጠገብ ነው ፕሮግራሙ የሚካሄደው።

@tikvahethiopia